የፓራዳይዝ ሰነዶች በአፍሪካ ተፈጥሯዊ ሃብቶች ላይ እየተደረገ ያለውን ዝርፍያ እያጋለጡ ነው

Katanga mine Image copyright Premieres lignes
አጭር የምስል መግለጫ ካታንጋ የማዕድን ማውጫ ስፍራ-ዲሞክራቲክ ሪፓፐሊክ ኦፍ ኮንጎ

በዓለማችን ከሚገኙ ታላላቅ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ግሌንኮር በ45 ሚሊዮን ዶላር ሙስና ለሚጠረጠር ነጋዴ ገንዘብ ካበደረ በኋላ ድሃ በሆኑ በመካከለኛው አፍሪካ በሚገኙ ሃገራት ውስጥ የማዕድን ፍለጋ ሥራ ላይ ለመሰማራት ፍቃድ እንዲደራደር መጠየቁን የፓራዳይዝ ሰነዶች (የፓራዳይዝ ፔፐርስ) አጋልጧል።

የፓራዳይዝ ስነዶች ምድን ናቸው?

የፓራዳይዝ ሰነዶች አምልጠው የወጡ የፋይናንስ (የገንዘብ) ሰነዶች ናቸው።

ሰነዶቹ የዓለማችን ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እና ብዙ ትርፍ የሚያስገቡ ግለሰቦች ገንዘባቸውን ከከፍተኛ ግብር ለማሸሽ ሲጠቀሙበት የነበረውን የረቀቀ ዘዴ ያጋለጡ ናቸው።

ባለፈው ዓመት የፓናማ ሰንዶች በጀርመኑ ጋዜጣ ዙተቹ ሳይተን እጅ ከገቡ በኋላ ቢቢሲ ፓኖራማ እና ዘ ጋርድያንን ጨምሮ ከሌሎች 100 የህዙሐን መገናኛ ተቋማት ጋር በመሆን በሰነዶቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው።

የአንግሎ-ስዊዝ ኩባንያው ግሌንኮር የብድር አቅርቦቱን የሰጠው እአአ በ2009 ለእስራኤላዊው ቢሊየነር ዳን ገርትለር ሲሆን ግለሰቡ በዲሞክራቲክ ሪፓፐሊክ ኦፍ ኮንጎ ውስጥ ከፍተኛ ባለስልጣናት መሃል የደለላ ስራ ይሰራ ነበር ተብሏል።

ቢሊየነሩ ገርትለር እንዲያስማማ ተጠይቆ የነበረው ለማዕድን አውጪ ኩባንያ አዲስ የማዕድን ውጣት ፍቃድን ማስገኘት ነበር። በዚህ የማዕድን አውጪ ኩባንያ ውስጥ ግሌንኮር ትልቅ ድርሻ የነበረው ሲሆን ተሟጋቾች ይህ ስምምነት ድሃዋን የአፍሪካ ሃገር ዲሞክራቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎን በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አሳጥቷታል ይላሉ።

ቢሊየነሩ ገርትለር እና ግሌንኮር ምንም አላጠፋንም ይላሉ።

ግሌንኮር ለዳን ገትለር በያዝነው ዓመት የካቲት ወር ላይ ከዲሞክራቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎ ማዕድን ቁፋሮ ወለድ የሚገኝ 534 ሚሊዮን ዶላር ለመክፍል ተስማምቶ ነበር።

የመካከለኛዋ አፍሪካ ሃገር በግጭት ስትታመስ እና ለአስርት ዓመታት በሙስና ተዘፍቃ ከመኖሯ በላይ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ዜጎቿ ከድህነት ወለል በታች ህይወታቸውን ይገፋሉ።

ይህ ይሁን እንጂ የሃገሪቷ ሰፊው የማዕድን ሃብት የተጠቀሙበት በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኞች የሚቆጠር ገንዘብ ያስገባሉ።

ይህም ግዙፉን ግሌንኮር፥ የአንግሎ-ስዊዝ የማዕድን እና ሸቀጥ ንግድ ኩባንያን ይጨምራል።

በገቢ ልኬት ግሌንኮር በፕላኔታችን 16ኛው ግዙፉ ኩባንያ ነው።

ግሌንኮር በዲሞክራቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎ ውስጥ በማዕድን ሥራ በተለይ መዳብ በማምረት ለበርካታ ዓመታት ተሰማርቶ ቆይቷል።

ኩባንያው እንደሚለው በሃገሪቱ ውስጥ 50 ቢሊያን ዶላር በስራ ላይ አውሏል። ከአስር ዓመት በፊት ግሌንኮር በሃገሪቱ ደቡባዊ ክፍል መዳብ የማውጣት ፍቃድ ከነበረው ካታንጋ ኩባንያ ውስጥ የ8.52 በመቶ ድርሻ ነበርው።

ሰኔ 2008 የግሌንኮር ከፍተኛ ባለስልጣናትን የያዘው የካታንጋ ቦርድ መልካም ያልሆነ ዜና ሰማ።

በፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ የሚመራው የዲሞክራቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎ መንግሥት በማዕድን ማውጣት ፈቃድ አስጣጥ ላይ በድጋሚ መደራደር እንደሚፈልግ አስታወቀ። በወቅቱ ግሌንኮር በካታንጋ ኩባንያ ውስጥ 150 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ አድርጎ ነበር። ኩባንያው በማዕድን ማውጣት ስራ ላይ ካልተሳተፈ ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ መባከኑ ነው።

በሃገሪቱ መንግሥት ስም ተመዝግቦ የነበረው ጌካማይንስ መዳብ እና ኮባልት ለማውጣት 585 ሚሊዮን ዶላር ጠየቀ።

ቀድሞ የነበረው ስምምነት ግን 135 ሚሊዮን ዶላር ነበር።

በፓራዳይዝ ሰነዶች ውስጥ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የካታንጋ ቦርድ የዲሞክራቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎ መንግሥት ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ከልክ ያለፈ እንደሆነ ተሰምቷቸው ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜም የኩባንያው ዳይሬክተሮች እራኤላዊውን ዳን ገትለርን ለእርዳታ ጠርተውት ሊሆን ይችላል።

የሰነዱ ምንጭ፡ የካታንግ ቦርድ ቃለጉባኤ- ሰኔ 2008(እአአ)

በካታንጋ ቦርድ ቃለጉባዔ ''ቦርዱ በኩባንያው ከፍተኛ ተዘዋዋሪ ጥቅም የሚያገኘው ዳን ገትለር ከኮንጎ ባለስልጣናት ጋር የመደራደር ስልጣን ሊሰጠው ይገባል'' የሚል ጽሁፍ ሰፍሯል።

''ቦርዱ... ገርትለር በዚህ መልኩ ለመንቀሳቃስ ዝግጁ መሆኑን ቀርቦ ማረጋገጥ አለበት'' ይላል።

ገርትለርም ካታንጋን ወክሎ ስምምነት ላይ ለመድረስ እንዲደራደር ጥያቄ ቀረበለት።

በዚሁ ተመሳሳይ ወቅት ግሌንኮር በካሪቢያን የብሪታንያ ደሴቶች ለሚገኘው ሎራ ኢንተርፕራይዝ የ45 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት ተስማማ።

ሎራ ኢንተርፕራይዝ በገርትለር ቤተሰቦች የሚመራ ድርጅት ነበር።

ግሌንኮር ለካታንጋም 265 ሚሊዮን ዶላር አበደረ። በኋላ ደግሞ የብድሩ ገንዘብ ወደ አክሲዮን ድርሻ ተቀየረና ግሌንኮር ከፍተኛው ባለድርሻ ሆነ። ዳን ገርትለርም ቢሆን ከሎራ ኢተርፕራይዝ ብድር ምንም ጥቅም እንዳላገኘ ቢናገርም በማዕድኑ ጉዳይ እጁን እንዲያስገባ መንገድ ከፍቶለት ነበር።

የሰነዱ ምንጭ

ካታንጋ በአውሮፓውያኑ 2009 በቶሮንቶ የአክሲዮን ዝውውር ጊዜ የብድሩን ወደ ድርሻ መቀየር ይፋ ቢያደርግም ዝርዝር መረጃው ግን እስካሁን ግልጽ አልነበረም።

በገርትለር የበድር ስምምነት ላይ በ3 ወራት ውስጥ አዲስ የመብት ስምምነት ማቅረብ ካልቻለ ግሌንኮር ብድሩን በፍጥነት የማስመለስ መብት እንደሚያገኝ ተጠቅሶ ነበር።

የፓራዳይዝ ሰነዶች ገርትለር ይህ በፍጥነት ተሳክቶለት እንደነበረ ይጠቅሳሉ። ጌካማይንስም የመጀመሪያውን የ585 ሚሊዮን ዶላር የመነሻ ክፍያ ጥያቄ ወደ 140 ሚሊዮን ዝቅ አድርጎታል። ይህ ደግሞ ካታንጋ በመጀመሪያው ስምምነት ያቀረበው መነሻ ገንዘብ ጋር እኩል መጠን ስላለው 445 ሚሊዮን ዶላር አትርፎለታል።

የሰነዱ ምንጭ

ፒት ጆንስ ግሎባል ዊትነስ ፀረ-ሙስና ዘመቻ እንደተናገሩት እንደ ግሌንኮር ያሉ ስምምነቶች እንደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ላሉ ሀገራት ከፍተኛ መዘዞችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

"በሀገሪቷ ተፈጥሮአዊ ሀብት ጥገኛ ለሆኑ እንደ ዴሞክራቲክ ሪፓፐሊክ ኦፍ ኮንጎ ላሉ ሃገራት ከኢኮኖሚው ገንዘቡን ሙጥጥ አድርገው የሚወስዱ ስምምነቶች ውጤታቸው አሉታዊ ነው።

ገትለር በበኩላቸው ለዲሞክራቲክ ሪፐፓሊክ ኦፍ ኮንጎ ጥሩ ያልሆነ ስምምነት ነው በሚለው ሀሳብ አጥብቀው ይከራከራሉ "ጌካሚንስ ከአዲሱ ጄቪኤ እንዲሁም ካታንጋ ከነበረው የመዳብ እንዲሁም የኮባልት ማዕደኖች ክምችት በ82.5 ሚሊዮን ዶላር መውሰዱ ጠቅሞታል" ብለዋል።

ግሌንኮር ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለሎራ ኢንተርፕራይዝ 45 ሚሊዮን ብድር " በንግድና እንዲሁም ስምምነቱ የተፈፀመውም ነፃ ሆነው ነው"

ከሰባት አመታትም በፊት ሙሉ በሙሉ ተከፍሏል። የገትለር ጠበቆች በበኩላቸው የንግድ ሽርክና ሲፈርስ አበዳሪው አካል ይከፈለኝ ማለቱ ያልተለመደ ጉዳይ አይደለም ብለዋል። በተጨማሪም "ሎራ ኢንተርፕራይዝ፣ ገትለርም ይሁን የትኛውም ኩባንያ የብድሩን ፈንድ በቀጥታ አልተቀበሉም" ብለዋል።

ገርትለር በዲሞክራቲክ ሪፓፕሊክ ኦፍ ኮንጎ ያላቸው መጥፎ ስም ሁለት አስርት ዓመታትን አስቆጥሯል። እአአ 2001 የተባበሩት መንግሥታት የአልማዝ ማዕድን ቁፋሮ መብትን በዋናነት ለመቆጣጠር በጦር መሳሪያና የውትድርና ስልጠና ስምምነት እንዳደረጉ የሚወነጅል ሪፖርት ወጥቷል።

በቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን የሚመራው የአፍሪካ ፕሮግረስ ፓናል ከአራት ዓመት በፊት ባወጣው ሪፖርት የገርትለር ኩባንያ በዲሞክሪቲክ ሪፐሊክ ኦፍ ኮንጎ የአልማዝ ማዕድን የማውጣት ስራን የፈፀሙት ካለው ትክክለኛ ዋጋ በዝቅተኛ እንደሆነ ይጠቁማል። የእስራኤላዊው ባለሀብት ጠበቆች በበኩላቸው በ2001ም ሆነ በ2013 የወጡትን ሪፖርቶች ፍፁም ውንጀላ ነው በማለት ይክዳሉ።

በባለፈው ዓመት ሄጅ ፈንድ ኦች ዚፍ በአሜሪካ ባለስልጣናት በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ጉቦ ከፍለዋል የሚለውን ክስ 412 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል ስምምነት ላይ ለመድረስ ሞክሯል። አቃቤ ህጎቹ እስራኤላዊው ባለሀብትን በስም ባይገልፁትም በኮንጎ የማዕድን ቦታን ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር በመሆን 100 ሚሊዮን ዶላር ጉቦ ከፍለዋል በሚልም ወንጅለውታል።

ዳን ገርትለር በበኩላቸው ይህንን ውንጀላ ክደዋል። በዋናነትም ገርትለር በ2012 የሞቱት የፕሬዘዳንት ካቢላ ቁልፍ አማካሪ የነበሩት ካቱምባ ምዋንኬ ቅርብ ጓደኛ መሆናቸውም ጥርጣሬ ላይ ጥሏቸዋል።

ግሎባል ዊትነስ ለተባለው መንግስታዊ ላልሆነ ድርጅት የሚሰሩት ዳንኤል ብሊንት ኩርቲ በዋነኝነት በዳን ገርትለርና በግሌንኮር መካከል ያለውን የዓመታት ግንኙነት ሲመረምሩ የነበረ ሲሆን ኩባንያው ከባለሃብቱ ጋር የነበረውን ሽርክና ማጤን ነበረበት ይላሉ።

" የኮንጎው ፕሬዚዳንት ቅርብ የነበረ ሰው ቀጥረው ገንዘብ በማንበሽበሽና ለሚደረጉ ስምምነቶች ሙሉ ስልጣን መስጠታቸው ራሳቸውን አደጋ ውስጥ ከተዋልም" ይላሉ።

የዳን ገትለር ጠበቆች ለቢቢሲ እንደተናገሩት "እርሳቸው ብዙ ሀብታቸውን ለተቸገሩ ሰዎች የሚለግሱ የተከበሩ ሰው ናቸው" ብለዋል።