"ወንዙን እናመልከው ነበር፤ አሁን ግና ምንም ልናደርግበት አንፈቅድም"

በደለል እየተሸፈመነ ያለው ዓባይ

ይህ የዓባይ ወንዝን ተከትለን ከምንጩ ጣና ሃይቅ ወደ መዳረሻው ሜዲትራኒያን ባሕር የምናደርገው ጉዞ መጨረሻ ክፍል ነው።

• ዓባይ ከጣና ሃይቅ እስከ ታላቁ ህዳሴ ግድብ

ወንዙ ግብፅ ከተማ ዋና ከተማ ካይሮ ሲደርስ ሙሉ በሙሉ ቆሻሻ ይዞ ነው።

በሰሜናዊ ዴልታ የሚኖሩ ገበሬዎች ስለ ውሃ እጥረት ማማረር ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል። ዓባይ ወንዝ በመስኖ ምክንያት ንፁህ እንደሆነ መዝለቅ ባለመቻሉ።

የፖለቲካ ውጥረት

የግብፅ ውሃ ሃብት ሚንስቴር ሠራተኛ የሆኑት አሊ ሙኖፊ ሲናገሩ "ዓባይ (ናይል) ለእኛ ሁሉ ነገራችን ነው። የምንጠጣው የምንበላው እሱን ነው" ይላሉ። "አንድ ነገር ቢሆን ነገሮች እንዳልሆኑ ይሆናሉ" ሲሉ ያስረግጣሉ።

በዓባይ ዙሪያ የሚደረጉ ፖለቲካዊ መግለጫዎች በተለይ ደግሞ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ጉዳዩ ጠንከር ያለ አጅንዳ እንደያዘ ማሳያ ናቸው።

በአውሮፓውያኑ 2013 በቀድሞው የግብፅ አስተዳደር ስር ባለስልጣን የነበሩ አንድ ግለሠብ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በወታደራዊ ኃይል እንዲመታ ሃሳብ አስተላልፈው እንደነበረ የሚታወስ ነው። በሌላ በኩል አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ ለጉዳዩ ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ወደ መገባደጃው እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ወቅት የግብፅ ባለስልጣናት ከፈረንሳይ ረጅም ርቀት ተጓዥ የጦር መሣሪያዎችን ገዝተዋል። ተንታኞች ይህ የግብፅ እንቅስቃሴ በደቡብ አቅጣጫ ላለችው ኢትዮጵያ መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ሲሉ ይናገራሉ።

ወታደራዊ እርምጃ አማራጭ ነው ወይ ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ "ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛው ላይ ቀርቧል" ይላሉ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እና የቀድሞ የዓባይ ጉዳይ ተደራዳሪ አሕመድ አቡ ዘይድ።

ድንበር ተሻጋሪ ወንዦች የሚያመጧቸውን ግጭቶች ብዙ ጊዜ በሰላማዊ መንገድ የመፈታት ዕድላቸው የሰፋ ነው። ግብፅም በዓባይ ዙሪያ መሰል ሰላማዊ ሂደቶችን ልትከተል እንደምትችል ማሳያዎች አሉ።

ነገር ግን ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ የምታሳየው ጥልቅ ድብቅነት ለሂደቱ ማነቆ እንዳይሆን ያሰጋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ትልቅ አካል የሆነው የውሃ ቋትንም ለመሙላት ምን ያህል ጊዜ ሊወስድበት እንደሚችል አለመታወቁ ሌላው አጠራጣሪ ነገር ነው።

በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የቃላት ጦርነትም ቅርፅ አልባ ሆኗል።

ዓባይ ወደ ሜዲቴራኒያን

በሮዜታ አካባቢ ዓሳ ለሚያጠምዱ ሰዎች የዓባይ ወነዝ ነገር ተስፋ አስቆራጭ እየሆነባቸው ይገኛል። ምክንያቱም ውሃው በጣም ቆሻሻ አዘል ከመሆኑ የተነሳ ዓሳዎች በውስጡ ለመኖር አልተቻላቸውም።

ዓሳ አጥማጆቹ እንደሚናገሩት ወንዙ ውቅያኖሱን የሚቀላቀልበት አካባቢ እንኳን ሕይወት ያላቸውን ነገሮችን ማግኘት እጅግ ከባድ ነው።

"ወንዙን እናመልከው ነበር። አሁን ግና ምንም ልናደርግበት አንፈቅድም" ሲል አሳ አስጋሪው ካሚስ ካላ ይናገራል። "በተቻለ መጠን ከወንዙ መራቅን ነው የምንመርጠው" በማለትም ያክላል።

ሮዜታ አካባቢ ዓሳ የሚያጠምደው ሞሓመድ ሁለት ጊዜ ያክል ሜዲታሪያን ባህርን ለሚያቋርጡ ስደተኞች መንገድ ጠቁሟል። ሁለቱንም ጊዜ ከመያዝ ለትንሽ ነው ያመለጠው።

ከወንዝ ዓሳ አጥምዶ ራሱንና ቤተሰቡን የመመገቡ ነገር አዋጭ የሆነለት አይመሰልም። ለስደተኞች አቅጣጫ በመጠቆም የሚያገኘው ገቢም ከአሳ ማስገሩ እጅግ የላቀ ነው።

"እንደ አያቴ እና አባቴ ዓባይ ወንዝን ተጠግቼ ብኖር ደስ ባለኝ ነበር፤ ግን ነገሮች እየሰመረልኝ አይደለም" ይላል ሞሓመድ።

ተጨማሪ ፡ጣና ሐይቅ የተጋረጡበት ፈተናዎች

ክፍል 1 ፡በፅኑ የታመመው የዓባይ ወንዝ

ክፍል 2 ፡የህዝብ ብዛት መጨመርና የአካባቢ ብክለት ሌሎቹ የዓባይ ስጋቶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ