ባርናቢ ጆይስ፡ የአውስትራሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት ውድቅ ተደረገ

የአውስትራሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ባርናቤይ ጆይስን ሹመት ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ

የአውስትራሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ባርናቢ ጆይስ እና ሌሎች አራት ፖለቲከኞች የሁለት ሃገራት ዜግነት አላቸው ብሎ ፍርድ ቤት ሹመታቸውን ውድቅ አደረገ።

ይህ የአውስትራሊያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ፖለቲከኞች ስልጣን እና ሃላፊነታቸውን ያሳጣቸዋል።

የአውስትራሊያ እና የኒውዚላንድ ዜግነት ያላቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለታችኛው ምክር ቤት አባልነት እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ካስተላለፈ በኋላ ''ውሳኔ አከብራለሁ'' ብለዋል።

የተቀሩት አራት ፖለቲከኞች ለምክር ቤት አባልነት ነበር የተመረጡት።

ጥምር ዜግነት ያላቸው ፖለቲከኞች ጉዳይ ካለፈው ዓመት ማብቂያ ጀምሮ የአውስትራሊያን ፖለቲካ ሲያነጋግር የቆየ ሲሆን በርካታ የምክር ቤት አባላት ስለያዙት ዜግነት ማብራሪያ እንዲሰጡ አድርጓቸዋል።

ተያያዥ ርዕሶች