የአርጀንቲና ሰርጓጅ የጠፋበት አካባቢ ፍንዳታ ተሰምቷል

The ARA San Juan disappeared last Wednesday Image copyright Reuters

ሳን ሁዋን የተሰኘው የአርጀንቲና ሰርጓጅ መርከብ 44 ሰዎችን አሳፍሮ ከተልዕኮው ወደ ዋና መቀመጫው እየተመለሰ ነበር ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ደብዛው የጠፋው።

መርከቡ የጠፋበት አካባቢ የተሰማው ፍንዳታ ግን በሕይወቱ ሊኖሩ ይችላሉ ተብሎ የተገመቱት አራባ አራቱ የመርከቧ አባላትን የማግኘት ተስፋ አጨልሞታል።

በደቡብ አትላንቲክ የተሰማው ፍንዳታ አንድ ጊዜ የተሰማ ሲሆን ኒውክሌር ያልሆነ ግን በጣም ኃይለኛ ድምፅ የነበረው እንደሆነ ማወቅ ተችሏል። አሜሪካም ተመሳሳይ ፍንዳታ በተመሳሳይ ቦታ መሰማቱን አሳውቃለች።

44 ሰዎችን የያዘው የአርጀንቲና ሰርጓጅ መርከብ ደብዛው ጠፍቷል

ሰርጓጅ መርከቡ ከጠፋበት ጊዜ ጀምሮ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደምና ሩስያን ጨምሮ ከ12 በላይ ሃገራት አሰሳቸውን እያጧጧፉት ይገኛሉ።

የአርጀንቲና ባሕር ኃይል ዜናውን ትላንት ይፋ ያድርገው እንጂ ፍንዳታው የተሰማው መርከበኞቱ ከጠፉ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ እንደነበር ማወቅም ተችሏል።

ባሕር ኃይሉ አክሎም የፍለጋውን ትኩረት ፍንዳታው በተሰማበት አካባቢ እንደሚያደርግ ገልጧል።

Image copyright EPA

የፍንዳታው ዜናው ከተሰማ በኋላ የመርከበኞቹ ቤተሰቦች ሃዘንና ቁጣቸው እየገለፁ እንደሆነ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።

የጠፉት ሰዎች ቤተሰብና አዝማድ የሆኑት ሰዎች ባሕር ኃይሉ የማይሆን ተስፋ እየሰጠን ነው ሲሉ ወቅሰዋል። ሌሎች ደግሞ በጦር ኃይሉ የሚስተዋለው ሙሰኝነት የሰርጓጅ መርከቡ አባላትን አደጋ ላይ ጥሏል ሲሉ የአርጀንቲና መንግሥትን ይወቅሳሉ።

ክላሪን ለተሰኘው የሃገሪቱ ጋዜጣ ቃሉን የሰጠ አንድ ግለሰብ "ወንድሜን ገደሉት። በነሱ ዝርክርነት ምክንያት ወንድሜ ሞተ" ሲል ተሰምቷል።

ከጠፉት መርከበኞች የአንዱ አባት የሆኑ ግለሰብም ለአንድ የራዲዮ ጣቢያ የሃገሪቱ ባሕር ኃይል ሁሉም መርከበኞች በተፈጠረው ፍንዳታ ምክንያት መሞታቸውን እንደነገሩት ተናግሯል።

43 ወንዶችና የ35 ዓመቷን የአርጀንቲና የመጀመሪያ የሰርጓጅ መርከብ ባልደረባ የሆነቸውን ኤልያን ማርያን አሳፍሮ የተጓዘው መርከብ የመገኘቱ ነገር ተስፋ ሰጭ ባይሆንም ፍለጋው ግን አሁንም ቀጥሏል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ