የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 3

በቦኮሃራም የታገቱት ልጃገረዶች ከብዙ ስቃይ በኋላ ሳምቢሳ ደን ደርሰዋል። ከዚያስ ምን ገጠማቸው? የልጃገረዶቹ ማስታወሻ ምንባብ ሶስተኛ ክፍል ይቀጥላል...

የእገታውን ማስታወሻ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ክፍሎች ለማግኘት ፦

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 1

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 2

የክፋት ተንኮሎች

ታጣቂዎቹ የታገቱት ሴቶች ላይ የተለያዩ የክፋት ዘዴዎችን በመጠቀም ያስፈራሯቸው ነበር።

ከማስፈራሪያዎቹ መካከል ምንም ውሸት ቢሆንም ወላጆቻቸው በቦኮ ሃራም ቁጥጥር ሥር እንደሆኑ ይነግሯቸው ነበር።

በአንድ ወቅት ክርስቲያኖቹን ከሙስሊም ሴቶች ለይተው ወደ ኃይማኖታቸውን ወደ እስልምና ካልቀየሩ በቤንዚን እንደሚያቃጥሏቸው ነገሯቸው።

"ወደኛ መጡና 'ሙስሊም ለሆናችሁ የጸሎት ሰዓት ደርሷል' አሉ። ከጸለዩ በኃላ እዲህ አሉን 'ሙስሊም የሆናችሁ በአንድ በኩል ክርስቲያ ደግሞ በዛኛው ማዶ ሁኑ'

"ከዚያ መኪናው ውስጥ ጄሪካን ስናይ ቤንዚን መሰለን እነሱም 'ስንቶቻችሁ ወደ እስልምና ትቀየራላችሁ?' አሉን። ብዙዎ በፍራቻ ምክንያት ከመካከላችን ተነስተው ወደ ውስጥ ገቡ... እነሱም መልሰው 'የቀራችሁት በሙሉ መሞት ስላማራችሁ ነው ሙስሊም መሆን የማትፈልጉት? እናቃጥላችኋለን' አሉንና ቤንዚን የያዘ መስሎን የነበረውን ጄሪካን ሰጡን። ቤንዚን ግን አልነበረም ... ዉሃ ነበር።''