በአሜሪካ የጦር መሣሪያን የተመለከተ አዲስ ህግ እንዲወጣ ተጠየቀ

bump stock Image copyright Reuters

የአሜሪካ ብሄራዊ ጠብመንጃ ማህበር የላስ ቬጋሱ ጥቃት ፈጻሚ በጠብመንጃው ላይ የገጠመው የፍጥነት ማቀላጠፊያ መሣሪያ ላይ ' ተጨማሪ ቁጥጥር' እንዲደረግ ጠየቀ።

ቡድኑ እንዳለው ''ከፊል-አውቶማቲክ ጠመንጃዎች እንደ ሙሉ አውቶማቲክ እንዲተኩሱ ለማስቻል የሚገጠሙት መሣሪያዎች ተጨማሪ ቁጥጥር ያስፈልጋቸዋል''

ሪፐብሊካኖችም ጉዳዩን ለዓመታት ቢቃወሙትም መሣሪያውን ለማገድ የቀረበውን ኃሳብ እንደሚያጤኑት ተናግረዋል።

ህግ አውጪዎች የመሣሪያውን ህገወጥነት በሚደነግግ ህግ ዙሪያ ለመሞከር እቅድ ይዘዋል።

ማህበሩ መሣሪያው የሀገሪቱን ብሄራዊ ህጎች እንደማይጥስ ግምገማ እንዲደረግበትም ጥሪ አቅርቧል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደራቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ መሣሪያው መታገድ ያስፈልገው እንደሆነ ይመለከታል ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ