የሶማሊያ ጥቃት፡ በሞቃዲሾ ፍንዳታ የሞቱ 165 ሰዎች ማንነታቸው ሳይታወቅ ተቀበሩ

ፍንዳታ Image copyright AFP

በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ባለፈው ቅዳሜ በተከሰተው የቦምብ ፍንዳታ የሞቱ 165 ማንነታቸው ያልተለዩ ሰዎች ተቀበሩ።

በጥቃቱ ቢያንስ 276 ሰዎች ሲሞቱ ማንነታቸውን መለየት የተቻለው ግን የ111ዱን ብቻ ነው።

የቱርክ ወታደራዊ አውሮፕላኖም 40 ቁስለኞችን ለህክምና ወደ ቱርክ ወስዷል።

ማንነታቸው ከተለዩ ሟቾች መካከል በማግስቱ የምትመረቅ የህክምና ተማሪ ትገኝበታለች።

በምርቃት ስነ ስነስርዓቷ ለመገኘት ወደ ሞቃዲሾ የመጣው አባቷም እጣፈንታው ቀብሯ ላይ መድረስ ሆኗል።

Image copyright Anfa'a Abdullahi
አጭር የምስል መግለጫ ሩቅ አስባ በአጭሩ የተቀጨችው መርየም አብዱላሂ

እህቷ አንፋ ለቢቢሲ እንደተናገረችው መርየምን ጥቃቱ ከመፈጸሙ ከ 20 ደቂቃዎች በፈት አናግራት ነበር።

''በምትሰራበት ባናድር ሆስፒታል ሆና አንድ ማህደር እስኪመጣ እየተጠባበቀች እንደሆነና ተመልሳ እንደምትደውል ቃል ገብታልኝ ነበር' ብላለች።

በሞቃዲሾ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ከ270 በላይ ደርሷል

ሰዎች በሚበዙባት አካባቢ ፈንድቶ ሆቴሎችን፣ የመንግስት ቢሮዎችንና ምግብ ቤቶችን ላወደመው ለዚህ ጥቃት እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

ሆኖም ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዲላሂ ፋርማጆ አልሸባብን ተጠያቂ አድርገዋል።

አልሸባብ ከዚህ ቀደም ለሚፈጽማቸው ጥቃቶች ወዲያውኑ ነበር ኃላፊነቱን የሚወስደው፤ እስካሁን ግን የተሰማ ነገር የለም።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ