ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንታቸውን ምናንጋግዋ ታማኝ አይደሉም በማለት ከስልጣን አባረዋል

ኤመርሰን ሙዋንጋ

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ,

ኤመርሰን ምናንጋግዋ ፕሬዝደንት ሙጋቤን በቀጣይ ይተካሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው መሪ ነበሩ።

የዝምባብዌ መንግሥት የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ከስልጣን መነሳታቸውን ይፋ አድርጓል።

የ75 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ፤ ''ታማኝ'' አይደሉም ሲሉ የኢንፎርሜንሽን ሚኒስትሩ ሳይመን ካሃያ ሞዮ ተናግረዋል።

የምክትል ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን በመነሳታቸው የሮበርት ሙጋቤ ባለቤት የሆኑት ግሬስ ሙጋቤ ባለቤታቸውን በመተካት ቀጣይ የዝምባብዌ መሪ ይሆናሉ ተብሏል።

ከዚህ በፊት ግሬስ ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንቱን ከስልጣናቸው እንዲያነሱ ሮበርት ሙጋቤን ሲወተውቱ ነበር።

የቀድሞው የደህንነት ሹም የነበሩት ምናንጋግዋ ፕሬዝዳንት ሙጋቤን የመተካት ተስፋ የተጣለባቸው መሪ ነበሩ።

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ,

ግሬስ ሙጋቤ እና ኤመርሰን ምናንጋግዋ

ምናንጋግዋ ከምክትል ፕሬዝዳንትነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በቀጣይ ወር ፓርቲው በሚያደርገው ስብሰባ ላይ የሙጋቤ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳናት ሆነው ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው እሁድ በዋና ከተማዋ ሃራሬ ግሬስ ሙጋቤ ባደረጉት ንግግር ''እባቡ በሃይል ጭንቅላቱን መመታት አለበት። በፓርቲው ውስጥ መከፋፈል እና አለመግባባትን የሚፈጥሩትን ማስወገድ አለብን። ወደ ቀጣዩ የፓርቲያችን ስብሰባ በአንድ መንፈስ ነው መሄድ ያለበን'' ሲሉ ተደምጠዋል።