የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 5

በቦኮሃራም የታገቱት ተማሪዎች እየተደፈሩ ነው መባሉን የሰማው መሪያቸው አቡበከር ሼኮ በተቀዳ መልእክት ''እኛ ያመጣናችሁ የፈጣሪን ትምህርት ልናስተምራችሁ ነው'' የሚል መልእክት አስተላልፎላቸዋል ። ከዚያስ?

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 1

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 2

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 3

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 4

Image copyright AFP

5) የታጣቂዎችን ፍላጎት ላለማነሳሳት ሂጃብ መልበስ

ታጣቂዎቹ ምንጊዜም ቢሆን ሴቶቹ ፍላጎታቸውን እንዳይፈታተኑ ይጠይቋቸው ነበር ፤ እናም ሰውነታቸውን በሂጃብ እንዲሸፍኑ ይነግሯቸዋል።

'' ቁርዓን ከፍቶ ማንበብ ጀመረ፤ ከዚያም ከአንድ ቦታ ይህን አነበበልን 'ለጂሃድ ውጊያ የታያዘ ሰው ሁሉ የራሳችሁ ነው፤ በዛ ሰው ላይ የፈለጋችሁትን ነገር ሁሉ ማድረግ ትችላላችሁ'... ሆኖም እነሱ ሰውነታችንን በማየት በእኛ ላይ ኃጢዓት እንዳይሰሩ ወይም ሌላ ክፉ ነገር እንዳይፈጽሙ በማሰብ ሂጃብ ሰጡን''

የታጋቾቹ ማስታወሻ መገለጡን ይቀጥላል...