የኬንያ የፖለቲካ አለመረጋጋት የግሉ ዘርፍ እድገት አሽቆልቁሏል

የቢዝነስ ቦርድ Image copyright AFP

በኬንያ በተከሰተው የፖለቲካ አመረጋጋት የግሉ ዘርፍ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛ ነው የተባለ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በባንኮች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው የቢዝነስ ተቋማት ግዙፍ ኢንቨስትመንቶችን አዘግይተው የምርጫውን ውጤት መጠባበቅን መርጠዋል።

መንግሥት በሥራ ላይ ያዋለው ለንግድ ሥራዎች የሚሰጠው የብድር ወለድ ምጣኔ ጣሪያም የብድር አቅርቦቱን አስቸጋሪ አድርጎታል።

ጥናቱን ያደረገው ስታቢክ ባንክ እንደሚለው የኬንያ የኢኮኖሚ ጤናማነት መለኪያዎች ላለፉት 5 ተከታታታይ ወራት ከ2014 ወዲህ ዝቅተኛ ቦታ ላይ ይገኛሉ።

የባንኩ የምጣኔ ሃብት ባለሞያ ጂብራን ኩሬሺ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ኬንያ ያለችበት የፖለቲካ ሁኔታ ነው ይላሉ።

ኬንያ በነሐሴ ወር ያካሄደችው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፍርድ ቤት በመሰረዙ በቅርቡ ሌላ ምርጫ ታካሂዳለች።