በሳምንቱ የጋሬዝ ክሩክስ ቡድን ውስጥ ደብሩይን፣ የሱስ፣ ደ ሂያ፣ ስተርሊንግና ክሌቨርሌይ ተካተውበታል።

ማንቸስተር ሲቲ ስቶክ ሲቲን 7 ለ 2 በማሸነፍ ሊጉን በሁለት ነጥብ ልዩነት መምራት ችሏል።

በጉጉት የተጠበቀው የሊቨርፑልና የማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ ክሪስታል ፓላስ የመጀመሪያ ድሉን ቼልሲን በማሸነፍ አሳክቷል።

ዋትፎርድ ምርጥ ብቃቱን አርሴናልን በመርታት ቀጥሎበታል።

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድና የቶተንሃም ሆትስፐር ተጫዋች የሆነው ጋሬዝ ክሩክስ የሳምንቱን ምርጥ አስራ አንድ እንደሚከተለው አቅርቧል።

ግብ ጠባቂ -ዴቪድ ደ ሂያ (ማንቸስተር ዩናይትድ)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በዘህ ሳምንት ከደ ሂያ በላይ ብዙ ኳሶችን ያዳነ ግብ ጠባቂ የለም

ፕሪሚየር ሊጉን ለማሸነፍ ትልቅ ግብ ጠባቂ መያዝ ያስፈልጋል። ደ ሂያ ከእነዚህ ግብ ጠባቂዎች አንዱ መሆኑን ሁሉም ይስማማበታል።

የሊቨርፑሉ ተከላካይ ጆኤል ማቲፕ የሞከረውን ኳስ በእግሩ ያዳነበት መንገድ አስደናቂ ነው።

ኳስ በእግሩ በማዳን በኩል የቀድሞው ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ፒተር ሽማይክል ተጠቃሽ ነው። በዚህ በኩል የቀድሞውን የሰሜን አየርላንድ ግብ ጠባቂ ፓት የኒንግስን የሚስተካከል አይገኝም።

ደ ሂያ በዚህ ረገድ ሁለተኛ እየሆነ ሲሆን እንደሱ ብቃት ባይሆን ማንቸስተር ዩናይትድ ከአንፊል ነጥብ ይዞ አይመለስም ነበር።

ተከላካይ - ፊል ጆንስ (ማንቸስተር ዩናይትድ)

Image copyright Rex Features
አጭር የምስል መግለጫ ፊል ጆንስ

ፊል ጆንስ ከጨዋታ ወደ ጨዋታ ራሱን በማሻሻል ላይ ይገኛል።

እንግሊዛዊው ተከላካይ በሊቨርፑል ጨዋታ ከእረፍት በፊት ብቻ ሁለት ጊዜ አስደናቂ ውሳኔ በመወሰን አጥቂዎች ጥሩ ዕድል እንዳይፈጥሩ አድርጓል።

አጥቂዎች ውሳኔ መወሰን እንዳይችሉ የሚያደርግ ተጫዋች ድንቅ ተከላካይ ነው። ጆንስ ይህንን በተደጋጋሚ በማሳየት ላይ ይገኛል።

ተከላካይ - ፐር መርተሳከር (አርሴናል)

Image copyright Rex Features
አጭር የምስል መግለጫ ፐር መርተሳከር ከ1400 ቀናት በኋላ ግብ አስቆጥሯል

በሳምንቱ ምርጥ ቡድኔ ውስጥ የተሸናፊ ቡድን ተጫዋችን የመምረጥ ልምድ ብዙም የለኝም።

በቪካሬጅ ሮድ በተደረገው ጨዋታ ከተከላካይ መስመር ለአሌክስ ኢዮቢ ድንቅ ኳስ ተሻግሮለታል።

ኳሱን ያቀበለው ፐር መርቲሳከር መሆኑ አስደንቆኛል።

ያስቆጠራት ኳስም ከህጻን ልጅ ከረሜላ እንደመቀበል የሚቀለው ነበር።

ተከላካይ - ማማዱ ሳኮ (ክሪስታል ፓላስ)

Image copyright Rex Features

ይህ ተጫዋች ባለፈው ዓመት ለክሪስታል ፓላስ ድንቅ ከመሆኑም በላይ ውጤታቸውም ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ነበረው።

ሳኮ በቋሚነት ፊርማውን ለክለቡ ማስቀመጡ ለፓለስ ደጋፊዎች ምርጡ ውሳኔ ነው።

ቼልሲ ወደ መሪዎቹ ቡድኖች ለመጠጋት ባደረገው ጨዋታ ሳኮ ጠንካራ ሆኖ አምሽቷል።

በተለይ አጥቂውን ሚቺይ ባትሹዋይን እንዳይንቀሳቀስ አድርጎት ነበር።

አማካይ - ጆይ ጎሜዝ (ሊቨርፑል)

Image copyright Reuters

ሊቨርፑል ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ባደረገው ጨዋታ ጆይ ጎሜዝ ድንቅ ሆኖ አምሽቷል።

እንግሊዛዊው ጎሜዝ የመስመር ተከላካይ ወይም የኋላ ተከላካይ በመሆን መጫወት ይችላል።

ሊቨርፑል ደካማ በሆነበት የመከላከል ስራም ጎሜዝ ጥሩ መሆኑ አስደስቶኛል።

አንቶኒ ማርሻል እና ማርከስ ራሽፎርድ የተለመደ እንቅስቃሴያቸውን እንዳያደርጉ በማድረግ ሚናውን በሚገባ ተወጥቷል።

አማካይ - ኬቪን ደብሩይን (ማንቸስተር ሲቲ)

Image copyright Rex Features

ቤልጂየማዊው ያሳየው ብቃት በዚነዲን ዚዳን ደረጃ የሚቀመጥ ነው።

ለሮይ ሳኔ ሁለተኛ ጎል ባስቆጠረበት ወቅት ደብሩይን ያቀበለበት መንገድ ደጋፊዎችን አፍ የሚያሲዝ ነው።

ጋብርኤል የሱስ አራተኛ ጎል ሲያስቆጥርም ምርጥ ኳስ ከቤልጂየማዊው አግኝቷል።

አማካይ - ቶም ክሌቨርሌይ (ዋትፎርድ)

Image copyright Getty Images

ትሮይ ዴንይ ከአርሴናል ጨዋታ በኋላ በሰጠው አስተያየት ቶም ክሌቨርሌይ በዕለቱ ብቻ ሳይሆን በአዲሱ ውድድር ዓመትም ምርጥ ብቃቱን እያሳየ ነው ማለቱ ትክክል ነው።

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድና ኤቨርተን ተጫዋች ብቃቱን በዋትፎርድ በማሳየት ላይ ይገኛል።

በቀድሞ ክለቦቹ ከስራው በበለጠ በዋትፎርድ መንቀሳቀስም ችሏል።

አማካይ - ራሄም ስተርሊንግ (ማንቸስተር ሲቲ)

Image copyright Getty Images

ስተርሊንግ ጎል ጋር ሲደርስ ጭንቀቱ ከፍተኛ መሆኑ የተለመደ ቢሆንም አሁን እየተየቀረ ይመስላል።

ፔፕ ጋርዲዮላ ይበልጥ እንዲረጋጋ አግዞታል።

እንደ ሳኔና ጋብርኤል የሱስ ያሉ ወጣት ተጫዋቾች መምጣታቸውም ክለቡን እንዲላመደው ረድቶታል።

ምክንያቱ ምንም ቢሆንም፤ ተፈላጊው ነገር የሚያሳየው እንቅስቃሴ መሻሻሉ ነው።

አጥቂ - ጋብሪኤል የሱስ (ማንቸስተር ሲቲ)

Image copyright Getty Images

ማንቸስተር ሲቲ ሌላኛውን ሮናልዶ ያገኘ ይመስላል። እንቅስቃሴው የቀድሞውን የብራዚልና የሪያል ማድሪድ አጥቂ የሚመስል ሲሆን ለጎል ያለው ዓይንም ከሃገሩ ልጅ ጋር ያመሳስለዋል።

የ20 ዓመቱ ተጫዋች ድንቅ ችሎታውን ከማሳየቱም በላይ ሲቲ በአውሮፓ መድረክ በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል።

ሲቲዎች ሊጉን ከመምራታቸውም በላይ የሚያሳዩት ምርጥ እንቅስቃሴ በማንቸስተር ዩናይትዶች ዘንድ ብስጭት የሚፈጥር ነው።

አጥቂ - ትሮይ ዴንይ (ዋትፎርድ)

Image copyright PA

አርሴናል እንዴት ቪካሬጅ ሮድ ላይ ተሸነፈ?

ዴንይ አንዳንድ የአርሴናል ተጫዋቾች ጨዋታው ላይ አልነበሩም ይላል።

የማርኮ ሲልቫ የተጫዋች ቅያሬ፤ የዴንይ ምርጥ የጭንቅላት ኳስ እና የዳኛው ኒል ስዋብሪክ አስደንጋጭ የፍጹም ቅጣት ምት ውሳኔ ተደማምረው አርሴናልን ለሽንፈት ዳርገውታል።

ዳኛ እንደዚህ ዓይነት መጥፎ ውሳኔ ሲሰጥ አንደኛው ቡድን ዕድለኛ ይሆናል ማለት ነው።

ለደቂቃዎች ሜዳ ውስጥ የነበረው ዴንይም ኳሷን ከመረብ አሳርፏታል።

አጥቂ - ዊልፍሬድ ዛሃ (ክሪስታል ፓላስ)

Image copyright Rex Features

ከጉዳት የተመለሰው ዊልፍሬድ ዛሃ ምርጥ ጨዋታ ነበር ያሳየው። ክሪስታል ፓላሶች ባለፉት ቸዋታዎች የአይቮሪኮስቱን ተጫዋች ፍጥነት አጥተው ነበር።

ተከላካዩን ዴቪድ ሉዊዝን ሁለት ጊዜ በአስገራሚ ሁኔታ ከማለፉም በላይ ድንቅ እንቅስቃሴ ሲያደርግ አምሽቷል።

ፓላስ በተለይ ደግሞ ዛሃ ምርጥ ብቃት ላይ ሲሆን የትኛውንም ነገር ማሳካት ይችላል። ምርጥ ሜዳ እና ምርጥ ደጋፊዎች።