በጋርዝ ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ ኦዚል፣ ሳንቼዝ፣ ሳላህ እና ፖግባ ተካተዋል

Image copyright BBC Sport

ማንችስተር ሲቲ ያለመሸነፍ ግስጋሴውን በማስቀጠል ሌስተር ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፎ በስምንት ነጥብ ልዩነት ፕሪሚየር ሊጉን እየመራ ይገኛል።

ሆዜ ሞሪኒዮ ኒውካስትልን አስተናግደው 4 ለ 1 ማሸነፍ ሲችሉ አርሰናል በሰሜን ለንደን ደርቢ እአአ ከ2014 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቶተነሃምን ኢሚሬትስ ላይ ማሸነፍ ችሏል።

ሞሐመድ ሳላህ ደንቅ ጎል ባስቆጠበት ጨዋታ ሊቨርፑል ሳውዝሃምፕተንን 3 - 0 አሸንፏል። ኤቨርተን ከኋላ ተነስቶ ከክሪስታል ፓላስ ጋር አቻ መለያየት ችሏል።

ቼልሲ ዌስት ብሮምን 4 ለ 0 ረምርሞታል።

ጋርዝ ክሩክስ ለኔ የሳምንቱን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ 11 እነዚህ ናቸው ይላል።

ግብ ጠባቂ- ኡሩዌልዩ ጎሜዝ (ዋትፎርድ)

Image copyright Getty Images

ጎሜዝ አምስት ኳሶችን በመያዝ ዌስት ሃም ጎል ሳይቆጠርበት ጨዋታው እንዲያጠናቅቅ አድርጓል።

የግብ ጠባቂ ዋና ተግባር መረቡን ሳያስደፍር ነጥብ ይዞ መውጣት ነው ይህን ያደረገ ግብ ጠባቂ ደግሞ ከፍተኛ ደስታ ይሰማዋል።

ጎሜዝ ማርኮ አርናውቶቪች ሁለት ጊዜ በተከታታይ ያደረገበትን አደገኛ ሙከራ ማዳን በመቻሉ ደስታ እንደሚሰማው እርግጥ ነው።

ተከላካይ- ክርስቲያን ካባሲል (ዋትፎርድ)

Image copyright Getty Images

በእዚህ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በርካታ ግሩም የሆኑ የመከላከለ ብቃቶች አይቻለው ግን እንደ ክርስቲያን ካባሲል ያስደነቀኝ የለም።

በተደጋጋሚ አደገኛ ኳሶችን ከግብ ክልል ሲያርቅ ነበር። የዌስት ሃሙ ማኑኤል ላንዚኒ ጎል ለማስቆጠር ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም ክርሰቲያን ካባሲል ግን ኳስ ሲያስጥለው ነበር።

ተከላካይ- ሾክደራን ሙስጣፊ (አርሰናል)

Image copyright Getty Images

በጨዋታ ሂደት ላይ የተከላካዮች ብቃት ጫፍ ሲደርስ ምን ይፈጠራል? የግብ ክልላቸውን አስጠብቀው ጎል ማስቆጠር ይችላሉ። ሙስጣፊም ይህን ማድረግ ችሏል።

ሙስጣፊ ጎሏን ሲያስቆጥር ከጨዋታ ውጪ ሆኖ ሊሆን ይችላል። የቪዲዮ ማስረጃውም እሱን ነው የሚያሳየው ግን ይሄ የሙስጣፊ ችግር ሊሆን አይችልም። ጎሏ አጠቃላይ ውጤቱን መቀየር ስለማትችል ስፐርሶችም ለመሸነፋቸው እንደምክንያት ሊያቀርቧት አይችሉም።

ተከላካይ- ቪንሰንት ኮምፓኒ (ማንችስተር ሲቲ)

Image copyright Getty Images

የማይዋዥቅ አቋም ያለው፣ አስተማማኝ እና በሁሉም ተፈላጊ የሆነ ተከላካይ ነው ሲሉ ብዙዎች ይስማሙበታል። እኔ ከዚህ በላይ ምን ልጨምር እችላለሁ?

አማካይ- ኬቪን ዲ ብሩይን (ማንችስተር ሲቲ)

Image copyright Getty Images

ከግንቦት በፊት የፕሪሚያር ሊጉን ምርጥ ተጫዋች አሳውቅ ብባል ያለምንም ማንገራገር ኬቪን ዲ ብሩይንን እመርጥ ነበር።

ይህን ምርጫዬን ማንም የሚቃወም አይመስለኝም።

ከማንችስተር ሲቲ እና ከኬቪን ዲ ብሩይን እየተመለከትን ያለነው ጥበብ ነው።

አማካይ- ፖል ፖግባ (ማንችስተር ዩናይትድ)

Image copyright Getty Images

ስለ ጸጉር አቆራረጡ እና የዳንስ ኤግዚቢሽኑ ጊዜ የለኝም። እኔ የምወድለት ግን በኳስ ችሎታው የሚፈጥራቸውን አስገራሚ ትዕይንቶች ነው።

ፖል ፖግባ ወደ ሜዳ መመለሱ ማንችስተር ዩናይትድ ኒውካስትልን በሰፊ የጎል ልዩነት እንዲያሸንፍ ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል።

ፈረንሳዊው እግርኳሰኛ ከኒውካስትል ጋር በነበረው ጨዋታ ያሳየውን አይነት ብቃት ከትላልቅ ቡድኖች ጋርም እንደሚደግመው እርግጠኛ ነኝ።

አማካይ- ሜሱት ኦዚል (አርሴናል)

Image copyright Getty Images

በሰሜን ለንደኑ ደርቢ ሜሱት ኦዚል ለቡድኑ ትልቅ ዋጋ ከፍሏል። ኦዚል ባሳየው ብቃት ደጋፊዎች ከመቀመጫቸው ተነስተው አድናቆታቸውን ገልጸውለታል።

የአርሰናል ደጋፊዎች ብዙ ጊዜ ቬንገር እና ኦዚል ላይ ቅሬታዎችን ያቀርባሉ እኔ ግን እግር ኳስን ጠንቅቀው የሚያውቁ ግለሰቦች ይህ ይገባቸዋል አልልም።

አማካይ ሞሐመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)

Image copyright Getty Images

ይህ ተጫዋች በአሁኑ ሰዓት የሚያቆመው የለም። ሳላህ በመጀመሪያዎቹ 12 የፕሪሚያር ሊግ ጨዋታው 11 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ሳላህ ወደ ሊጉ ሲመጣ ጥሩ ጊዜ ሊያሳልፍ እንደሚችል ገምቼ ነበር በዚህ ብቃት ይህን ሁሉ ጎል ማስቆጠር ይችላል ብዬ ግን አልገመትኩም። የመጀመሪያዋ ጎል አስደናቂ ነበረች።

የሳዲዮ ማኔ፣ የሮቤርቶ ፌርሚኖ፣ የኩቲኒሆ እና ሳላህ ጥምረት የትኛውንም ቡድን መፈተን የሚችል ነው።

የፊት መስመር

አጥቂ- ኤደን ሃዛርድ (ቼልሲ)

Image copyright Getty Images

ሃዛርድ እንደ ተደራቢ አጥቂ ሆኖ ሲጫወት አይቼው አላውቅም በአሁኑ ሰዓት ግን ይህን ሃላፊነት ይዞ ነው ወደ ሜዳ የሚገባው።

ከአልቫሮ ሞራታ ጋር ያለው ጥምረት እጅግ ውጤታማ እያደረገው ነው።

አጥቂ- ካለም ዊልሰን (ቦርንማውዝ)

Image copyright Getty Images

በዘንድሮ የፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ዊልሰን በአንድ ጨዋታ ሶስት ጎሎችን ያስቆጠረ የመጀመሪያ እንግሊዛዊ ኖኗል።

መቼም ዊልሰን ሃትሪክ ሰርቶ በምርጥ ቡድን ውስጥ ባላካትተው አግባብ አይሆንም።

በአንድ ጨዋታ ሶስት ጎሎችን ማስቆጠር ቀላል አይደለም በተለይ ደግሞ ለወራት በጉዳት ከሜዳ ርቆ ከተመለሰ በኋላ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

አጥቂ- አሌክሲስ ሳንቼዝ (አርሴናል)

Image copyright Getty Images

ሳንቼዝ የትኛውንም አይነት ኳስ ለመቀማት ጥረት ሲያደርግ፣ ኦዚል በተነሳሽነት ሲጫወት እና ሙስጣፊ የባላንጣ ቡድን አጥቂዎችን አላፈናፍንም ሲል አርሴናል ልዩ ቡድን ይሆናል።

ቶተንሃሞች ነጥብ ለማግኝት ወደ ሜዳ ሲገቡ አርሴናሎች ግን የሞት ሽረት ያክል ትግል ነው ያደረጉት።

ቺሊያዊው አጥቂ አሁን አስገራሚ ችሎታ ላይ ይገኛል ይህም አርሴናሎች ከጨዋታው የሚገባቸውን ሶስት ነጥብ ይዘው እንዲወጡ አስችሏቸዋል።