የካታሎንያ ባለስልጣናት ተይዘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጥያቄ ቀረበ

የካታሎንያ ባለስልጣናት ተይዘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጥያቄ ቀረበ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የስፔን ፍርድ ቤት ስምንት የካታሎንያ ባለስልጣናት ተይዘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጠየቀ።

የስፔን መንግሥት አቃቤ ሕግ የካታሎንያን ነፃነት እንቅስቃሴ ሲመሩ ነበር ያላቸውን ስምንት ባለስልጣናት የመያዣ ትዕዛዝ እንዲወጣባቸው ጠየቀ።

ከዚህም በተጨማሪ የነፃነት እንቅስቃሴው መሪ የነበሩት ካርልስ ፒዩጅመንትም ካሉበት የአውሮፓ ክፍል ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚያስችል ትዕዛዝም ተጠይቋል።

ባለሥልጣናቱ አመፅ በማነሳሳት እንዲሁም የመንግሥት ገንዘብ በማባከን ወንጀል ነው የተከሰሱት።

ባለፈው ሰኞ የስፔን ከፍተኛ አቃቤ ሕግ "በአማፅያኑ" ላይ ክስ እንደሚከፍት መግለፁ ይታወሳል።

ፒዩጅመንትና የተወሰኑ ሚንስትሮቻቸው በቤልጂየም የሚገኙ ሲሆን መሪው ጥገኝነት እንደማይጠይቁ ተናግረውም ነበር።

ካርለስ ፒዩጅመንት ለካታላኖንያ ነጻነት ሕዝበ-ውሳኔ በማካሄድ ነፃነት ቢያውጁም የሃገሪቱ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ግን ምርጫውን ውድቅ አድርጎታል።

አሁን ላይ የስፔን መንግሥት ካታላኖንያን በቀጥታ ተቆጣጥሮ ይገኛል።