የሶሪያ ጦርነት፡ በአሜሪካ የሚደገፈው ጦር ራቃን ተቆጣጠርኩ አለ

ወታደር Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ራቃ ከአይ አስ ነጻ መውጣቷን የሚያረጋግጥ ይፋዊ እወጃ እየተጠበቀ ነው

በሶሪያ የሚገኘው በአሜሪካ የሚደገፈው ጦር የአይ ኤስ መቀመጫ የነበረችውን ራቃን መቆጣጠሩንና አሁን የቀሩት ጥቂት ታጣቂዎች ብቻ መሆናቸውን ገልጿል።

የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች አይ ኤስ የሞት ቅጣትን በይፋ ሲያስፈጽምበት የነበረውን የአል-ናይም አደባባይም ተቆጣጥረናል ብለዋል።

ድላቸውም በቅርብ ሰዓታት በይፋ እስኪታወጅ እየተጠባበቁ ነው።

ከ3000 በላይ የሚሆኑ ንጹኃንም ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ከአይ ኤስ ነጻ ሆነዋል።

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ጦሩ ለወራት ከተማዋን ከቦ የአይ ኤስ ታጣቂዎች እስኪወጡ እየተጠባበቀ ነበር

ራቃ አይ ኤስ ከአውሮፓውያኑ 2014 ጀምሮ ከተቆጣጣራቸው ትልልቅ ከተሞች አንዷ ነበረች።

አሁን ግን በከተማዋ ሆስፒታልና ስታዲየም ወደ ሃምሳ የሚጠጉ ታጣቂዎች ብቻ መቅረታቸው እየተነገረ ነው።

ወደ ራቃ የመግባት እድል የገጠመው የበቢሲ ጋዜጠኛም በወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለአየር ድብደባ፣ ያለቦምምብ ፍንዳታና ያለተኩስ እሩምታ እንዳገኛት ዘግቧል።

ይልቁንስ የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች በፈራራሱት መንገዶች እየተመላለሱ ነዋሪዎቹ በነጻነት ወጥተው ትኩስ ሾርባ እንዲጠጡ በድምጽ ማጉያ እየጋበዙ ነበር ብሏል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ