የሩስያ አብዮት፡ አአአ ከ1917 ጀምሮ የነበሩ አስር የፕሮፖጋንዳ ፖስተሮች

  • By Vera Panfilova
  • State Central Museum of Russian Contemporary History

የሩሲያ አብዮት ጣራ የነኩ ዓመፆችን ያስተናገደ ቢሆንም ከፍተኛ ፈጠራም የተስተዋለበት ወቅት ነው።

የአብዮቱን 100ኛ ዓመት ክብረ-በዓል በሚዘከርበት ወቅት፤ እአአ ከ1917 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ ማንቀሳቀስ የቻሉ አስር ፎቶዎች እነሆ፡

የነፃነት "ብድር"

የፎቶው ባለመብት, sovrhistory.ru

የሩሲያ በአንደኛው የዓለም ጦርነት መሳተፍ ከፍተኛ ገንዘብና ጉልበት በመፍሰሱ እአአ ከ1917 ዓ.ም ጀምሮ በነበረው የፊውዳል አገዛዝ ዛር ላይ ከፍተኛ የሆነ ዓመፅን አቀጣጥሏል።

የቦሪስ ኩስቶዲየቭ ታዋቂ ስዕል የሆነው አንድ ጠመንጃ የተሸከመ የሩሲያ ወታደር ብዙዎችን ለጦርነቱ ገንዘብ እንዲለግሱ አነሳስቷል። ይህ ፖስተር በየካቲት ወር "የነፃነት ብድር"ን የሚለውን ሀሳብ ለማስተዋወቅ ሲሆን፤ ሁለተኛው የጥቅምት አመፅ እስከተነሳበትም ድረስ ይህ ወታደር በተለያዪ ፓስተሮች ታይቷል።

አብዮታዊ ቀናት

የፎቶው ባለመብት, sovrhistory.ru

በአውሮፓውያን መጋቢት እአአ 1917 የሞስኮ ቮስክረሴንስካያ አደባባይና የከተማዋ የፓርላማ ህንፃ ለአብዮታዊ ሰልፎች ማዕከላዊ ቦታዎች ነበሩ።

ይህ ፖስተርም የሚያሳየው አብዮቱን አዲስ ምዕራፍ ከፋችነቱን እንዲሁም ህዝቡ ምን ያህል የጠለቀ ስሜትና ጉጉት ለአብዮቱ እንደነበረው ነው። ይህ ሁሉ የተከናወነውም ከጦርነት ጀርባ በተቃራኒ ነው።

መሪዎቹ ወንዶች

የፎቶው ባለመብት, sovrhistory.ru

ይህ በእውነቱ ፖስተር አይደለም። በበራሪ ወረቀት ላይ የተሳለው ይህ ስዕል በሩሲያ ውስጥ የነበረውን የስልጣን አደራደር ሰውኛ ምስል በመስጠት ነው። እነዚህ ወንዶችም በሽግግር መንግሰቱ መሪ የሆኑ ታላላቅ የፓለቲካ ሰዎች ናቸው።

መሀል ላይ የሚታዩት የአገሪቷ ፓርላማ ሊቀ-መንበር ሚክሄይል ሮዲዚያንኮ ፤ የሀገሪቷ የመጀመሪያው ሶሻሊስት ፓርቲና ሊቀ-መንበር አሌክሳንደር ኬረንስኪ በግራ በኩል ተቀምጠዋል።

ከላይ በኩል ያለው ደግሞ የሚያሳየው መሳሪያ የታጠቁ ወንዶች "መሬትና ነፃነት" እንዲሁም "በትግል ብቻ ነው መብት የሚከበረው" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው፤ እንዲሁም ለጊዜው ቦልሸቪካውያን የሉም የሚሉ ናቸው።

የተቀየረው ንፋስ

የፎቶው ባለመብት, sovrhistory.ru

ይህ ግራ ዘመም ከሆነው ፓሩስ ከሚባለው ማተሚያ ቤት የተገኘ ሲሆን፤ የተቆረቆረውም ከፀሀፊው ማክሲም ጎርኪ አብዮት በፊት ነበር።

የፓስተሮቹን ሀሳብ ያመነጩ የነበሩት እንደ ቭላድሚር ማያኮቭስኪና አሌክሲ ራዳኮቭ የመሳሰሉ ገጣሚያንና አርቲስቶች ናቸው።

ከላይ ያለው ምስል አንድ ወታደር ንዑስ ከበርቴን ሲከላከል የሚያሳይ ሲሆን በምስሉ ላይ ያለው መግለጫም " ወታደሩ እነዚህን ነበር ከጥቃት የሚከላከለው" የሚል ነው።

ሁለተኛው ምስል ከአብዮቱ በኋላ ሲሆን የምስል መግለጫውም "መሬትና ነፃነት!"፣ዲሞክራሲና ሪፐብሊክ"፣ "ነፃነት" የሚሉ ሲሆን ወታደሩም አሁን እነዚህን ነው የሚደግፈው የሚል የምስል መግለጫም ተሰጥቶታል።

የምትወጣው ፀሀይ

የፎቶው ባለመብት, sovrhistory.ru

እአአ በመጋቢት በ1917 ዛር ኒኮላስ ሁለተኛ ተገርስሶ የሀገሪቷ የፓርላማ ተወካዮች የሽግግር መንግስትን መስርተዋል።

የፓስተሩ ርዕስም "የህዝብ ድል ማስታወሻ" የሚል ነው።

እንደሚያሳየውም በትህትና የተሞላው ዛር ለአብዮታዊ ሀይሎች ስልጣንን ሲያስረክብ ነው።

የተመሰለውም በወታደርና በሰራተኛ ነው። ከጀርባ የሚታየው የታውሪድ ቤተ-መንግስት ሲሆን፤ የፓርላማ አባላቶቹም የተገናኙበት ነው።

ከላይ የምትታየዉ በመውጣት ላይ ያለቸው ፀሀይም የነፃነት ምሳሌ ናት። በዛን ጊዜ በነበረውም ፖስተሮች የተወደደ ምልክት ነው።

ማህበራዊው ፒራሚድ

የፎቶው ባለመብት, Sovrhistory.ru

በፓሩስ ማተሚያ ቤት የማያኮቭስኪ ራዳኮቭ የተጣመሩበት ስራ ነው። በቀልድ መልኩ የተሰራው ይህ ፖስተር ዛሩ መጎናፀፊያውን እንደለበሰ ህዝቡን ከላይ ሆኖ ሲያይ የሚያሳይ ነው። ከላይ ወደታችም ፅሁፉ ሲነበብ " እንገዛለን፤ እንፀልይላችኋለን፤ እንዳኛችኋለን፤ እንጠብቃችኋለን፤ እንመግባችኋለን፤ እናንተም ትሰራላችሁ" የሚል ነው። እነዚህ ታዋቂ የሆኑ ምፀታዊ ታሪኮች ከክረምት 1917 በኋላ በዛሩ ኒኮላስ ሁለተኛና በሚስቱ ላይ ያተኮረ ሲሆን በተጨማሪም በፊውዳሉ ስርአትን ለመቃወም ያነጣጠረ ነው።

የዘመቻው አካሄድ

የፎቶው ባለመብት, sovrhistory.ru

በ1917ቱ የበልግ ዘመን ሩሲያ የመጀመሪያውን የጠቅላላ ምርጫ ዘመቻ ማካሄድ ጀመረች። ፉክክሩ ጠንክራና የማይነቃነቅ ነበር። በርካታ ድርጅቶች ቢሳተፉበትም ከፍተኛ ቦታ የነበረው ግን የሶሻሊስት አብዮታዊ ፓርቲ ነበር። ፖስተሩ ላይ የሰፈሩት ቃላት ደግሞ '' ጓድ ዜጎች በተወካዮች ጉባኤ ቀን ራሳችሁን ለሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጁ'' የሚል ነበር።

"አናርኪ በዴሞክራሲ ይደመሰሳል''

የፎቶው ባለመብት, sovrhistory.ru

ይህ የእንስሳ እና የአፈታሪካዊ ምስሎች ስብጥር ፖስተር የሊበራል ካዴት ፓርቲ ነው፤ ግዙፉ ድራጎን አናርኪን(የመንግስትን አወቃቃር የሚቃወሙትን) ሲወክል ፈረሰኛው ደግሞ የዴሞክራሲ ተምሳሌት ነው።

ሰንሰለቱን መሰባበር

የፎቶው ባለመብት, sovrhistory.ru

የሶሻሊስት አብዮታዊ ፓርቲ የምርጫ ፖሰተር ቀላልና ሰራተኞችና አርሶደሮችን ኢላማ ያደረገ ነበር።

'' መብታችሁን የምታገኙት በትግል ብቻ ነው'' ይላል። ያካሄዱት ዘመቻም በጣም ተወዳዳሪ ሲሆን ድላቸውን የተጎነጸፉበት መሪ ቃል ደግሞ ''መሬትና ነጻነት' እንዲሁም " ሰንሰለቱን ሰባብሩ፤ያኔ መላው ዓለም ነጻ ይሆናል'' የሚሉ ነበሩ።

ዘግይቶ የተቀላቀለው ፓርቲ

የፎቶው ባለመብት, sovrhistory.ru

የቦልሼቪክ ፓርቲ(አር ኤስ ዲ ኤል ፒ) የፖስተር ጫወታውን የተቀላቀለው ዘግይቶ ነው፤ ይህ የ1917 የምርጫ ዘመቻ ፖስተር '' የአር ኤስ ዲ ኤል ፒን ይምረጡ'' የሚል ብቻ ነው የሰፈረበት።

አር .ኤስ .ዲ. ኤል. ፒ የሩሲያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ሌበር ፓርቲ ምህጻረ ቃል ነው። በሩሲያ ቋንቋ ግን አር.ኤስ.ዲ.አር.ፒ ነው።

ህዳር 1917 የእርስ በእርስ ጦርነት ሲቀሰቀስ ቦልሼቪክም በፖስተር የሚመራውን የሶቪየት የፕሮፖጋንዳ ዘዴ ተቀላቀለ።

ማያኮቪስኪ እና ራዳኮቭን የመሳሰሉ አርቲስቶችን ያቀፈ ቡድንም ዝነኛውን 'ሮስታ ዊንዶው' የተሰኘ መለያ ሥም ፈጠረ። ፖስተሮቹ ቀለል ያሉ፣ አጭር፣ ቀጥተኛና ግልጽ መልዕክት የሰፈረባቸው ነበሩ።በሂደትም የሶቪየት መገለጫና የዓለማቀፍ የፖስተር ዲዛይኖች ተመሳሌቶች ሆኑ።

የሩሲያ ዘመናዊ ታሪክ ማዕከላዊ ሙዚየም ዳይሬክተር ቬራ ፓንፊሎቫ ነበረች ከቢቢሲ የሩሲያ አገልግሎት አሌክሳንድሪያ ሴምዮኖቭ ጋር የተነጋገረቸው።