ሞሃመድ ሳላህ - ግብጽ እና ሊቨርፑል
የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።

ሞሃመድ ሳላህ እ.አ.አ ከ2008 በኋላ የቢቢሲን ሽልማት የሚያሸንፍ ግብጻዊ ይሆን?

ግብጽን ወደ ሩሲያው የዓለም ዋንጫ ካደረሷት ሰባት ጎሎች አምስቱን ያስቆጠረው ሳላህ ነው። በ2017ቱ የአፍሪካ ዋንጫም አስገራሚ ብቃት አሳይቷል። ግብጽ ካስቆጠረቻቸው አምስት ጎሎች በአራቱ ላይ በመሳተፉ የውድድሩ ምርጥ ቡድን ውስጥ ለመካተትም ችሏል።