ስለካታሎንያ ነጻነት ጥያቄና መልስ

Barcelona anti-police roadblock, 3 Oct 17 Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ በባርሴሎና የተሰባሰቡ ሰልፈኞች

የስፔን መንግሥት ህገወጥ ነው ያለውን ሕዝበ-ውሳኔ ተከትሎ የካታሎንያ ተገንጣዮች መንግሥት ነጻነቱን በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚያውጅ አስታውቋል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሠልፍ ከወጡ በኋላ ውጥረቱ አይሏል።

እንዴት እዚህ ተደረሰ?

የ7.5 ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ የሆነችው ካታሎኒያ በስፔን ከሚገኙ ሃብታም እና ምርታማ ግዛቶች አንዷ ናት። ከስፔን የእርስ በእርስ ጦርነት በፊት ራሷን ችላ ቆይታለች። እ.አ.አ ከ1939-75 በቆየው የጄነራል ፍራንኮ አምባገነናዊ አገዛዝ ወቅት ግን ይህን መብቷን ተነጥቃለች።

ፍራንኮ ሲሞት የካታላኖናውያን ብሔርተኝነትም ማቆጥቆጥ ጀመረ። ከዚህም ጋር ተያይዞ እአአ የ1978ቱ ህገመንግስትም የሰሜን ምስራቅ ክልል ራሱን እንዲያስተዳደር ፈቃድ ሰጥቷል።

እ.አ.አ በ2006 የወጣው ደንብ ደግሞ ይህን ኃይል ይበልጥ ቢያሳድገውም የስፔን ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤት እ.አ.አ በ2010 አብዛኛውን ውሳኔ ቀይሮታል። ይህ ሁኔታ በአካባቢው ኃላፊዎች ዘንድ ቁጣን ፈጥሯል።

ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄያቸው መልስ ከማጣቱም በላይ በተቀረው አካባቢ በተስፋፋው ሙስናና የመወሰን ብቃት ማነስ ስፔንን ለኢኮኖሚ ድቀት ዳርጎ የሚገባቸውን ድጋፍ እንዳያገኙ እንዳደረጋቸውም ይገልጻሉ። በዚህም ተገፋፍተው እ.አ.አ በ2014 ይፋዊ ያልሆነ የነጻነት ምርጫ አካሂደዋል። 80 በመቶ ድምጽ ሰጪዎች የመገንጠል ጥያቄን መደገፋቸውን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የመገንጠል ጥያቄ ያነገቡ ሃይሎች እ.አ.አ የ2015ቱን የካታሎንያን ምርጫ አሸንፈዋል። ስፔን አትለያይም የሚለውን የሃገሪቱን ህገመንግስት በመጻረርም ህዝበ-ውሳኔ እንደሚያካሂዱ አስታውቀዋል።

ጥያቄው ምንድነው?

በምርጫው ወረቀት ላይ አንድ ጥያቄ ብቻ ነው ያለው፡ "ካታሎንያ ነጸነቷን የተቀዳጀች ሪፐብሊካዊ መንግስት እንድትሆንት ትፈልጋላችሁ?" የሚል።

በተጨማሪም ሁለት የመልስ አማራጮች ቀርበዋል፡ "አዎ ወይም አይደለም" የሚል።

እንደአወዛጋቢው ህግ ከሆነ ውሳኔው የማይቀለበስ ሲሆን የካታሎንያ የምርጫ ቦርድ ውጤቱን ይፋ ባደረገ በሁለት ቀናት ውስጥ ፓርላማው ውሳኔውን ማወጅ አለበት። ውጤቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚገለጽ ይጠበቃል።

Image copyright EPA

ካታሎናያን ነጻነቱን በእርግጥ ይፈልጋሉ?

የነጻነት ፈላጊ ደጋፊዎች መገንጠልን ደግፈው ትልልቅ ሰልፎችን አካሂደዋል። መስከረም ወር በሚከበረው ብሄራዊ ቀን ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ባርሴሎና አደባባይ ወጥተዋል።

ጉዳዩን በይበልጥ ያሳያል የተባለው የህዝብ አስተያት ድምጽ ባለፈው ሐምሌ ይፋ ተደርጓል። በካታሎንያ መንግሥት ድጋፍ በተካሄደው የህዝብ አስተያየት ድምጽ እንደሚያሳው 41 በመቶ ድምጽ ሰጪዎች ነጻነቱን ሲደግፉ 49 በመቶዎቹ ግን ተቃውመውታል።

እ.አ.አበ2014 በተደረገው ምርጫ2.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ግለሰቦች ነጻነትን መርጠዋል። የተገንጣዮች ህብረት ፓርቲ የሆነው ጁንትስ ፔል ሲ የግራ ክንፍ ፓርቲ ከሆነው ሲ ዩ ፒ ጋር በመሆን እ.አ.አበ2015 ምርጫ 48 በመቶ ድምጽ አግኝቷል።

ለነጻነት የሚደረገው ድጋፍ ተዳክሟል ቢባልም የስፔን ባለስልጣናት ምርጫው እንዳይካሄድ በፖሊሶች የወሰዱት ጠንካራ እርምጃ ብዙዎችን መጉዳቱና ሃዘን ያልተሰማው የንጉሱ የአንድነት ንግግር የተገንጣዮችን ምክንያት የደገፈ ሆኗል።

Image copyright EPA

ካታሎንያ ሃገር ለመሆን ጥሩ ምክንያት አላት?

ካታሎንያ የራሷ ቋንቋ እና ከአንድ ሺህ ዓመት በላይ የቆየ ራሷን የቻለ የክልል ታሪክ አላት።

እንደተገንጣዮች ከሆነ አካባቢውን "ይበልጥ ስፔናዊ" የማድረግ ከፍተኛ ስራ በስፔን መንግሥት እየተሰራ ነው።

ከስፔን ሃብታም አካባቢዎች አንዷ የሆነችው ካታሎንያ 16 በመቶ የህዝብ ቁጥርና ከስፔን ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 19 በመቶውን ትይዛለች። ሆኖም ማዕከላዊው መንግስት መልሶ ከሚሰጠው ይልቅ የሚወስደው ይበዛል የሚል ስሜት በብዙዎች ዘንድ አለ።

እ.አ.አ በ2014 ካታሎንያ ለስፔን ታክስ ባለስልጣን 9.89 ቢሊዮን ዩሮ ስታስገባ ያገኘችው ግን ከዚህ ቁጥር ያነሰ ነው።

የማቻቻል ዕድል ይኖር ይሆን?

ሁለቱም አካላት ካላቸው ጠንካራ አቋም አንጻር አንዱ ሌላኛውን የሚችልበት ዕድል ያለ አይመስልም። በምንም መልኩ ግን እርግጠኛ መሆን አይቻልም።

ተያያዥ ርዕሶች