"አንዱ በጥይት መታው። ጭንቅላቱ ነበር የተመታው"

በሰሜን ናይጄሪያ ከቦኮ ሃራም ጋር በሚደረገው ጦርነት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ብዙዎች በናይጄሪያ ጦር ቁጥጥር ስር ወደምትገኘው ማይዱጉሪ ከተማ ቢሰሹም የጠበቃቸው ወሲባዊ ጥቃት ነው ።