በዚህ ሳምንት በርካታ ኹነቶችን ያሳለፈችው አህጉረ አፍሪካን እስኪ ከብዙ በጥቂቱ በፎቶግራፍ እንቃኛት

እነሆ አፍሪካ በዚህ ሳምንት የነበራት ጉዞ በአፍሪካ ሲገለጥ

Image copyright Empics

ዕለተ ረቡዕ በደቡብ አፍሪካዋ ፕሪቶሪያ ከተማ የተነሳው ይህ ፎቶ አንድ የራግቢ ጨዋታ አድናቂ የሆነች ሴት ደቡብ አፍሪካ የ2023 የዓለም የራግቢ ዋንጫ አስተናጋጅነትን በፈረንሳይ በመነጠቋ ምክንያት የተሰማትን ሃዘን ስትገልፅ ያሳያል።

Image copyright AFP

በሌላ ፅንፍ ደግሞ በሞሮኮዋ ማራኬሽ ከተማ ለሩስያው ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አይቮሪ ኮስትን በማሸነፍ ማለፉን ያረጋገጠውን የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ድል ሞሮኳዊያን ሲያጣጥሙ

Image copyright EPA

ባለፈው ሳምንት በኢኳቶሪያል ጊኒ በነበረው ምርጫ አንዲት ሴት ድምጿን ስትሰጥ

Image copyright AFP

በኬንያ መዲና ናይሮቢ ሁለት ወታደሮች ከዝናብ ራሳቸውን በዣንጥላ ጠልለው የሃገሪቱን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ሲጠብቁ ነበር። ፍርድ ቤቱ በድጋሚ የተደረገው የሃገሪቱ ምርጫ ፍትሃዊ ስላልነበር በህግ ይታይልን የሚሉ ሰዎችን አቤቱታ እየተመለከተ ይገኛል።

Image copyright AFP

ወደ ደቡባዊ የአህጉሪቱ ክፍል ስንጓዝ ደግሞ በዚምባብዌ ከተማ ሃራሬ የሃገሪቱ ጦር ስልጣን መቆጣጠሩን የሰማነው በዚህ ሳምንት ነበር። የጦር ኃይሉ ስልጣን የጠቆጣጠርኩት በሙጋቤ ዙሪያ ያሉ የጦር ወንጀለኞችን ለማስወገድ እንጂ መፈንቅለ-መንግሥት እየፈፀምኩ አይደለም ሲል ተሰምቷል።

Image copyright AFP

ጋናዊቷ ሞዴል ናና አዶ እሁድ ዕለት በናይጂሪያ ከተማ ሌጎስ በተካሄደው የአፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት ላይ እንዲህ አጊጣ ተገኝታ ነበር።

Image copyright AFP

ባለፈው ማክሰኞ በአይቮሪ ኮስት ዋና መዲና አቢጃን የተነሳው ይህ ፎቶግራፍ ቼ ጉቬራ (ግራ) እንዲሁም የቀድሞውን የሊቢያ መሪ ሙአማር ጋዳፊን ባዘለው ግድግዳ በኩል ብስክሌተኛው ሲያልፍ ያስመለክተናል።

Image copyright EPA

አዲሱ የዘይትዝ የጥበብ ማሳያ በኬፕ ታውን ከተከፈተ ወዲህ በጎብኚዎች መጨናነቅ ጀምሯል። ምስሉ ላይ የሚታዩት ሴቶች የናይጄሪያዊውን አርቲስት ታይዬ ኢዳሆር ስራዎች ሲመለከቱ በመቅረፀ ምስል ሊያዙ ችለዋል።

በቢቢሲ ዙሪያ