የቢቢሲ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ዕጩ፡ ቪክተር ሞሰስ - ናይጄሪያ እና ቼልሲ

ቪከቶር ሞሰስ
አጭር የምስል መግለጫ "አዲሱ ውል ለቪክቶር ጠንካራ ሰራተኛነት እና ለስኬት ላለው ቁርጠኝነት ምስክር ነው"

ቪክተር ሞሰስ ዞር በማለት የተጫዋችነት ህይወቱን ሲመለከት የ2016-17 የውድድር ዓመት በእጅጉ የተለየ ዓመት እንደሚሆንለት ጥርጥር የለውም።

የ26 ዓመቱ ተጫዋች ከዓመታት ያልተረጋጋ እና በውሰት የተሞላ የእግር ኳስ ህይወት በኋላ ትክክለኛ ቦታውን በስታምፎርድ ብሪጅ አግኝቷል። በዚህም ፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ባነሳው የቼልሲ ቡድን ውስጥ ወሳኝ መሆኑን አስመስክሯል።

በአርሴናል እና በሊቨርፑል ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ የቼልሲው አስልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ለሃል ሲቲ ጨዋታ አሰላለፋቸውን ወደ 3-4-3 ቀይረወዋል። በዚህም ናይጄሪያዊውን ባለተለመደ መልኩ የቀኝ ተመላላሽ በማድረግ ያሰለፉበት ጨዋታ በቪክተር ሞሰስ ሁሌም የሚታወስ ነው።

ይህ ጨዋታ ከሶስት ዓመታት በኋላ ለቼልሲ ቋሚ ሆኖ የተሰለፈበት የመጀመሪያው ጨዋታው ነው። በተፈጥሮ ያለውን የማጥቃትና የመከላከል ብቃት ተጠቅሞ አስገራሚ ብቃት በማሳት የጨዋታው ኮከብ ለመሆንም በቅቷል።

የሃል ሲቲው ድል ቼልሲ በተከታታይ 13 ጨዋታዎችን በማሸነፍ የራሱን ክብረ ወሰን የተጋራበት ጅማሬ ሆኗል። ሚያዚያ ላይ ጉዳት እስካጋጠመው ድረስም ሞሰስ 22 ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ቋሚ ተሰላፊ ሆኖ ተጫውቷል።

ቼልሲን ለመጀመሪያ ጊዜ በ2012 ከተቀላቀለ በኋላም ዳጎስ ያለ ገንዘብ የሚያስገኝለትን ውል ለመፈረም ችሏል።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ቪክተር ሞሰስ ከጄይ ጄይ ኦኮቻ በመቀጠል የቢቢሲን ሽልማት ያሸነፈ ናይጄሪያዊ ይሆናል?

ይህ የሆነው በቅድመ ውድድር ወቅት ኮንቴ ማንም ያላየውን የቪክተርን ችሎታ በማየት ዕድል ስለሰጡት ነው። የተሰጠውን ዕድል እና ያለውን ብቃት፣ ጥንካሬ እና ፍጥነት ተጠቅሞም የ26 ዓመቱ ተጫዋች ብቃቱን ለማሳየት ችሏል።

"አዲሱ ውል ለቪክተር ጠንካራ ሰራተኛነት እና ለስኬት ላለው ቁርጠኝነት ምስክር ነው" ሲሉ የቼልሲ የቴክኒክ ዳይሬክተር ሆኑት ማይክል ኤሜናሎ ተናግረዋል።

ቼልሲ በአርሴናል መሸነፉን ተከትሎ ከፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ በተጨማሪ ቪክተር የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ የብር ሜዳሊያ ቢያገኝም ተጫዋቹ በጨዋታው ቀይ ካርድ አግኝቷል።

ቪክተር በዚህ የውድድር ዓመት ሶስት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ብቻ ነው ያደረገው። የመጀመሪያው ጨዋታ ላይ ካሜሮንን 4 ለ 0 ሲያሸንፉ ጎል ለማስቆጠር ችሏል። በዚህም ካሜሮን ከዓለም ዋንጫ ውጭ ስትሆን ናይጄሪያ ደግሞ ወደ ሩሲያው የዓለም ዋንጫ አልፋለች።

ሱፐር ኤግሎችን ለዓለም ዋንጫ ያበቃው ቪክቶር ሞሰስ፤ ጄይ ጄይ ኦኮቻ በ2004 የቢቢሲን ሽልማት ካሸነፈ በኋላ ውድድሩን የሚያሸንፍ የመጀመሪያው ናይጄሪያዊ ይሆናል?

ይህንን በመጫን የሚፈልጉትን ተጫዋች መምረጥ ይችላሉ።