የአፍሪካ ምርጥ ፎቶዎች፡ በባለፈው ሳምንት አፍሪካ እንዴት አሳለፈች?
በዚህ ሳምንት አፍሪካ ውስጥ የተከሰቱ ነገሮችን የሚያሳዩ ምርጥ ፎቶዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
እነዚህን መኪናዎች ሌላ ቦታ ማግኘት ከባድ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከዚህ የተለየ ነው። ሮይተርስ ባለፈው አርብ ባወጣው ፎቶ ላይ አንድ ግለሰብ እ.አ.አ በ1977 የተሰራች መኪና ላይ ቁጭ ብለው ጥንካሬዋን ያሳያሉ።
የፎቶው ባለመብት, Reuters
ይህ ታዳጊ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በሚገኘው ኪቦሮ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከፈተና በፊት ሲጸልይ ይታያል።
የፎቶው ባለመብት, AFP
በኬንያ የተካሄደው ድጋሚ ምርጫ የብዙዎችን ቀልብ ገዝቷል። በምዕራብ ኬንያ በምትገኘው ኪሱሙ ነዋሪ የሆኑት እነዚህ ሰዎች ምርጫውን በተመለከተ የሚተላለፈውን መረጃ በቴሌቪዥን እየተከታተሉ ነው።
የፎቶው ባለመብት, AFP
በ19ኛው ክፍለ-ዘመን በጃፓን የተጀመረውን "ማንጋ" የሚባለውን የስዕል አይነት በሊቢያ ትሪፖሊ የሚገኝ ሰዓሊ ሲስል።
የፎቶው ባለመብት, AFP
የግብጹ አልሃሊ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ወደ ሞሮኮ አቅንቶ ከመጫወቱ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያደረገውን ልምምድ ደጋፊዎቹ ሲከታተሉ። የደጋፊዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ፕሮግራሙ እንዲሰረዝ ተደርጓል።
የፎቶው ባለመብት, EPA
ይህቺ የአይቮሪኮስት ዜጋ በባህላዊ መንገድ የወይራ ዘይት ስታመርት ይታያል። ለብዙ ነገሮች የሚጠቅመውን የወይራ ዘይት ምርታማነት ለማሳደግ የአይቮሪኮስት መንግሥት ዕቅድ ይዟል።
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
አስደሳች ቢመስልም እነዚህ ሊቢያዊያን አራት ኪሎሜትር የሚረዝመውንና በሽቦ አጥር ስር ጭምር የሚደረገውን አስቸጋሪ ውድድር ባለፈው ቅዳሜ አካሂደዋል።
የፎቶው ባለመብት, AFP
ባለፉት ዓመታት በጦርነት ሲታመስ በቆየችው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ካሳይ ክልል የሚገኙ ህጻናት በፈራረሰ ህንጻ አካባቢ ሲጫወቱ።
የፎቶው ባለመብት, PA
የቀድሞው የእንግሊዝ የኪሪኬት አምበል ማይክል ቫውጋንና ደቡብ አፍሪካው ኮከብ ሄርሼል ጊብስ ባለፈው ቅዳሜ በኪጋሊ የተካሄደውን የኪሪኬት ጨዋታ በአምበልነት መርተዋል።
የፎቶ ምንጭ፡ AFP, EPA, PA እና Reuters