የሙጋቤ ሕይወት በምስል ሲቃኝ

ሮበርት ሙጋቤ በአንድ የሚሽን ት/ቤት ከተማሩ በኋላ በአስተማሪነት የሠሩ ሲሆን ከዛም ከፎርት ሃሬ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ለሥራ ወደ ጋና አመሩ። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ሮበርት ሙጋቤ በአንድ የሚሽን ት/ቤት ከተማሩ በኋላ በአስተማሪነት የሠሩ ሲሆን ከዛም ከፎርት ሃሬ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ለሥራ ወደ ጋና አመሩ።
ሳሊ ሃፍሮን (ግራኝ) ሮበርት (ቀኝ) Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ከዚያም ከሳሊ ሃፍሮን ጋር በአውሮፓውያኑ 1961 ትዳር መሠረቱ። በዚያን ወቅት ሳሊ ከሙጋቤ በተሻለ በፖለቲካው ዓለም የሚሳተፉ የነበረ ሲሆን ኋላ ላይ ግን ጥቁር ብሔርተኞች ሙጋቤን አጯቸው። ከዚያም የሮዴሲያ መንግሥት ሙጋቤን ወደ እሥር ቤት ወረወራቸው። የገዛ ልጃቸውን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይም እንዳይገኙ አደረጋቸው።
ጆሽዋ ንኮሞ (ቀኝ) Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በ1974 ከእሥር የተፈቱት ሙጋቤ ከጆሽዋ ንኮሞ (ቀኝ) ጋር በመሆን የዚያን ጊዜ የነበረውን የነጭ አገዛዝ በጉሬላ ጦርነት ዋጋት ጀመሩ።
ለጥቆም በሰላመዊ መንገድ ትጥቅ ለመፍታት ተስማምተው ዚምባብዌ ነፃ ከወጣች በኋላ የተደረገውን የመጀመሪያ ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ በማሸነፍ በ1980 ሥልጣን ያዙ። Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ለጥቆም በሰላመዊ መንገድ ትጥቅ ለመፍታት ተስማምተው ዚምባብዌ ነፃ ከወጣች በኋላ የተደረገውን የመጀመሪያ ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ በማሸነፍ በ1980 ሥልጣን ያዙ። ከ10 ዓመታት የስደት ኑሮ በኋላም ጠቅላይ ሚንስትር በመሆን ሃገራቸውን ማስተዳደር ጀመሩ። ሁሉን አቀፍ መንግሥትም መሠረቱ።
በመጀመሪያዎቹ የሥልጣን ዕድሜያቸው ሙጋቤ ከዓለም መሪዎች አድናቆትን ማግኘት ቻሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆኑት የኩባው ፊደል ካስትሮ በ1986 ዚምባቢዌን ጎበኙ። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በመጀመሪያዎቹ የሥልጣን ዕድሜያቸው ሙጋቤ ከዓለም መሪዎች አድናቆትን ማግኘት ቻሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆኑት የኩባው ፊደል ካስትሮ በ1986 ዚምባቢዌን ጎበኙ።
Margaret Thatcher and Robert Mugabe in 1980 Image copyright PA
አጭር የምስል መግለጫ ሙጋቤ ከያኔዋ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ማርኣጋሬት ታቸር ጋርም የቀረበ ግንኙነት ነበራቸው። ዚምባብዌን በቅኝ ገዝተው ከነበሩ ነⶐች ጋርም በስምምነት መሥራት ጀመሩ።
President Robert Mugabe and his wife Grace leave parliament in their ceremonial car after its official opening, Harare - 22 July 2003 Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የቀድሞ ሚስታቸው ከሞቱ ጥቂት ዓመታት በኃላ የቢሮ ፀሐፊያቸው ከነበሩት ግሬስ ማሩፉ ጋር በ1996 ጋብቻ ፈፀሙ። ከጋብቻው በፊት ግን ከግሬስ ሁለት ልጆችን አፍርተው ነበር። በ1990ዎቹ በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ በነበረው ጦርነት ጣልቃ በመግባታቸው ምክንያት የዚምባብዌ ምጣኔ ሃብት መዳከም አሳየ።
Schoolchildren by a farm 40km east of Harare, renamed "Black Power Farm" by war veterans who have taken it over - 21 June 2000 Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በ1997 የዩናይትድ ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር አነጋጋሪውን የዚምባብዌ የመሬት ፖሊሲን በገንዘብ እርዳታ አልደግፍም ማለታቸውን ተከትሎ የሙጋቤ ደጋፊ የሆኑ ሚሊሺያዎች በነጮች የተያዙ መሬቶችን መውረር ጀመሩ።
Posters for President Robert Mugabe are covered with graffiti for the opposition Movement for Democratic Change in Harare, Zimbabwe - 27 June 2008 Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የሙጋቤ ተዋዳጅነት በተለይ ደግሞ በከተሞች አካባቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣት ጀመረ። በ2008 በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ተሸነፉ፤ በሁለተኛው ዙር ምርጫ ተቃዋሚ ፓርቲው ራሱን ከምርጫው ማግለሉን ተከትሎ ቢያሸንፉም ቅሉ።
ከአሜሪካና አውሮፓ ሕብረት የተጣለባቸውን ቅጣት ተከትሎ ሙጋቤ ፊታቸውን ወደ ምስራቅ ማዞር ጀመሩ። ከቻይና ጋርም ጥብቅ የኢንቨስትመንት ግንኙነት መመሥረት ያዙ። ልጃቸው ቦና (መሃል) የትምህርት ሕይወቷ በሆንክ ኮንግና ሲንጋፖር እንዳሳለፈችም ይታወቃል። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ከአሜሪካና አውሮፓ ሕብረት የተጣለባቸውን ቅጣት ተከትሎ ሙጋቤ ፊታቸውን ወደ ምስራቅ ማዞር ጀመሩ። ከቻይና ጋርም ጥብቅ የኢንቨስትመንት ግንኙነት መመሥረት ያዙ። ልጃቸው ቦና (መሃል) የትምህርት ሕይወቷ በሆንክ ኮንግና ሲንጋፖር እንዳሳለፈችም ይታወቃል።
የሙጋቤ ፓርቲ የሆነው ዛኑ ፒኤፍ በ2013 ምርጫ ማሸነፍ ቻለ። ነገር ግን የጥሬ ገንዘብ እጥረት የሃገሪቱን ዜጎች ለተቃውሞ ወደ ጎዳናዎች እንዲወጡ ዳረጋቸው። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የሙጋቤ ፓርቲ የሆነው ዛኑ ፒኤፍ በ2013 ምርጫ ማሸነፍ ቻለ። ነገር ግን የጥሬ ገንዘብ እጥረት የሃገሪቱን ዜጎች ለተቃውሞ ወደ ጎዳናዎች እንዲወጡ ዳረጋቸው።
ሁሌም ከሙጋቤ ጎን የማይለው የሃገሪቱ ጦር ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ ሥልጣን ለመረከብ ማኮብኮባቸውን በተረዳ ጊዜ ግን ፊቱን አዞረባቸው። ጦር ኃይሉ በአውሮፓውያኑ ኅዳር 15/2017 ሃገሪቱን ተቆጣጠረ። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ሁሌም ከሙጋቤ ጎን የማይለው የሃገሪቱ ጦር ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ ሥልጣን ለመረከብ ማኮብኮባቸውን በተረዳ ጊዜ ግን ፊቱን አዞረባቸው። ጦር ኃይሉ በአውሮፓውያኑ ኅዳር 15/2017 ሃገሪቱን ተቆጣጠረ።
የ93 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው ሙጋቤ በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣን መልቀቃቸውን ኅዳር 13/ 2010 (ኅዳር 21/2017) አሳወቁ። Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ሙጋቤ ከሥልጣን አልወርድም ማለታቸውን ተከትሎ ተቃውሞች ሲበረቱ የሃገሪቱ ፓርላማ በግድ ሊያወርዳቸው እንቅስቃሴ ጀመረ። ነገር ግን ነገሮች ሌላ ቅርፅ ከመያዛቸው በፊት የ93 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው ሙጋቤ በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣን መልቀቃቸውን ኅዳር 13/ 2010 (ኅዳር 21/2017) አሳወቁ።

All pictures copyright

ተያያዥ ርዕሶች