ዢ ከማኦ በኋላ ከፍተኛው ተፅእኖ ፈጣሪ መሪ ሆነዋል

ዢ ዢንፒንግ Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ዢ ዢንፒንግ

ዢ ዢንፒንግ ከማኦ ዜዱንግ በኋላ የቻይና ከፍተኛ ተፅእኖ ፈጣሪ መሪ መሆን ችለዋል።

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የዢ ዢንፒንግን ርዕዮተ ዓለም በህግ-መንግሥቱ ውስጥ እንዲሰርፅ ድምፅ ሰጥቷል፤ ይህም ዢን ከኮሚኒስት ፓርቲው መስራች ከማኦ ዜዱንግ እኩል ቦታ ላይ ያስቀምጣቸዋል።

ዢ እአአ 2012 ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ተፅእኖ ፈጣሪነታቸው እጅጉን ጨምሯል።

ከ2000 በላይ የሚሆኑ ልዑካን የቻይናን የወደፊት እጣ ፈንታ በሚወስነው ዝግ ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት ኮንግረሱ ሲጀምር ዢ ዢንፒንግ ለመጀመሪያ ጊዜ ''ኅብረተሰባዊነት በአዳዲስ የቻይና መገለጫዎች'' የተሰኘውን ፍልስፍናቸውን ለሦስት ሰዓታት ባደረጉት ንግግር አስተዋውቀው ነበር።

የቢቢሲዋ የቻይና አርታኢ ኬሪ ግሬሲ እንደምትለው የዢ ዢንፒንግ ርዕዮተ ዓለም በህግ-መንግሥቱ ውስጥ እንዲሰርፅ መደረጉ የዢ ተቀናቃኞች በፓርቲውን አመራር ላይ ተፅእኖ ማሳደር እሰካልቻሉ ድረስ ጠንካራውን ዢ መጋፈጥ ይከብዳቸዋል።

ከዚህ በፊት የነበሩ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ መሪዎች 'ርዕዮተ ዓለም' በፓርቲው ህገ-መንግሥት ውስጥ ማካተት ቢችሉም መስራቹ ማኦ ዜዱንግ ብቻ ነበሩ በህግ-መንግሥቱ ውሰጥ የማኦ 'አስተምህሮ' ተብሎ የተቀመጠው።

Image copyright Getty Images

ተያያዥ ርዕሶች