ዩኒቨርሲቲው እና ተማሪዎቹ በመስማማታቸው ወደ ቅጥር ግቢው እንዲመለሱ ተደርጓል።

Image copyright Bahir Dar University

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የ4ኛ ዓመት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ተቋም ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ለብቃት ምዘና ፈተና ዝግጅት በቂ ጊዜ አልሰጠንም፤ የምዘና ስርዓቱም አዲስ እና አግባብነት የሌለው ነው በማለት ፈተናውን አንወስድም በማለታቸው ከቅጥር ግቢ እንዲወጡ መደረጉ ይታወሳል።

ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ የምዘና ስርዓቱ የነበረ ነው በማለት የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት አቋርጦ ካሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ ተማሪዎቹ በፖሊስ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ አድርጎ ነበር።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ1400 በላይ ተማሪዎችን ከግቢው አስወጣ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፡ ዛሬም አዲስ ነገር የለም ይላሉ

አብዛኛው ተማሪም አዳሩን በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ አድርጎ የነበረ ሲሆን በምግብ በኩል የከተማው ነዋሪዎች ባሰባሰቡት መዋጮ ፈቃደኛ ግለሰቦች ሲያበሰሉላቸው ነበር።

ዛሬ ከተማሪዎቹ እና ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ንጉስ ጋቢዬ ማረጋገጥ እንደቻልነው ለፈተና ዝግጅት ከ2 ያላነሰ እና ከ3 ሳምንት ያልበለጠ ጊዜ እንዲሰጣቸው በመስማማት ወደ ግቢው ተመልሰዋል።

በስልክ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እንደነገሩን አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ወደ ቅጥር ግቢ እየተመለሱ እንደሆነና የምግብ አገልግሎት እንደተጀመረ ነገረውናል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ