የሣምንቱ የአፍሪካ ምርጥ ምስሎች: ከጥቅምት 03-09 2010

በሳምንቱ ከአፍሪካና በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ አፍሪካዊያን የተሰባስቡ ምርጥ ፎቶግራፎች

Gabonese striker Pierre-Emerick Aubameyang Image copyright AFP

ጋቦናዊው ፒየር ኤምሪክ ኦባምያነግ በጀርመን አንደኛ ዲቪዚዮን የሚገኘው ቡድኑ ዶርትሙንድ በሜዳው አርኤል ላይፕዚግን በገጠመበት ጊዜ የማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሮ ደስታውን ሲገልፅ

Cost effective container flats Image copyright EPA

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ማቦኔንግ በተባለ አካባቢ ኮንቴይነሮችን በመደራረብ የተሰሩ ዝቅተኛ ወጪን የሚጠይቁ መኖሪያ ቤቶች

Liberians read from a 'Daily Talk' Image copyright EPA

የፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ውጤት ጋዜጣ ገዝተው ለማንበብና በሞባይል ኢንተርኔት ለመከታተል ያልቻሉ ላይቤሪያዊያን በአማካይ ስፍራ ላይ የተዘጋጀን የምርጫው ውጤት የሰፈረበት ጥቁር ሰሌዳን ሲያነቡ

Dancers perform Image copyright AFP

የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት ቀዳማዊ እመቤቶች የህፃናት የጉልበት ብዝበዛን ለማስቆም ዘመቻ ለማካሄድ በታቀደ ጉባኤ ላይ የቀረበ የዳንስ ትርኢት

A Congolese fashion model Image copyright AFP

ለትርኢት የምትዘጋጅን ሞዴል የሞባይል ስልክ መብራትን በመጠቀም ባለሙያዎች ፊቷን ሲያስውቡ

Traditional Moroccan knights Image copyright EPA

ከሞሮኮዋ ካዛብላንካ ከተማ በስተደቡብ በምትገኘው ኤል-ጃዲዳ የፈረሰኞች ትርኢት...

Traditional Moroccan knights fire Image copyright EPA

ፈረሰኞቹ በአንድ መስመር እየጋለቡ ወደ ሰማይ ሲተኩሱ

Diwali (Festival of Lights) Hindu festival celebrations Image copyright AFP

በደቡብ አፍሪካዋ ደርባን ዲዋሊ በተባለው የህንዶች ደማቅ በዓል ላይ የታደሙ ሴቶች ለዳንስ ትርኢት ሲዘጋጁ

Liberian students Image copyright EPA

በላይቤሪያ ዋና ከተማ ሞንሮቪያ ውስጥ የሴት ልጆች ቀን ሲከበር የፆታ እኩልነት መልዕክት ያለበት ኮፍያ ያደረጉ ታዳጊዎች

ፎቶዎች ከኤኤፍፒ፣ ከኢፒኤ፣ ከፒኤ እና ሮይተርስ የተገኙ ናቸው።