አዕምሮዎን ያዳብሩ - እንቆቅልሽ 14

የዛሬውን እንቆቅልሽ እስኪ ይሞክሩ

ጥቁር እና ነጭ ኮፍያ ያደረጉ የህግ ታራሚዎች

እንቆቅልሽ 14

ያሉት ከአበበ እና ከከበደ ጋር በእስር ቤት ውሰጥ ነው። ሶስታችሁም በመስመር ቆማችሁ ወደ ፊት ለፊት እየተመለከታችሁ ነው። እርስዎ ከፊት ሲሆኑ ከእርስዎ ኋላ ደግሞ አበበ ከእሱ ቀጥሎ ደግሞ ከበደ አለ።

ሶስት ጥቁርና ሁለት ነች ኮፍያዎች አሉት። ምንም መምረጥ እጁ የገባለትን ኮፍያ እያነሳ ለእያንዳንዳችሁ አደረገላችሁ።

ከበደ የእርስዎንና የአበበን ኮፍያ ማየት ይችላል። አበበ ደግሞ የእርስዎን ክፍያ ማየት ይችላል። እርስዎ ግን የማንንም ማየት አይችሉም።

ሦስታችሁም የእስር ቤቱ ጠባቂ ያደረገላችሁ የኮፍያ ቀለም ዓይነት አታውቁም።

የእስር ቤቱ ጠባቂም "ከመካከላችሁ አንዳችሁ የሌሎቹን የኮፍያ ቀለም ሳይናገር የራሱን የኮፍያ ቀለም በትክክል ካወቀ፤ ሁላችሁም ከእስር ነፃ ትወጣላችሁ" ይላቸዋል።

በመጀመሪያም ከበደ እንዲመልስ እድል ይሰጠዋል። ከበደም በጣም ቅንና ብልህ ሰው ቢሆንም " አላውቅም። ይህን በእርግጠኝነት የማውቅበት ምንም መንገድ የለም" ይላል።

የእስር ቤቱ ጠባቂም ቀጥሎ አበበን ይጠይቀዋል። አበበም ብልህና ምክንያታዊ ሰው ቢሆንም የተጠየቀውን ሊመልስ አልቻለም። ጠባቂው ወደ እርስዎ መጥቶ ሲጠይቅዎ ያደረጉትን የኮፍያ ቀለም ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ሆነው ይነግሩታል።

የእስር ቤቱ ጠባቂም ሦስታችሁንም ከመልቀቅ ሌላ አማራጭ አልነበረውም። ምን ዓይነት ቀለም ያለው ኮፍያ ነበር እርስዎ አድርገው የነበሩት? እንዴትስ ሊያውቁ ቻሉ?

መልሱን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ

መል

እርስዎ ጥቁር ኮፍያ ነው ያደረጉት።

ይህንን እንቆቅልሽ ለመፍታት ሌሎቹ ሰዎች ማየት ያልቻሉትን ማሰብ ይኖርብዎታል። ከበደ ሁለት ነጭ ኮፍያዎችን ለማት አልቻለም፤ ወይም የእራሱ ኮፍያ ጥቁር መሆኑን አላወቀም። ከበደ ጥቁርና ነጭ ወይም ጥቁርና ጥቁር ኮፍያ ቢመለከትም የራሱ ኮፍያ ቀለም ምን ዓይነት እንደሆነ እርግጠኛ አይደለም።

ከበደን ሰምተው ሁለት ነጭ ኮፍያዎችን ለማየት አለመቻሉን ካወቁ በኋላ፤ አበበ እርግጠኛ ሊሆንበት የሚችለው ብቸኛው መንገድ ከፊት ለፊቱ ያለው ነጭ ኮፍያ መሆኑን ከተመለከተ፤ ይህ ማለት የእራሱ ኮፍያ ጥቁር ነው ማለት ነው። ነገር ግን ከበደም የራሱ ኮፍያ ምን ዓይነት ቀለም እንዳለው እርግጠኛ አልነበረም። ስለዚህ እርስዎ በእርግጠኝነት ጥቁር ኮፍያ ነው ያደረጉት።