በግብጽ መስጊድ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 235 ሰዎች ሞቱ

ታጣቂዎቹ በአል-አሪሽ አቅራቢያ የሚገኝን መስጊድ ኢላማ አድርገዋል Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ታጣቂዎቹ በአል-አሪሽ አቅራቢያ የሚገኝን መስጊድ ኢላማ አድርገዋል

ተጠርጣሪ ታጣቂዎች በግብጽ ሰሜናዊ ሲናይ ክልል የቦምብና የተኩስ ጥቃት በመሰንዘር 235 ሰዎች መግደላቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የዓይን እማኞችም በአል-አሪሽ አቅራቢያ በቢር አል-ኣቤድ ከተማ የሚገኘው አል-ራውዳ በአርብ ጸሎት ጊዜ ኢላማ መደረጉን አረጋግጠዋል።

አሶሺየትድ ፕሬስ በበኩሉ የአካባቢውን ፖሊስ በመጥቀስ ታጣቂዎቹ በአራት መኪኖች በመምጣት በምዕመናኑ ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ገልጿል።

ግብጽ ከአውሮፓውያኑ 2013 ጀምሮ የእስላማዊ ሰርጎ ገቦችን ጥቃት ለመመከት እየሰራች ነው።

እስካሁን በሲናይ በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶች ቢፈጸሙም በደም አፋሳሽነቱ ግን ይህ ከፍተኛ ነው።

በጥቃቱ ሌሎች 100 ሰዎችም ተጎድተዋል።

ተያያዥ ርዕሶች