ሲዘዋወር የተያዘ የዝሆን ጥርስ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ

ከዝሆን ጥርስ የተሰሩ ቅርፆች Image copyright Getty Images

በአፍሪካ ይፈፀም የነበረው የዝሆኖች አደን በተከታታይ ለአምስት ዓመታት መቀነስ ቢያሳይም ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ ሲዘዋወር የተያዘው የዝሆን ጥርስ መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደደረሰ አንድ ሪፖርት አመለከተ።

ለጥፋት የተጋለጡ ዝርያዎችን ደህንነትና ንግድ የሚከታተለው ዓለም አቀፍ ተቋም ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው 40ሺህ ኪሎ የሚመዝን የዝሆን ጥርስ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተይዟል።.

በበርካታ ቦታዎች የዝሆን አደን እየቀነሰ ቢሆንም ባለፉት አስር ዓመታት 111ሺህ የአፍሪካ ዝሆኖች ለጥርሳቸው ሲባል ተገድለዋል።

ጥናቱ የተያዘውን የዝሆን ጥርስ በተመለከተ የቀረበውን ግኝት በመልካምነቱ ቢጠቅሰውም ማስጠንቀቂያም መያዙን አመልክቷል።

''በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ያለው ጥረት አውንታዊ ውጤት እያሳየ ቢሆንም የሚፈለገው ደረጃ ላይ ግን አልደረስንም'' ሲሉ የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ ጆን ስካንለን ተናግረዋል።

ሪፖርቱ እንዳመለከተው በቁጥጥር ስር የዋለው ከፍተኛ መጠን ያለው የዝሆን ጥርስ ጠንካራ የህግ ማስከበር ሥራ በመሰራቱና የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር በመቻሉ ነው ይላል።

ዋና ፀሃፊው እንዳሉት ባለፉት አስር ዓመታት በዝሆኖች አደን ክፉኛ ከተጠቃው የምሥፍቅ አፍሪካ አካባቢ መልካም ዜና አለ።

''ከ2011 በኋላ በዝሆኖች ህገ-ወጥ አደን ላይ ከፍ ያለ መቀነስ የታ ሲሆን በ2016 በተደረገው ጥናት የዝሆኖች አጠቃላይ የአደን ሁኔታ ከ2008 በፊት ወደ ነበረው ዝቅተኛ መጠን የመመለስ አዝማሚያን አሳይቷል'' ይላሉ።

በቦትስዋና፣ በደቡብ አፍሪካ እና በናሚቢያ ያሉ ዝሆኖች መልካም ሁኔታ ላይ ቢገኙም በመካከለኛው አፍሪካ ግን ባለፉት አስር ዓመታት ''ህገ-ወጥ አደን እየጨመረ በመቀጠሉ የዝሆኖች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።

ተያያዥ ርዕሶች