ሙጋቤ ለፓርላማው በሚቀርበው ክስ ከስልጣን ሊወርዱ ይችላሉ

ሙጋቤ Image copyright EPA / The Herald
አጭር የምስል መግለጫ ሙጋቤ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ግፊት እየተደረገባቸው ነው

የዚምባብዌ ገዢ ፓርቲ ዛኑ ፒኤፍ ሮበርት ሙጋቤ ላይ ክስ በመመስረት ከሥልጣን ሊያነሳቸው ነው።

ዚምባብዌ እንዴት ሰነበተች?

የፓርቲው ኃላፊዎች ሙጋቤን ከሥልጣን ለማውረድ ዛሬ ክስ ለፓርላማው እንደሚቀርብ እና በሁለት ቀናት ውስጥ ከሥልጣናቸው እንደሚወርዱ ተናግረዋል።

ለፓርላው በሚቀርበው 'ሞሽን' ላይ የ93 ዓመቱ ሮበርት ሙጋቤ ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤን አግባብ ባልሆነ መልኩ ሕገ-መንግስታዊ ሥልጣን እንዲቆጣጠሩ አስችለዋል የሚል ክስን ያካትታል።

ሙጋቤን በቁም እስር ላይ ያቆየው ጦር በበኩሉ ሙጋቤ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ከነበሩት ኤመርሰን ምንጋግዋን ጋር ይወያያሉ ብሏል።

ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንታቸውን ታማኝ አይደሉም በማለት ከስልጣን ማባረራቸው ይታወሳል።

ሙጋቤ ታማኝ አይደሉም ያሏቸውን ምክትላቸውን ከስልጣን አነሱ

ጦሩ ቀጣይ የሙጋቤ እጣፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችልም አቅደናል ብሏል።

እሁድ ምሽት ሙጋቤ በሰጡት መግለጫ ስልጣን በፍቃዳቸው ይለቃሉ ተብሎ ቢጠበቅም በቀጣዩ አጠቃላይ ስበሰባ ላይ ፓርቲውን እየመሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

"እምቢተኛው" ሙጋቤ ከስልጣኔ አልወርድም አሉ።

ሙጋቤ የተመሰረቱባቸው ክሶች ምንድን ናቸው?

ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ሙጋቤ ስልጣን እንዲለቁ ቀነገደብ አስቀምጦላቸው ነበር። ሙጋቤ ግን ፓርቲው እና ሌሎች አካላት ስልጣን እንዲለቁ ግፊት ቢያደርጉባቸውም ስልጣናቸው ላይ የሙጥኝ ብለዋል።

የፓርላማ አባል የሆኑት ፖል ማንግዋን ''ሙጋቤ ግትር የሆነ አቋም ነው የያዙት። የህዝቡን ድምጽ መስማት አይፈልጉም'' ሲሉ ተናግረዋል።

ሙጋቤ ከቀረቡባቸው ክሶች መካከል ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ መሪ ሳይሆኑ ህግ-መንግሥታዊ ስልጣን እንዲኖራቸው አስችለዋል የሚለው ይገኝበታል። ግሬስ ሙጋቤ የመንግሥት ስራተኞችን እና የቀድሞውን ምክትል ፕሬዝዳንት በአደባባይ ይሳደባሉ እንዲሁም የሃገሪቱን የጦር ኃይል ያንቋሽሻሉ የሚሉ ክሶች ቀርበውባቸዋል ሲሉ ፖል ማንግዋን ያስረዳሉ።