የአፍሪካ ሳምንት በተመረጡ ፎቶዎች

Image copyright AFP

የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ የአልጀሪያውን ዩኤስኤም አልጀርን አሸንፎ ለካፍ ፍፃሜ ጨዋታ ማለፉን አስመልክቶ የካዛብላንካ መሀመድ አራተኛ ስታዲየምን በቀይ መብራት በማጥለቅለቅ ደስታቸውን ሲገልፁ።

Image copyright AFP

በሌጎስ በተደረገው የሌጎስ የፋሽን ዲዛይን ሳምንት አመዴ የተባለው ዲዛይነር የናይጀሪያን እንዲሁም የአፍሪካ ፋሽን ኢንዱስትሪን የሚያስተዋውቁ ስራዎቹን አቅርቧል።

Image copyright Reuters

ባለፈው አርብ በተከበረው የጀግኖች ቀን (የማሹጃ ቀን) ሁለት ወንዶች ለኬንያ ሰላምን በመመኘት ፎቶ ሲነሱ።

Image copyright AFP

ግጭቶችና ጭንቀት በተሞላበት የኬንያ ድጋሚ ምርጫ ላይ ከምርጫው በፊት የሚቃጠል እንጨት የያዘ ሰው በኪቤራ ተቃውሞዉን ሲገልፅ።

Image copyright Reuters

በምርጫው ቀን ሐሙስ የበለጠ ግጭቶች ተባብሰው ነበር። በኪቤራም ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር ሲጋጩ ይህ ሰው ራቅ ብሎ በቤቱ መስኮት የሚሆነውን ይመለከታል።

Image copyright AFP

የኬንያ ሌጊዮ ማሪያ ቤተ-ክርስቲያን አባላትም ከዚህ አላመለጡም በምርጫው ቀን የአስለቃሽ ጋዝ ተረጭቶባቸዋል።

Image copyright Reuters

በሊቢያ ሚስራታ ከተማ አፍሪካዊያን ስደተኞች መንገድ ዳር ቁጭ ብለው ስራ እየጠበቁ።

Image copyright Reuters

በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር በጋምቤላ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ንጉየልን ባለፈው ማክሰኞ በጎበኙበት ወቅት ከደቡብ ሱዳን የመጣች ስደተኛ ትታያለች።

Image copyright EPA

በለንደን "የማንዴላ ጉዞ" ዝግጅት ላይ የኔልሰን ማንዴላ ባለቤት ግራሻ ማሼል፣ የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ፀሐፊ ኮፊ አናንና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።

Image copyright Reuters

ተአምራዊ በሚመስል መልኩ እንግሊዛዊው ቶም ሞርጋን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በፊኛ በመታገዝ በወንበር 25 ኪ.ሜ ወደላይ በሯል።

Image copyright EPA

እንዲሁም ደቡብ አፍሪካዊው ማይክ ሼልባች በባህር ማዕበል ውስጥ ሲቀዝፍ

ምስሎቹ የተገኙት ከ ኤኤፍፒ፣ ኢፒኤ፣ ፒኤና ሮይተርስ ነው።

በቢቢሲ ዙሪያ