በካሊፎርንያ በ'ሄፒታይተስ ኤ' በሽታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 19 ደርሷል

ጎዳና ተዳዳሪ Image copyright Getty Images

በካሊፎርንያ የጤና አስቸኳይ ጊዜ በታወጀ ከአንድ ሳምንት በኋላ በ'ሄፒታይተስ ኤ' የሞቱ ሰዎች ቁጥር 19 ደርሷል።

ከ500 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ካለፈው ህዳር ጀምሮ በበሽታው ተይዘዋል።

ጉበትን የሚያጠቃው ይህ በሽታ የሚተላለፈው በግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲሁም የተበከሉ ምግቦችና ቁሶች ጋር ንክኪ ነው።

በአሜሪካ የ20 ዓመት ታሪክ በፍጥነት በመዛመት ሁለተኛው ነው።

በሳንዲያጎ ብቻ 500 ሰዎች ሲያዙ አውራ ጎዳናዎችን መድኃኒት መርጨትና የእጅ መታጠቢያ ማእከላትን ማዘጋጀት ጀምረዋል።

በሽታው የከፋው ደግሞ የንጽህና መጠበቂያና የቆሻሻ ማስወገጃ በሌላቸው የጎዳና ተዳዳሪዎች ላይ ነው።

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በሳንዲያጎ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ጊዜያዊ መጠለያ ተዘጋጅቶላቸዋል

በሳንዲያጎ ከ 5000 በላይ የሚሆኑ ቤት አልባ ሰዎች ይገኛሉ።

በሽታው በሌሎች ከተሞችም እየታየ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ጎዳና ተዳዳሪዎች ተከትበዋል።

ተያያዥ ርዕሶች