ላውሮ እና ሙዚቀኛው ሬች 32 የሳምንቱን የፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎች ገምተዋል

ጆሴ ሞሪንሆ ባለፈው ዓመት ቡድናቸውን ይዘው ወደ አንፊልድ ባቀኑበት ወቅት የመከላከል ጨዋታን መርጠው ነበር። ቅዳሜ ምን ዓይነት ጨዋታን ይመርጣሉ?

የቢቢሲው የስፖርት ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን በሳምንታዊው የፕሪሚየር ሊግ የጨዋታዎች ውጤት ግምቱ ዩናይትድ ለማሸነፍ ፍላጎቱን ከፍ ቢያደርግም የተለየ አጨዋወት ይዞ ላይቀርብ ይችላል ይላል።

በዚህ ሳምንት ከላውሮ ጋር በመሆን ግምቱን የሚሰጠው ሙዚቀኛው ጀርማይን ስኮት በመድረክ ስሙ ሬች 32 ተብሎ የሚታወቀው ራፐር ነው።

በቶተንሃም የተወለደው ሬች 32 ከልጅነቱ ጀምሮ የአርሴናል ደጋፊ መሆኑን ይገልጻል። የቀድሞው የመድፈኞቹ ተጫዋች ኢያን ራይት ደግሞ ክለቡን እንዲደግፍ ምክንያት ከሆኑት ተጫዋቾች ቀዳሚው መሆኑን ይጠቅሳል።

Image copyright Rex Features
አጭር የምስል መግለጫ የአርሴናል የደጋፊ ሆነው ድምጻዊው ሬች 32

የላውሮ ግምት

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ሊቨርፑል ከማንስተር ዩናይትድ

ሁለቱ ክለቦች ካላቸው ታሪክ አንጻር አሁንም የሃገሪቱ ትልቅ ጨዋታ እንደሆነ አምናለሁ።

የየርገን ክሎፕ ቡድን ባለፈው ነሐሴ አርሴናልን 4 ለ 0 ካሸነፈ በኋላ ለ90 ደቂቃ ጥሩ ሆኖ ያሳለፈበት ጨዋታ የለም።

ማሸነፋቸውን የሚያረጋግጥ ውጤት ሳይዙ በተደጋጋሚ በተከላካዮች ስህተት ጎል እየተቆጠረባቸው ይገኛል።

ሁለቱም ቡድኖች ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን በጉዳት አጥተዋል። ፖል ፖግባ እና ማሩዋን ፌላይኒ ከማንቸስተር ዩናይትድ ሳዲዮ ማኔና አዳም ላላና ከሊቨርፑል ጨዋታው ያልፋቸዋል።

በሁለቱም በኩል አደገኛ አጨዋወቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ጨዋታውን የሚመሩት ማርቲን አትኪንሰን የሚሰጡት ውሳኔ ጨዋታውን ሊወስን ይችላል።

የላውሮ ግምት: 1-1

የሬች 32 ግምት: የተቀራረቡ ቡድኖች ቢሆኑም ማንቸስተር የሚያሸንፍ ይመስለኛል። ሊቨርፑል ጥሩ እየተጫወተ ቢሆንም ማንቸስተር አሁን በጠንካር ጉዞ ላይ ይገኛል። ስለዚህ ሊቨርፑል 1-2 ማንችስተር ዩናይትድ

Image copyright BBC Sport

በርንሌይ ከ ዌስት ሃም

ሁለቱም ቡድኖች የመጨረሻ ጨዋታዎቻቸውን አሸንፈዋል።

በርንሌይዎች ከሜዳቸው ውጭ ሲጫወቱ በሚኖርባቸው ግፊት ምክንያት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ይበልጥ የተመቻቸው ይመስላል።

ከዚህ በተጨማሪም ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ጥሩ ተጫዋቾችን ይዘዋል።

ሁለቱም ቡድኖች ደስተኛ ባይሆኑበትም ጨዋታው በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስለኛል።

የላውሮ ግምት: 1-1

የሬች 32 ግምት: 0-0

Image copyright BBC Sport

ክሪስታል ፓላስ ከ ቼልሲ

ክሪስታል ፓላስ በዘንድሮው ዓመት ምንም ነጥብ ካላመያዙም በላይ ጎል ማስቆጠርም ተስኖታል። የዊልፍሬድ ዛሃ ወደ ልምምድ መመለስ ተስፋ ሰጪ ሆኗል።

ቼልሲ በበኩሉ ኑጎሎ ካንቴንና አልቫሮ ሞራታን በጉዳት ቢያጣም ክሪስታል ፓላስ በጨዋታው ነጥብ ያገኛል ተብሎ አይጠበቅም።

መልስ የማይገኝለት ጥያቄ የሚመስለው ጎሎቹን ማን ያስቆጥራል የሚለው ነው።

የላውሮ ግምት: 0-2

የሬች 32 ግምት: 0-2

Image copyright BBC Sport

ማን ሲቲ ስቶክ

ማንቸስተር ሲቲ እያስመዘገበ የሚገኘው ውጤት ከጉዳት ተመልሶ ልምምድ የጀመረውን ሰርጂዮ አጉዌሮ ያጣ አይመስልም።

ጥሩ ውጤትም በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ።

ስቶክ ባለፈው ዓመት ወደ ኢትሃድ አቅንቶ አቻ መለያየቱ ይታወሳል።

ዘንድሮ ግን ሲቲን አጥቂ ተቋቁመው ይህን ማሳካት ይችላሉ ብዬ አላምንም።

የላውሮ ግምት: 3-0

የሬች 32ግምት: የትኛውም የሊጉ ቡድን ከሲቲ አጥቂ ጋር የሚወዳደር አይደልም ሆኖም ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል። 1-1

Image copyright BBC Sport

ስዋንሲ ከ ሃደርስፊልድ

ሁለቱም ቡድኖች ሶስት ነጥብ ማግኘት ከቻሉ ቆየት ብለዋል።

ሰዋንሲዎች ጎል የማስቆጠር ችግር አለባቸው።

ሃደርስፊልዶች ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ካለመቻላቸውም በላይ አንድ ጎል ብቻ ነው ያስቆጠሩት።

ሁለቱ ቡድኖች አሁን ባላቸው አቋም ላለመውረድ የሚጫወቱ ይመስላሉ።

ጨዋታውን ስዋንሲዎች ማሸነፍ የሚፈልጉት በመሆኑ ይህንን ለማድረግ ብዙ ይጥራሉ።

ላውሮ ግምት: 2-0

የሬች 32 ግምት: 1-0

Image copyright BBC Sport

ቶተንሃም ከርንማውዝ

እስካሁን በዌምብሌይ ማሸነፍ ያልቻሉት ቶተንሃሞች በዚህ ሳምንት የሚሳካላቸው ይመስላል።

በርንሌዮች በቀላሉ ጎል ከማስተናገዳቸውም በላይ የቶተንሃሙ አጥቂ ሃሪ ኬንም በምርጥ ብቃቱ ላይ ይገኛል።

ላውሮ ግምት: 2-0

የሬች 32 ግምት: 1-0

Image copyright BBC Sport

ዋትፎርድ ከ አርሴና

የላውረን ኮሽልኒ መሰለፍ አራጣሪ መሆኑና የሙስጣፊ መጎዳት የአርሴናል ተከላካይ መስመር ችግር ላይ ሊጥለው ይችላል።

አርሴናል ባለፈው ነሐሴ በሊቨርፑል ከደረሰበት ሽንፈት ማገገም ችሏል።

እንደብርንሌይ ሁሉ ዋትፎርድም ዘንድሮ አስደናቂ ቡድን መሆኑን እያሳየ ቢሆንም በሜዳው ግን ማሸነፍ እየቻለ አይደለም።

ላውሮ ግምት: 0-2

የሬች 32's ግምት: አርሴናል 3 ለ 0 ያሸንፋል። አርሰን ቬንገር ዘንድሮ ይቆይ፤ ስለሚቀጥለው ዓመት ወደፊት መፍትሄ ይሰጠዋል።

እሁድ

Image copyright BBC Sport

ብራይተን ከ ኤቨርተን

ኤቨርተን ያለበትን የአጥቂ ችግር ለመፍታት እስከ ጥር ዝውውር መስኮት መጠበቅ ይኖርበታል።

በመጪው እሁድ ለኤቨርተን ከባድ ፈተና የሚሆነው ጠንካራውን የብራይተንን ተከላካይ መስበር መቻል ነው።

የክሪስ ሁውተን ቡድን መከላከልን መሠረት ያደረገ አጨዋወትን ይመርጣል።

የላውሮ ግምት: 1-1

የሬች 32 ግምት: ሩኒ ጎል አስቆጥሮ ኤቨርተን ያሸንፋል። 0-1

Image copyright BBC Sport

ሳውዝሃምፕተን ከ ኒውካስትል

ራፋኤል ቤኒቴዝ ኒውካስትል ከሊቨርፑል ጋር ባደረገው ጨዋታ ቡድናቸውን ምን ያህል ጥሩ ማድረግ እንደሚችል ያሳዩበት ነበር።

ኒውካስትሎች በእሑዱ ጨዋታ ጥሩ ውጤት ያስመዘግባሉ ብዬ አልጠብቅም።

ሳውዝሃምፐተኖች ጎል የማስቆጠር ችግር ቢኖርባቸውም በዚህኛው ጨዋታ የተሻለ ዕድል አላቸው።

የላውሮ ግምት: 2-1

የሬች 32 ግምት: 2-2

ሰኞ

Image copyright BBC Sport

ሌስተር ከ ዌስት ብሮም

ሁለቱም ቡድኖች በዚህ ወር ሶስት ነጥብ ማስመዝገብ አቅቷቸው ነበር።

የጂሚ ቫርዲ ከጉዳት መመለስ ለሌስተሮች ተስፋ ይሰጣል።

የዌስትብሮሙ አሰልጣኝ ስጋት የሚሆነው አዲሶቹን የክለቡ ባለቤቶች ማስደሰት መቻላቸው ነው።

የላውሮ ግምት: 2-0

የሬች 32 ግምት: ጂሚ ቫርዲ አንድ ጎል አስቆጥሮ ሌስተር ያሸንፋል። 2-0