የታገቱ ማስታወሻዎች ፡ ክፍል 7

የታገዱትን ልጃገረዶች ለማስመለስ የተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ Image copyright AFP

7) አምልጠው የነበሩትን ልጃገረዶች በአቅራቢያቸው ያሉ ነዋሪዎች መልሰው ለቦኮ ሃራም አስረከቧቸው።

የእገታውን ማስታወሻ የመጀመሪያዎቹን ክፍሎች ለማግኘት ፦

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 2

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 3

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 4

የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 5

የታገቱ ማስታወሻዎች ፡ ክፍል 6

'ሴት ልጆቻችንን መልሱ' [ብሪንግ ባክ አወር ገርልስ] የተሰኘው በዓለም ዙሪያ የተደረገው እንደ ሚሼል ኦባማና ሌሎችንም ታዋቂ ሰዎችን ያሳተፈ እንቅስቃሴ ቢደረግም በደኑ አካባቢ የነበሩ ነዋሪዎች ግን ልጃገረዶቹን በመመለስ ጣልቃ መግባት ካለመፈለጋቸውም በላይ ጠፍተው ያገኟቸውን መልሰው ለቦኮ ሃራም አስረክበዋል።

"አንዳንድ ሴቶች ሮጡ፤ ለማምለጥ ቢሞክሩም እንኳን ሊሳካላቸው አልቻሉም። አንዳንድ ሰዎችም አሰሯቸው።የተያዙበት መንገድ ደግሞ አምልጠው በአቅራቢያ ወደነበረ ሱቅ ውሃና ብስኩት ሲለምኑ ነው። 'ማን ናችሁ ከየት ነው የመጣችሁት? 'ብለው ሲጠይቋቸው በቦኮ ሃራም ከመንግሥት ሴቶች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ታግተው እንደነበር ነገሯቸው።

ሰዎቹ ግን 'እነዚህ የሼኮ ልጆች አይደሉ እንዴ? ' ብለው ተጠያየቁ።

"ከዚያም ምግብና የሚተኙበት ቦታ ሰጧቸውና በማግስቱ ለቦኮ ሃራም አስረከቧቸው። በምሽት ነበር ወደ ሳምቢሳ ያመጧቸው... እነሱም አንገታቸውን እንደሚቆርጡ አስፈራሯቸውና ገረፏቸው።"

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ