የተባበሩት ምንግሥታት በየመን የዓለማችን አስከፊው ረሃብ ሊከሰት ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ

የመን ረሃብ Image copyright MOHAMMED HUWAIS

ለየመን የሚደረገው እርዳታ እደገና ካልተጀመረ ሚሊዮኖችን የሚጎዳ አስከፊው ረሃብ ሊከሰት ይችላል ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣን አስጠነቀቁ።

ማርክ ሎወኮክ በሳውዲ የሚመራው ጥምር ኃይል የእርዳታ ቁሶች ወደ የመን እንዲገቡ መተባበር አለበት ብለዋል።

ባለፈው ሰኞ የሁቲ አማጺያን ወደ ሳዑዲ ሚሳዬል ከተኮሱ በኋላ ጥምር ኃይሉ ወደ የመን የሚደረጉ የአየር፣ የየብስ እና የምድር መጓጓዣ ዘዴዎችን በሙሉ ዝግ አድርጓል።

ሳውዲ አረቢያ ወደ የመን የሚደረጉ የመጓጓዣ ዘዴዎችን በሙሉ ዝግ ማድረጉ ያስፈለገው ኢራን የመን ውስጥ ለሚገኙ የሁቲ አማጺያን የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዳታደርግ ነው ብላለች።

እአአ ከ2015 ጀርምሮ የሳውዲ መራሽ ኃይልን ስትዋጋ የቆየችው ኢራን፤ ለአማጺያኑ ምንም አይነት ድጋፍ አለደረኩም ትላለች።

በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የተባበሩት ምንግሥታት እና የቀይ መስቀል ማህበር በየመን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚሹ ሚሊዮኖች እርዳታ ማቅረብ አለመቻሉን ተናግረዋል።

በጦርነት እየታመሰች ያለቸው የመን የዜጎቿን ፍላጎት የምታሟለው ሁሉንም አይነት ሸቀጦች ከውጪ ሃገር በማስገባት አው። አሁን ላይ ግን ምግብም ሆነ፣ ነዳጅ አልያም መድሃኒት ወደ ሃገሪቱ ማስገባት አልተቻለም።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ