የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 4

እንዲቃጠሉ ተፈርዶባቸው የነበሩት በቦኮሃራም የታገቱት ልጃገረዶች ተሰጥቷቸው የነበረው ጄሪካን ቤንዚን ሳይሆን ዉሃ መሞላቱን ደርሰውበታል ። ከዚያ ...

የእገታውን ማስታወሻ የመጀመሪያዎቹን ሶስት ክፍሎች ለማግኘት ፦

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 1

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 2

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 3

በሴቶኡ መደፈር ጥያቄ ላይ የተነሰ የታጣቂዎቹ ቁጣ

ከዚህ በፊት ቃላቸውን የቺቦክ ትምህርት ቤት ታጋች ልጃገረዶች ሲሰጡ አልፎ አልፎ የጋብቻ ጥያቄዎች ቢቀርቡላቸውም እንኳን ወሲባዊ ጥቃትም ሆነ ያለፍላጎታቸው እዲያገቡ እንዳልተደረጉ ተናግረዋል።

አጭር የምስል መግለጫ ልጃገረዶቹ ማስታዎሻዎቻቸውን በመቅበር ወይ በውስጥ ሱሪያቸው በመወሸቅ ይደብቋቸው ነብር

እነዚህ ማስታወሻዎችም ልጃገረዶቹ እንደተደፈሩ ተደርጎ በተለያዩ ሚድያዎች መወራቱ ታጣቂዎቹን እሳት ለብሰው እንዲጎርሱ እንዳደረጋቸው ይጠቅሳሉ። የታጣቂዎቹ አለቃ የሆነው አቡበካር ሼኮ በተደጋጋሚ ንዴቱን ግልጽ አድርጓል እሱም በመጀመሪያ በተቀዳ መልዕክት ለልጃገረዶቹ አስተላልፏል።

"ከዚያም በማታ አሰባሰቡንና የተቀዳ ካሴት አብርተው ይሰብኩልን ጀመር። ካሴቱ ከአለቃቸው ከአቡከር ሼኮ መሆኑንም ገለጹልን... እሱም የፈጣሪን መንገድ ለማስተማር ብናግታችሁ ወላጆቻችሁ፣ ትምህርት ቤታችሁና መንግስታቸሁ እንደደፈርናቸኹና መጥፎ ነገር አድርገናችዃል በማለት እያለቃቀሱ ነው። እኛ ግን የአላህን የአላህን መንገድ ልናስተምራችሁ ነው ያመጣናችሁ ። "

ተያያዥ ርዕሶች