የቢቢሲ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ዕጩ፡ ሳዲዮ ማኔ - ሴኔጋል እና ሊቨርፑል

ሳዲዮ ማኔ
አጭር የምስል መግለጫ የሊቨርፑል የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች እና የዓመቱ በተጫዋቾች የተመረጠ ምርጥ ተጫዋች ሆኗል

የሴኔጋልና ሊቨርፑል ኮከብ የሆነው ሳዲዮ ማኔ 2017 የውድድር ዓመትን በጥሩ መልኩ አሳልፏል። በሌሎች ተጫዋቾች የፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱ ቡድን ውስጥ እንዲካተት ከመመረጡም በላይ የባለንዶር ዕጩ ከሆኑ ሁለት አፍሪካዊያን አንዱ ሆኗል።

ሴኔጋል ከአውሮፕያኑ ከ2002 በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫ እንድታልፍም ትልቅ ዕገዛ አድርጓል ።

ለሴኔጋል ብዙ ጎል ባስቆጠረበት የውድድር ዓመት በዘጠኝ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ አራት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ከውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ማኔ ያለውን የኳስ ችሎታ፣ ፍጥነት እና ጎል የማስቆጠር ብቃት ለማሳየት ችሏል።

በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ላይ በአፍሪካ ዋንጫ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ላይ ለሴኔጋል ጎል ቢያስቆጥርም ከዚያ በኋላ ግን ነገሮች የተሳኩ አልነበሩም።

በሩብ ፍጻሜው ላይ ከካሜሮን ጋር በነበራቸው ጨዋታ ወሳኟን ፍጹም ቅጣት ምት ስቷል። ካሜሮን ውድድሩን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስታለች።

ተጫዋቹ በሌለበት ከሰባት ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ያሸነፉት እና ከሁለት ውድድሮች ውጭ የሆኑት ሊቨርፑሎች ማኔ ከአፍሪካው ዋንጫው መልስ ባሳያቸው አቋም ደስተኛ ሆነዋል።

ወደ ጋቦን ካቀና በኋላ ማሸነፍ ለተሳናቸው ሊቨርፑሎች ጥሩ ብቃት ላይ የነበሩት ቶተንሃሞች ላይ ባስቆጠራቸው ጎሎች ቡድኑ 2 ለ 0 እንዲያሸንፍ ከማስቻሉም በላይ አርሴናልን ሲያሸንፉም ጎል አስቆጥሯል። በተጨማሪም ኤቨርተን ላይ በሜዳቸውም ሆነ ከሜዳቸው ውጭ እንዲያሸንፉ ያስቻላቸውን ጎሎች ከመረብ አሳርፏል።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ሳዲዮ ማኔ ለተከታታይ ዓመታት ዕጩ የሆነበትን ሽልማት ዘንድሮ ያሳካው ይሆን?

ማኔ የውድድር ዓመቱን በ13 ጎሎች ለማጠናቀቅ ችሏል። ታህሳስና ግንቦት ወሮችን በጉልበት ቀዶ ጥገና ምክንያት ከሜዳ ርቆ ቢያሳልፍም በፕሪሚር ሊጉ ብዙ ጎሎችን ያስቆጠረበት የውድድር ዓመት ሆኗል።

ማኔ አነስተኛ ቁጥር ያለው ጨዋታ ቢያደርግም ከኩቲንሆ ጋር የውድድር ዓመቱን የክለቡ ጥምር ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን አጠናቋል። በዚህም በስምንት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ቡድኑ በምርጥ አራት ውስጥ እንዲያጠናቅቅ በማድረግ ክለቡን የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ አድርጓል።

የሊቨርፑል የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች እና በተጫዋቾች የተመረጠ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመሆንም ለድርብ ድል በቅቷል።

በአዲሱ የውድድር ዓመት በሶስት ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን አስቆጥሯል። ማኔ ሲኖር ሊቨርፑል በየጨዋታው በአማካይ 2.2 የሊግ ጎሎችን የሚያስቆጥር ሲሆን ያለማኔ ደግሞ 1.6 ጎሎችን ብቻ ያስቆጥራል።

የ25 ዓመቱ ተጫዋች ከሜዳ በሚርቅበት ወቅት ክለቡ ውስጥ ያለው ተጽእኖ ምን ያህል እንደሆነ እየታወቀ ነው። ለሶስተኛ ጊዜ ዕጩ የሆነበትን የቢቢሲ የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች ውድድርን ለማሸነፍም ተስፋ አድርጓል።

ይህን በመጫን የሚፈልጉትን ተጫዋች መምረጥ ይችላሉ።