የታገቱ ማስታወሻ ደብተሮች ፡ ክፍል 9

የልጃገረዶቹ ፊት ደብዘዝ ተደርጓል ምክንያቱም የተወሰኑት የቦኮ ሃራም ታጣቂዎችን በማግባታቸው ከተፈቱ በኃላ መገለል ደርሶባቸዋል

የፎቶው ባለመብት, AFP/BOKO HARAM

የምስሉ መግለጫ,

የልጃገረዶቹ ፊት ደብዘዝ ተደርጓል ምክንያቱም የተወሰኑት የቦኮ ሃራም ታጣቂዎችን በማግባታቸው ከተፈቱ በኃላ መገለል ደርሶባቸዋል

ልጃገረዶቹ ካጋቾቹ ይልቅ እርስ በርስ መወቃቀስ ከጀመሩ በኋላ ምን ላይ እንደደረሱ በዚህኛው ክፍል እንመልከት።

የእገታውን ማስታወሻ የቀድሞ ክፍሎችን ለማግኘት ፦

9) ቪድዮዎቹ እዴት ተቀዱ?

የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በየጊዜው ያገቷቸውን ልጃገረዶች በቪድዮ እየቀረጹ ይለቁ ነበር። ይህ ደግሞ ስለ ቀረጻው የውስጣዊ እይታ የሚሰጠን ክፍል ነው።

" ከአንድ ቀን በፊት መጥተው ከመካከላችን 10 የሚሆኑትን ከዛፉ ሥር በቪድዮ ቀረጿቸው። አንድ በአንድ እየነጠሉ ስማቸውንና ስለቤተሰቦቻቸው ጥያቄ መጠየቅ ጀመሩ። ከዚያም 'ጉዳት አድርሰንባችኋል? 'ብለው ሲጠይቁን እኛም 'አይ' ብለን መለስን። ለቤተሰቦቻችንና ለመንግሥት ምን እያደረጉን እንደሆነ እንድንናገር ጠየቁን። ምክንያቱም መንግሥትና ቤተሰቦቻችን እየደፈሩንና እየረበሹን እንደሆነ ስለተናገሩ። ''

"ከኛ መካከል አንደኛዋን ወስዶ 'ካገትንሽ ሰዓት አንስቶና እዚህ ቦታ ካመጣንሽ ጀምሮ ደፍረንሽም ሆነ አብረንሽ ተኝተን እናውቃለን?' ብሎ ሲጠይቃት እሷም 'አይ' ብላ መልስ ብትሰጠውም በድጋሚ ጠየቃት 'ለቤተሰቦችሽና ለመንግሥት ምን እያደረግንልሽ እንደሆነና እንዴት እየተንከባከብንሽ እንደሆነ አሳያቸው። ''

በነገው የመጨረሻው ክፍል ምን ይፈጠር ይሆን? ነገ እንመለስበታለን።