የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 8

ልጃቸው የታገተችባቸው እናት ራሳቸውን ይዘው ሲያለቅሱ

የፎቶው ባለመብት, STRINGER

አምልጠው የነበሩት ልጃገረዶች በአቅራቢያቸው ወዳሉ ነዋሪዎች ቢሄዱም ሰዎቹ መልሰው ለቦኮ ሃራም አስረክበዋቸዋል።

የእገታውን ማስታወሻ የቀድሞ ክፍሎችን ለማግኘት ፦

የወቀሳው ጫወታ

ከልጃገረዶቹ ማንም ሳይቀር ሁሉም እምነታቸውን ወደ እስልምና ለመቀየር ከተስማሙ ወደ ቤት ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀል እንደሚችሉ ተነግሯቸው ነበር።

እናም በዚህ ኃሳብ የተስማሙት ልጃገረዶች እምቢታን መርጠው እገታውን ያስቀጠሉትን ልጃገረዶችን ተጠያቂ ያደርጉ ነበር።

"እስልምናን የማይቀበሉት 'እንደ በግ፣ላምና ፍየል የሚቆጠሩ ናቸው' በሚል እንደሚገድሏቸው ይዝቱ ነበር። ከዚያም ከታጣቂዎቹ አንዱ የሆነው ማላም አባ እስልምናን ያልተቀበሉት በአንድ በኩል እንዲቆሙ ተናገረ።ለመቀበል ከተስማሙት ጋር እንዳይቀላቀሉም አዘዘ። 'ለእነርሱ ሌላ ቦታ ይዘጋጅላቸዋል' ቢልም ሌላኛው ደግሞ የእርሱን ሳብ በመቃወም አንድ ላይ መቆየት እንዳለብን ተናገረ። ከአንድ ሳምንት በኋላ ኃይማኖታችንን ለመቀየር ያልተስማማነው 'ወደቤታችን ከመሄድ እየገደብን ያለነው እኛው ራሳችን ነን' አልን''

ከዚያስ ምን ሊፈጠር ይችላል? ነገ እንመለስበታለን።