እነሆ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ አስራንድ ተጫዋቾች

Mesut Ozil (centre) provided a goal and assist during Arsenal's 5-2 win at Everton on Sunday Image copyright Rex Features

ካለፈው አርብ ጀምሮ ባሉ ሶስት ተከታታይ ቀናት ሃያ ክለቦችን እርስ በርስ ያገናኘው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 34 ጎሎችን ሲያስተናግድ አስደናቂ እና ያልተጠበቁ የተባሉ ውጤቶችን አሳይቶናል ይላል ጋርዝ ክሩክስ።

ሰባት ጎሎችን ባስተናገደው የጉዲሰን ፓርክ ጨዋታ ሜሱት ኦዚል እና አሌክሲስ ሳንቼዝ ደምቀው አምሽተዋል። በዌምብሌይ በተካሄደ ሌላ ፍልሚያ ደግሞ ሃሪ ኬይን ሊቨርፑል ላይ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ነገር ግን የዚህ ሳምንት አስደናቂ ትርኢት የነበረው ጆን ስሚዝ ሜዳ ላይ አሮን ሙይ እና ሎረንት ዲፖይትሬ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች ከ65 ዓመታት በኋላ ሃደርስፊልድ ማንቸስተር ዩናይትድ ያሸነፈበት ጨዋታ ነው።

መሰል ክስተቶችን ያስተናገደው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ አስራ አንድ ተጫዋቾችን እነሆ የሚለን ጋርዝ ክሩክስ ነው።

ግብ ጠባቂሁጎ ሎሪስ (ቶተንሃም)

Image copyright Rex Features

የሚገርም ግብ ጥበቃ! ኩቲንሆ ወደጎል የሰደዳትንና ምናልባትም ጎል ብትሆን ሊቨርፑልን ወደ ጨዋታው ልትመልስ የምትችል ኳስ ነበረች።

ነገር ግን ፈረንሳዊው ግብ ጠባቂ ሁጎ ሎሪስ በሚገርም ሁኔታ አድኗታል።

በጣም ድንቅ ብቃት ላይ የነበረው ሁጎ ሎሪስ እንዳሳየው ብቃት ጎል ሊቆጠርበት ባልተገባ ነበር።

ተከላካይ፡- ቶሚ ስሚዝ (ሃደርስፊልድ)

Image copyright Rex Features

ቶሚ ስሚዝ አንቶኒ ማርሺያል ከፈተነበት ደቂቃ ጀምሮ ማንቸስተር ዩናይትድ ምን እያደረጉ እንደሆነ ያወቁ አልመሰለኝም።

በማርሺያል በኩል ዩናይትድ እጅግ ደክሞ የታየውም በቶሚ ስሚዝ ብቃት ነበር።

ዩናይትዶች ነቅተው ወደጨዋታው መመለስ ሲጀምሩ ግን ነገሮች ቀላል አልነበሩም።

የአምበልነት ሚናውን በሚገባ የተወጣው ቶሚ ስሚዝ ለሃደርስፊልድ ማሸነፍ የጎላ ሚና መጫወቱም የማይካድ ነው።

ተከላካይ፡- ሌዊስ ዳንክ (ብራይተን)

Image copyright Rex Features

የብራይተኑ ሌዊስ ዳንክ በዚህ የውድድር ዘመን 15 ውጤታማ ኳሶችን በመመከት በሊጉ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ዳንክ በታችኛው ሊግ ያሳየውን ብቃት በፕሪሚየር ሊጉ ይደግመዋል የሚለው አጠራጣሪ ነበር። ዳንክ ግን ድንቅ ብቃቱን ማሳየቱን ቀጥሎበታል።

ብራይተን ዌስትሃምን በገዛ ሜዳው 3-0 በረመረመበት ጨዋታ የሌዊስ ዳንክ የመካለከል ብቃት ትልቅ ሚና ነበረው።

ብራይተን በፕሪሚየር ሊጉ መቆየት መቻል አለመቻሉ ለእኔ እስካሁን አሳማኝ ባይሆንም ሌዊስ ግን ለዚህ ብቃቱ እንዳለው በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ።

ተከላካይ፡- ሼን ዳፊ (ብራይተን)

Image copyright Rex Features

ዕለተ አርብ ከብራይተን በነበራቸው ፍልሚያ መዶሻዎቹ ዌስትሃሞች የሼን ዳፊን አጥር ሰብረው መግባት ተስናቸው አምሽተዋል።

አየርላንዳዊው ዳፊ ከቡድን አጋሩ ዳንክ ጋር በመሆን መዶሻዎቹ ምንም ዓይነት ኳስ ወደ ብራይተን መረብ እንዳይሰዱ አድርጓል።

አሁን የኔ ጥያቄ የክሪስ ሂዩተን ቡድን ይህን ድንቅ መካለከል ይዞ በሊጉ መዝልቅ ይችላል ወይ የሚለው ነው?

ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ ካገኘ ዳፊ በጣም ውድ እና ተፈላጊ ተከላካይ እንደሚሆን አልጠራጠርም።

አማካይ፦ ኬቪን ደብሩይን (ማንቸስተር ሲቲ)

Image copyright Rex Features

በወድድር ዘመኑ ካየኋቸው የሲቲ ጨዋታዎች ከበርንሌይ ጋር የነበረው ብዙም ማራኪ ያልነበረ ቢሆንም ደብሩይን ግን ምርጥ ብቃትን ማሳየቱን ቀጥሏል።

ደብሩይን ኳስ እግሩ ላይ ሲገባ በአደገኛ ሁኔታ ወደፊት እንደሚያሻግር እሙን ነው።

በጨዋታው ከታዩ ሶስት ጎሎች ሁለቱ የደብሩይን ውጤት መሆናቸውም ፍፁም የሚዘነጋ አይደለም።

አማካይ፦ አሮን ሙይ (ሃደርስፊልድ)

Image copyright Rex Features

አነስተኛ ግምት የተሰጠው ቡድን እንደ ማንቸስተር ካለ ትልቅ ቡድን ጋር ሲጫወት አሽንፋለሁ ብሎ መግባት ትልቅ ወኔ የሚጠይቅ ገዱይ ነው።

ሃደርስፊልድም ያደረገው ይሄንን ነው። በቀድሞው ማነችስተር ሲቲ ተጫዋች አሮን ሙይ በመታገዝ ሃደርስፊልድ ዩናይትድን በልጦ መገኘት ችሏል።

ሙይ በዚህ ብቃቱ ከቀጠለ በጥር ወር የዝውውር መስኮት የክለቦችን ቀልብ መሳቡ የማይቀር ነው።

አማካይ፦ ሜሱት ኦዚል (አርሴናል)

Image copyright Rex Features

ሜሱት ኦዚል በአውሮፓውያኑ 2013 አርሴናልን ከተቀላቀለ ወዲህ 43ኛ ለጎል የሚሆን ኳስ በማቀበል ታሪክ ሰርቷል።

ኦዚል፣ ላካዜት እና ሳንቼዝ አንድ ላይ ሲሰለፉ አርሴናል ከኤቨርተን ጋር እንደነበረው ዓይነት ጥሩ ብቃት ማሳየት የሚችል ከሆነ ቬንገር እነዚህን ተጫዋቾች ማጣት የለባቸውም።

ኦዚል ጉዲሰን ፓርክ ላይ እጅግ ድንቅ ነበር። ተቺዎቹንም አፍ ማዘጋት ችሏል።

አማካይ፦ ሪያድ ማህሬዝ (ሌይስተር ሲቲ)

Image copyright Rex Features

ማህሬዝ ከስዋንሲ ጋር በነበረው ጨዋታ ያሳየው ድንቅ ብቃት አስገራሚ ነበር።

ሌይስተሮች አሰልጣኝ ባባረሩ ማግስት የሚያሳዩት ብቃት እጅግ አነጋጋሪ ነው። ራኒየሪም ሆኑ ሼክስፒር ከክለቡ በተሰናበቱ ማግስት ሌይስተሮች ያደረጓቸውን ጨወታዎች ማሸነፍ ችለዋል።

የክለቡ ባለቤቶች አሁን ላይ ቋሚ አሰልጣኝ ቀጥረው ዘላቂ ውጤት ላይ ማተኮር እንዳለባቸው ይሰማኛል።

አጥቂ፦ ግሌን መሪ (ብራይተን)

Image copyright Rex Features

ለብራይትን በሊጉ መቆየት ጉዳይ ላነሳሁት ጥያቄ አንዱ ምላሽ የግሌን መሪ ብቃት ነው።

መሪ ከዌስትሃም ጋር በነበረው ጨዋታ አስገራሚ ነገር ማሳየት ችሏል።

ብራይተን ተቀያሪ ተጫዋቾች እንደሚያስፈልጉት ምንም ጥርጥር የለውም። ይህ ካልሆነ ጥር ላይ ብራይተኖች ትንፋሽ እንደሚያጥራቸው ግልፅ ነው።

አጥቂ፦ ሰርጂዎ አጉዌሮ (ኣንቸስተር ሲቲ)

Image copyright Rex Features

በርናንዶ ሲልቫ በበርንሌይ 16 ከ50 ክልል ውስጥ ተጠልፎ ወድቆ ፍፁም ቅጣት ምት ያገኘበትን ክስተት መልሼ መላልሼ ብመለከተውም ዳኛው ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን አለመወሰናቸውን ማረጋገጥ አልቻልኩም ነበር።

መጨረሻ ላይ ግን መሃል ዳኛው ትክክለኛ ውሳኔ መወሰናቸውን አምኛለሁ።

ሆኖም በጨዋታው ድንቅ ብቃቱን ከማሳየቱም አልፎ የሲቲ የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ታሪክ መፃፍ ችሏል።

አጥቂ፦ ሃሪ ኬን (ቶተንሃም)

Image copyright Rex Features

ከጨዋታ ጨዋታ ሃሪ ኬን እያሳየ ያለው ብቃት እየጨመረ መጥቷል።

በሳንቲያጎ በርናቢዩ የነበረው ብቃትም አንዱ ማሳያ ነበር። ከሊቨርፑልም ጋር በነበረው ፍልሚያ ኬን አስፈላጊነቱን አስመስክሯል።

ቶተንሃም ሊቨርፑልን ባሸነፈበት ጨዋታ ሃሪ ኬን ሁለት ኳሶችን ወደጎል በመቀየር ጥሩ ምሽት አሳልፏል።