የሌሉት 350 ሚሊዮን ሠዎች

Unesco annual report Image copyright Getty Images

"በዓለም አቀፍ ደረጃ" የሚል ሪፖርት ይፋ በሆነ ቁጥር፤ በሚሊዮን ወይንም በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሠዎች የሚል መረጃ አብሮ ይፋ መደረጉ የተለመደ ነው።

መገናኛ ብዙሃን በዓለም ላይ ላይ የተከሰተን ትልቅ ችግር እና አደጋ በሚዘግቡበት ወቅት ቁጥሩን አግዝፈው ስለሚያስቀምጡ ዜናው መልዕክቱን ያጣል።

ትክክለኛውን መረጃም ሳያስቀምጡ ቀርተው ሊሆን ይችላል።

ምክንያቱም እንደዓመታዊው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባሕል ተቋም (ዩኔስኮ) ሪፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ የትምህርት ተደራሽነት ቁጥር በ 350 ሚሊዮን ልዩነት ያለው ሆኗል።

ይህ ልዩነት ትንሽ አይደለም። የእንግሊዝ፣ የጀርመን፣ የፈረንሳይ፣ የጣሊያንና የስፔን አጠቃላይ የህዝብ ቁጥርን የሚያክል ነው።

ያልተመዘገቡ እና የማይታዩ

"የማይታዩት" ሠዎች "የደሃ ደሃዎች" በሚል የሚገለጹ ናቸው። እነዚህ ቤተሰቦች በማይመች አካባቢ በመኖራቸው ምክንያት የህዝብ ቆጠራና እና የመንግሥት አስተዳደር ያልደረሳቸው ናቸው።

እነዚህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እና ያልተመዘገቡ ሰዎች በታዳጊ ሃገራት፣በህገወጥነት እና ሳይመዘገቡ ደግሞ በስደተኝነት ይኖራሉ።

የዩኔስኮ ሪፖርት እንደሚገልጸው ቤት ለቤት ጥናት፣ ቆጠራ እና የልደትና የሞት ምዝገባ መደበኛ ለሆነው የመረጃ አሰባበሰብ ቢጠቅምም ትክክለኛ ውጤት የሚሰጠው በተደራጀ፣ በሚታይና አገልግሎት በተዳረሰባቸው አካባቢዎች ነው።

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ዓለም አቀፍ አሃዞች ምን ያህል ትክክለኛ ናቸው?

በዚህ ምክንያትም በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በመረጃ ሰብሳቢዎች የማይመዘገቡ ይሆናል።

የጎዳና ተዳዳሪ ልጆችም ትምህርት ቤት ካልገቡ ልጆች ጋር አብረው አልተቆጠሩም።

መረጃው ካላካተታቸው ጋርም አብረው አልተደመሩም። ቤት የሌላቸውና ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚኖሩ ሰዎች መረጃዎችን ከቤት ወደ ቤት በመሄድ በሚሰበበስቡ ሰዎችም አልተመዘገቡም።

የፖለቲካ ግጭትን ተከትሎ ድንበር እንዲሻገሩ የተደረጉ ስደተኞች መረጃም ስለማይታወቅ አልተቆጠሩም።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲ በታዳጊ ሃገራት ከቤት ወደ ቤት በተደረገ መረጃ መሰብሰብ ሥራ 250 ሚሊዮን ሰዎች እንዳልተቆጠሩ ግምቱን አስቀምጧል።

በበለጸጉት ሃገራት በህገወጥ መንገድ የሚኖሩትን ጨምሮ 100 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ መረጃ ከሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ውጭ ናቸው ይላል።

ተጠያቂነት

የዘንድሮው የትምህርት ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ትኩረቱን በተጠያቂነት ላይ አድርጓል።

ሆኖም የዩኔስኮ ጥናት እንደሚያሳው መንግሥታት የትምህርት ተደራሽነት ባለማሳደጋቸው ሊጠየቁ የሚገባው ድጋፍ በሚፈልጉት ሰዎች ብዛት ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ መሃይምነትን ለመቀነስ እና የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋፋት የተቀመጠው ግብ አንዳንዶችን ያላካተተ ነው።

ይህ በብሄራዊ መዝገብ ውስጥ ያልተካተቱ ሰዎችን ጉዳይ ማን ይከታተለዋል የሚል ጥያቄን ይጭራል ይላል ዩኔስኮ።

ይህን መሰሉ የመረጃ ልዩነት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሃዝ ላይም ይስተዋላል።

የትምህርት ዕድል ያላገኙ ህጻናትን የሚገልጸው ዓመታዊው ሪፖርቱ፤ መረጃ ለመሰብሰብ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎች ያሉትንም ያካትታል በማለት የዩኔስኮ ሪፖርት ያስረዳል።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ቢገቡም አሁንም 264 ሚሊዮን የሚሆኑት ዕድሉን አላገኙም

ከትምህርት ስርጭት አለመመጣጠን እና ትምህርት ላይ ከሚደረገው የገንዘብ ፍሰት አንጻር ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩት እና "የማይታዩት" አለመካተታቸውን ዩኔስኮ ይገልጸል።

ትምህርት ቤት አለመግባት

በዚህ ዓመት ይፋ የሆነ አዲስ ሪፖርት እንደሚገልጸው 264 ሚሊዮን ወጣቶች የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አላገኙም።

የትምህርት ዘርፉ ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመት የሚደረግለት ፋይናንስ ድጋፍ መቀነሱን ሪፖርቱ ገልጾ ስጋቱን አስቀምጧል።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ቤት አልባ እና ስደተኛ ሰዎች ከይፋዊ ቆተራ ውጭ ናቸው

የቀድሞ ትምህርት ሚንስቴሮች ቡድን የሆነው አትላንቲስ ግሩፕ ለትምህርት የሚደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ሊሆን ይገባል ብሏል።

ባለፈው ወር ሌላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት እንደገለጸው የትምህርት ተደራሽነትን ከማስፋፋት አንጻር ባለፉት አስር ዓመታት የነበረው ለውጥ ወደ ዜሮ የተጠጋ ነበር።

ሌላ የድርጅቱ ሪፖርት ደግሞ 600 ሚሊዮን ወጣቶች ትምህርት ቤት ቢገቡም መሠረታዊ ዕውቀት አልገበዩም ብሏል።