የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሳዑዲን እየጎበኙ ነው

ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳላህ እና ኢማኑኤል ማክሮን Image copyright AFP/Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳላህ እና ኢማኑኤል ማክሮን ሃሙስ በሪያድ ተገናኝተዋል

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሳዑዲ ያልተጠበቀ ጉብኘት በጀመሩበት ወቅት የሌባኖስ መረጋጋት አስፈላጊ ስለሆነ በጉዳዩ ላይ ትኩረት እስጣለው በለዋል።

ባሳለፍነው ቅዳሜ የሌባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳድ ሃሪሪ ሪያድ ሆነው ለህይወቴ ሰግቻለው በማለት በፍቃዳቸው ሥራ መልቀቃቸው ይታወሳል።

እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ የሳዑዲ ባለስልጣናት ጫና ሳያሳድሩባቸው አልቀረም ተብሏል።

ማክሮን በየመን ስላለው ቀውስ ከሳውዲ ባለስልጣናት ጋር እወያያለው ብለዋል።

የሳውዲ መራሹ ጥምር ኃይል በየመን የመጓጓዣ ዘዴዎችን ከዘጋ በኋላ የእርዳታ ቁሶችን ወደ የመን ማስገባት እንዳልቻለ የተባበሩት ምንግሥታት አስታውቋል።

ባለፈው ሰኞ የሁቲ አማጺያን ወደ ሳዑዲ ሚሳዬል ከተኮሱ በኋላ ነበር ጥምር ኃይሉ ወደ የመን የሚደረጉ የአየር፣ የየብስ እና የምድር መጓጓዣ ዘዴዎችን በሙሉ ዝግ ያደረገው።

ሳዑዲ ለጥቃቱ በኢራን የሚደገፈውን የሌባኖስ ሚሊሻ ቡድን ሄዝቦላህን ተጠያቂ ታደርጋለች።

የመን ''የዓለማችን አስከፊው ረሃብ'' ተጋርጦባታል

ትናትን ሳዑድ አረቢያ በሌባኖስ የሚገኙ ዜጎቿ በአስቸኳይ ሃገሪቱን ጥለው እንዲወጡ አሳስባለች።

ማክሮን ወደ ሳውዲ ከማቅናታቸው በፊት በተባበሩት አረብ ኢሚሬት ባደረጉት ንግግር ከሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳላህ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው እንደሚወያዩ ተናግረዋል።

''በሌባኖስ መረጋጋት እና አንድነት'' ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው እንደሚወያዩ አሳውቀዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳነት ከቀድሞ የሌባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሪሪ ጋር መነጋገራቸውን ቸምረው ተናግረዋል።

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የሃሪሪ ስልጣን መልቀቀ በሌባኖስ የለመረጋጋትን ፈጥሯል

ሃሪሪ ሳዑዲ ሆነው በሰጡት መግለጫ በፍቃዴ ስልጣን መልቀቅ የፈለኩት በስልጣን መቆየቴ ለህይወቴ አስጊ ስለሆነ ነው ብለዋል።

በሰጡት መግለጫ በሌባኖስ ጠንካራ ወታደራዊ አቋም ያለውን ሄዝቦላህን ኮንነዋል።

እአአ በ2005 የሃሪሪ አባት እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራፊክ ሂዝቦላህ አጥምዶታል በተባለ ቦንብ ተገድለዋል።

በሌላ በኩል ሄዝቦላህ ሃሪሪ ከስልጣናቸው የለቀቁት በሳዑዲ አረቢያ ግፊት ነው ይላል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ