የታገቱ ማስታወሻዎች ፡ ክፍል 6

የቺቦክ ልጃገረድ Image copyright Getty Images

6) የጋብቻ ጥያቄዎች

የእገታውን ማስታወሻ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ክፍሎች ለማግኘት ፦

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 2

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 3

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 4

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 5

ከታጣቂዎቹ የሚቀርቡት የጋብቻ ጥያቄዎች የሚደጋገሙና የሚያስገድዱ ነበሩ።

"አንደኛዋ ልጅ ዕቃ ፈልጋ ወደ ክፍል ስትገባ ማላም አህመድ የተሰኘው አንደኛው ታጣቂተከትሏት ገብቶ ስለጋብቻ ጠይቋት እምቢ አለችው። መልሶ ግን "ስለ ጋብቻ የራስሽ ውሳኔ ምንድን ነው? አላት"

"እሷበድጋሚ እምቢ አለችው። 'በቺቦክ ማርበት ከነበረ የሴቶች የመንግሥት ትምህርት ቤት ወደ ሳምቢሳ አመጣችኹኝ አሁን ደግሞ ስለ ጋብቻ ትጠይቁኛላችሁ' አለች። እዴት ልታገባ ትችላለች በዚያ ላይ እናቷም አባቷም ሆነ አክሰቶቿና ጓደኞቿ አያውቁም። ዚያ አላገባም ብትልና ባለችበት አምላኳን ብቻዋን ብታመልክ ጥሩ አይደለም ወይ ብላ ጠየቀችው። እሱም "መጥፎ ነው" ብሎ መለሰላት።"

አንዳንዶች ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ ግፊት ተደርጎባቸዋል።

"ሰዎቹ በሁለት ሃይሉክስ መኪኖች ሲመጡ አይተናቸዋል። እደመጡም ከመካከላችን ማግባት የሚፈልጉ ካሉ ጠየቁ። ከዚያም እስልምናን የተቀበልነው ግድ ማግባት እነዳለብን ነገሩን በተለይ ሃይማኖቱን በሙሉ ልብ የተቀበልን ከሆነ። ምላሽም እንድንሰጣቸውም ግማሽ ሰዓት ጠበቁን። ከዚያ አንድ ሙሉ ሰዓት ጠበን ማንም መልስ አልሰጣቸውም። "

ናዖሚ አዳሙ እንደነገረችኝ ከሆነ ለማግባት ፈቃደኛ ያልሆኑትን እንደ ባሪያ ነበር የሚመለከቷቸው። "በየቀኑ ይደበድቡን ነበር፤ እንድናገባቸውም ይጠይቁንና እምቢ ካልን ይደበድቡን ነበር። ልብስ እናጥብ ነበር፣ ዉሃ ከወንዝ እንቀዳለን፣ ለሚስቶቻቸው ደግሞ ሁሉን ነገር እናደርግ ነበር። ባሪያዎቻቸው ነበርን።"

ተያያዥ ርዕሶች