የቢቢሲ የዓመቱ አፍሪካዊ እግርኳስ ተጫዋች እንዴት ይመረጣል?

የቢቢሲ ምርጫ

የቢቢሲ የ2017 አፍሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋች ሽልማት የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች በቢቢሲ ዓለምቀፍ አገልግሎት፣ በቢቢሲ ዓለማቀፍ ዜና፣ በቢቢሲ ድረገጽ እና በማህበራዊ ሚዲያ በቀጥታ በተላለፈ ልዩ ዝግጅት በይፋ ተጀምሯል።

የድምጽ መስጫ ገጹ ደግሞ ከምሽት 3:50 ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኗል።

የድምጽ አሰጣጥ ሂደቶችና መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦

ጩዎቹ አመራረጥ ሂደት

አምስቱ ተጫዋቾች የሚመረጡት አፍሪካዊና ሌሎች የእግርኳስ ባለሙያዎች ምርጥ አምስቶችን እንዲመርጡና ከ1-5 ውጤት እንዲሰጧቸው በመጠየቅ ነው( ከፍተኛው 5 ነጥብ ያገኛል ማለት ነው)።

ዕጩዎችን የሚመርጡባቸው መስፈርቶች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው።

የስፖርት ልምድ፡ የግል ክህሎት፣ የቴክኒክ ችሎታ፣ የቡድን ሥራ፣ ለውጤት የነበራቸው ሚና፣ ዋንጫዎች፣ፍትሃዊ ጫወታ፣በ2017 ወጥ አቋም ማሳየት እንዲሁም የአቋም ማሳደግ

አካባቢያዊ ተጽዕኖ፡ ተጫዋቹ በእግርኳስና በስፖርት ሜዳ ውስጥም ሆነ ከሜዳ ውጭ ለአካባቢው ያበረከተው ሚና

ዓለማቀፍ ጠቀሜታ፡ ለዓለማቀፍ ጫወታዎችና ለእድገቱ የሰጠው ጥቅም

ከዚህም በተጨማሪ ከጥር 2017 ጀምሮ እስካሁን ያለውን ጊዜ እንደመለኪያ እንዲጠቀሙበት ተጠይቀዋል።

የዕጩነት ምርጫውን ለመለየት አደጋች በሚሆንበት ጊዜ የቢቢሲ የዓመቱ የአፍሪካ እግርኳስ ተጫዋች አዘጋጆች ቡድን የመጨረሻዎቹን ዝርዝር እስከ ስድስት ማድረስ ይችላሉ።

እጩ መሆን የሚችለው ማነው?

የቢቢሲ አፍሪካ የዓመቱ እግርኳስ ተጫዋች መባል የሚችለው በአፍሪካ ብሄራዊ ቡድኖች ሀገሩን መወከል የሚችል ተጫዋች ነው።

የህዝብ ምርጫ

የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ዝርዝር ይፋ ከሆነ በኋላ አሸናፊው የሚወስነው በድረገጽ በሚሰጥ የህዝብ ድምጽ ነው።

የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ቅዳሜ ህዳር 2 ምሽት 3፡50 ተጀምሮ ህዳር 18 ምሽት 3 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል።

የመጨረሻው ውጤት ደግሞ ታህሳስ 2 ምሽት 2፡35 ላይ በ 'ፎከስ ኦን አፍሪካ' ዝግጅት ላይ ይፋ ይደረጋል።

በቢቢሲ ስፖርት የአፍሪካ እግርኳስ ድረ-ገጽ ላይም ከመመሪያና ሁኔታዎች ጋር ያገኙታል።

ሁለት ተጫዋቾች ተመሳሳይ ውጤት ካመጡ ሽልማቱን ይጋሩታል።

Image copyright BBC Sport

በድረ-ገጽ እንዴት መምረጥ ይቻላል?

የቢቢሲ ስፖርት የአፍሪካ እግርኳስ ድረገጽን በመጎብኘትና መመሪያዎችን በመከተል ድምጽ መስጠት ይችላሉ።

በአንድ ኮምፒዮተር ድምጽ መስጠት የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው።

ለመምረጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

የቢቢሲ የዓመቱ አፍሪካዊ እግር ኳስ ተጫዋች መምረጫ ገፅ

የህዝድ ድምጽ- ደንቦችና ሁኔታዎች

1. ይህ ምርጫ በቢቢሲ የሚካሄድ በመሆኑ ሽልማቱም የቢቢሲን የውድድርና የምርጫዎች መመሪያን የሚከተል ይሆናል።

2. አሸናፊው 'የቢቢሲ የ2017 አፍሪካዊ እግርኳስ ተጫዋች'' ተብሎ ይሰየማል፤የተቀረጸ የዋንጫ ሽልማትም ያገኛል።

3. የቢቢሲ የዓመቱ አፍሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋች በህዝብ ድምጽ ከመዳኘቱ በፊት የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች በአፍሪካውያን የእግርኳስ ባለሙያዎች ይመረጣሉ።

4. የመጨረሻ ዕጩዎች የተመረጡባቸው መስፈርቶች ውስጥ የግል ልምድ፣ቴክኒካዊ ችሎታ ፣የቡድን ስራ፣በውጤት ላይ ያለ ተፅእኖ፣ሽልማት፣ፍትሀዊ ጨዋታ እንዲሁም ተጫዋቾቹ በእግር ኳሱም ይሁን በስፖርቱ፤ በአካባቢው በሜዳም ይሁን ከሜዳ ውጭ፤ እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ጨዋታዎችና ልማት በ2017 ያደረጉት አስተዋፅኦ ይገኙበታል።

5. የመጨረሻ ዕጩዎች ዝርዝርም በቢቢሲ ስፖርት አፍሪካን ፉት ቦል ድረ-ገፅ ላይ ለህዝብ ምርጫ ክፍት ይሆናል።

6. ቢቢሲ የምትሰጡትን የግል መረጃ ከ'ፕራይቬሲ' ፖሊሲያችን እንዲሁም ከአጠቃቀማችን ሂደት ጋር በማዛመድ እንጠቀምበታለን። ለምሳሌ ምርጫውን ለማካሄድ እንዲሁም በምርጫው ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ እክሎችን ለመርመር የግል መረጃዎቻችሁን እንጠቀምበታለን።

7. የምርጫው መዝጊያ ቀን ህዳር 18 2010 ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ነው።

8. የምርጫው ውሳኔ የመጨረሻ ሲሆን ሌሎች ግንኙነቶች አይፈቀዱም።

9. ሽልማቱ በተባለበት ቀን መወሰድ ያለበት ሲሆን ለሌላ ጊዜ አይተላለፍም። የሽልማቱን አይነት መምረጥ አይቻልም፤ ወደ ብርም አይቀየርም።

10. ቢቢሲ ከተቋራጮቹ ፣ከአጋሮቹ እና ከሌሎች ኤጀንሲዎች ለሚከሰቱ የቴክኒካል ችግሮች፣ ስህተቶች፣ ከኢንተርኔት አቅርቦት ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ በኢንተርኔት ላይ፣ከኢንተርኔት አቅራቢው ወይም ከመሳሪያዎች ጋር በሚመጡ ችግሮች ምክንያት የምርጫ ውጤቶች በትክክል ባይመዘገቡ ወይም ቢጠፉ ቢቢሲ ኃላፊነትን አይወስድም።

11. ቢቢሲ ምርጫው የተጭበረበረ ለመሆኑ እንዲሁም ምርጫውን ለመቀልበስ የሚደረጉ ሙከራዎች አሉ የሚል ምክንያት ካለው ምርጫውን ውድቅ የማድረግ እንዲሁም የማገድ መብት አለው። ቢቢሲ ምርጫውን በትክክለኛ መንገድ ለማስኬድ በተለየ የምርጫ መንገድ የመተካት መብት አለው። እክል አለባቸው ብሎ የሚያምናቸውን ምርጫዎች ለመርመር በምትመርጡበት ድረ-ገፅ (bbc.co.uk)የሰጣችሁትን የግል መረጃ ያላችሁበትን ቦታ የሚያሳየውን (ኢንተርኔት ፕሮቶኮል) አድራሻ ሊጠቀም ይችላል። ቢቢሲ እነዚህን መረጃዎች ውልን ለማስፈፀም በሚያስፈልጉበት በስተቀር ያለፈቃድ አያትምም፤አሳልፎም አይሰጥም።

12. በዚህ ምርጫ ላይ የሚሳተፉት እነዚህን ህግጋት ከመቀበል በተጨማሪ በነሱም ለመተዳደር ተስማምተዋል። ማስተዋል ያለባችሁ ቢቢሲ የሚሰራ ሰው ወይም በቀጥታ ከዚህ ሽልማት ጋር የሚገናኝ ሰው የመመምረጥ መብት የለውም።

13. ሁሉም የአመራረጥ ሂደቶችን ቢቢሲ አፍሪካ በበላይነት ይቆጣጠራል።

14. ተወዳዳሪዎቹ ሽልማቱን ጉዳት ላይ ጥለውታል ብሎ ካመነ፤ ወይም ደግሞ ቢቢሲን የሚያሳፍር መስሎ ከተሰማው ተመራጩን ውድቅ የማድረግ ወይም ሽልማቱን የመያዝ መብት አለው።

15. ይህ ምርጫም ሆነ እነዚህ ህግጋት በእንግሊዝና ዌልስ ህጎች ይተዳደራሉ።