የሳምንቱ ምርጥ አስራ አንድ ተጫዋቾች እኚህ ናቸው

አማካይ - ሞሐመድ ሳላህ (ሊቨርፑል) Image copyright PAUL ELLIS

ማንቸስተር ሲቲ ወደ ሃደርስፊልድ ሜዳ ሄዶ 2 - 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሰንጠረዡን መምራቱን ቀጥሏል። ዩናይትድም ብራይተንን አስተናግዶ 1 - 0 በማሸነፍ ሲቲ ላይ ጫና ማሳደሩን ተያይዞታል። አርሴናል ደግሞ ባለቀ ሰዓት ባስቆጠራት ጎል አራት ውስጥ መግባት ችሏል።

ሊቨርፑል ከቼልሲ 1 አቻ የተለያዩበት ጨዋታና ሳውዝሃምፕተን ኤቨርተንን 4 - 1 የረመረመበት ጨዋታ የሳምንቱ መርሃ ግብር አነጋጋሪ ክስተቶች ነበሩ። ኒውካስል በገዛ ሜዳው 3 - 0 መሸነፉን ሳንዘጋ።

ለማንችስተር ዩናይትድና ቶተንሃም በአጥቂነት ሥፍራ የተጫወተው ጋርዥ ክሩክስ በቅዳሜና አሁድ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ እኚህን ምርጥ አስራ አንደ ተጫዋቾች አሳይቶናል ይላል።

ግብ ጠባቂ - ቤን ፎስተር (ዌስት ብሮም)

Image copyright Getty Images

ፎስተር የቶተንሃሙ አጥቂ ሰን ወደጎል የሰነዘራትን ኳስ ያደነበት መንገድ እጅግ አስደናቂ ነበር። ይህ ጎል ሳይቆጠረበት ለመውጣት የሚጥር ግብ ጠባቂ መለያ ነው።

ፎስተር አራት ንፁህ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን በማዳን ዌስትብሮም ወደ ዌምብሌይ ተጉዞ ከቶተንሃም ጋር ነጥብ ተጋርቶ እንደሚጣ አግዟል።

ተከላካይ - ሉዊስ ሳንክ (ብራይተን)

Image copyright Getty Images

ይህንን ተጫዋች በፕሪሚየር ሊጉ ሲጫወት ባየሁት ቁጥር እጅግ እየወደድኩት መጥቻለሁ።

በዳንክ የተጨረፈችው የአሽሊ ያንግ ኳስ ጎል ሆና ብራይተኖች ጨዋታውን በሽንፈት ቢያጠናቅቁም እንደነበራቸው አቋም ነጥብ ይዘው መውጣት እንደበረባቸው አስባለሁ።

ተከላካይ - ሲዛር አዝፕሊኬታ (ቼልሲ)

Image copyright Getty Images

የሊቨርፑሉ ዳንኤል ስታሬጅ ወደ ቼልሲ የላካትን ኳስ አዝፕሊኬታ የመከተበት መንገድ በጣም ቢያስገርመኝም የሞሐመድ ሳላህን ኳስ የተከላከለበት ሁኔታ ሳይ እጅግ ደንቆኛል።

ባለፈው የውድድር ዘመን ዳቪድ ሉዊዝ ለቼልሲ ሲያከናውን የነበረውን ሁሉ አዝፕሊኬታ አሁን ላይ እያደረገ ይገኛል። ሉዊዝንም ተጠባባቂ ወንበር ላይ ማስቀመጡን ተያይዞታል። ብቃቱ በጣም እየጨመረም ይገኛል።

ተከላካይ - ቪንዜንት ኮምፓኒ (ማንችስተር ሲቲ)

Image copyright Getty Images

ሲቲ ያስተናገዳት ጎል ለየት ያለች ነበረች። ሃደርስፊልዶች ነጥብ ይዘው እንዲወጡም ታግዛለች ብዬ አስቤ ነበር። ኮምፓኒ ሜዳ ውስጥ በነበረበት ደቂቃ ሙሉ የራሱን ድርሻ ብቻ ሳይሆን የቡድን አጋሩ የሆነው ኒኮላስ ኦታሜንዲን ድርሻንም ሲወጣ ነበር።

ጋርዲዮላ በ70ኛው ደቂቃ ቡድኑ ውስጥ አለ የሚባለውን ተከላካይ አስወጥቶ በምትኩ ወደፊት የሚጓዝ አማካይ ማስገባቱ በራሱ ሶስት ነጠብ የሚያሰጥ ድፍረት የተሞላው ድርጊት ነበር።

ተከላካይ - ራያን በርትራንድ (ሳውዝሃምፕተን)

Image copyright Getty Images

በዘመናዊ እግር ኳስ በድፍረት ኳስን ወደ ጎል የሚልኩ ተጫዋቾች ማየት እጅግ አዳጋች ቢሆንም ቤርትራንድ ግን ይህንን አድርጓል።

ወደ ዱሳን ታዲች የላካት ኳስም ውጤታማ ሆና የጨዋታውን የመጀመሪያ ጎል አሳይታናለች።

ለቻርሊ ኦስቲን የላካት ኳስ ደግሞ ሌላኛዋ ተጫዋቹ ያለበት ብቃት እጅግ አስደናቂ መሆኑን የምታሳይ ናት።

አማካይ - ሞሐመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)

Image copyright Getty Images

ባለፈው ሳምንት ሳላህን በሳምንቱ ምርጥ አስራ አንድ ውስጥ ሳስገባው የአጨራረስ ብቃቱ በጣም እየጨመረ እንደመጣ ተናግሬ ነበር።

በዚህ ሳምንት ቡድኑ ከቼልሲ ጋር በነበረው ጨዋታ ሳላህ ይህንን ማረጋገጥ ችሏል። ሁሌም የማስበው ሊቨርፑል የተከላካይ ክፍሉ ጠንካራ ቢሆን የት ይደርሳል የሚለው ነው። አሁን ያሉበት ደረጃ ላይ ይገኙ ነበር?

አማካይ - ዊል ሁጌስ (ዋትፎርድ)

Image copyright Getty Images

ሁጌስ ባለፈው ሳምንት ቡድኑ ከዌስትሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ባሳየው ብቃት በምርጥ አስራ አንድ ውስጥ ላካትተው አስቤ ቦታ አጥቼለት ነበር።

ነገር ግን ከአማካይ ሥፍራ ላይ ሆኖ የሚያስቆጥራቸው ጎሎች በዚህ ሳምንት እንዳካትተው አስገድዶኛል።

በእንግሊዙ ጋሬዝ ሳውዝጌት የዓለም ዋንጫ ቡድን ውስጥ ተካቶ ያስገርመን ይሆን? አቋም በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ሊፈጠር የማይችል ነገር እንደማይኖር አስባለሁ።

አማካይ - ሩበን ሎፍተስ ቺክ (ክሪስታል ፓላስ)

Image copyright Getty Images

ሎፍተስ ቺክ ባሳየው ብቃት እንዳስገረመኝ መናገር ፈልጋለሁ። ለቼልሲ ሲጫወት ተመልክቼ ለምንድነው ይህ ተጫዋች መነጋገሪያ የሆነው ስል ነበር። ኳስ አያያዙ ጥሩ ቢሆንም ፍጥነት ግን አልነበረውም።

ነገር ግን ክሪስታል ፓላስ ከመጣ ወዲህ በራስ መተማመኑ በጣም መጨመሩን አስተውያለሁ። ኃላፊነት የመውሰድ ብቃቱም እጅግ ጨምሯል።

አማካይ - ራሂም ስተርሊንግ (ሲቲ)

Image copyright Getty Images

ራሂም ስተርሊንግ በፔፕ ጋርዲዮላ ጥላ ሥር ካረፈ ወዲህ የአቋም ለውጥ አሳይቷል። እንዲህ ለጎል ተጠምቶ አይቼውም አላውቅም።

በያዝነው የውድድር ዓመት ስተርሊንግ ለሲቲ ባለቀ ሰዓት የማሸነፊያ ጎል ሲያስቆጥር ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ስተርሊንግ በዚህ አቋሙ ዋጋውን ውድ እያደረገም ይገኛል።

አጥቂ - ኤን ሃዛርድ (ቼልሲ)

Image copyright Getty Images

አንፊልድ ላይ የነበረው ጨዋታ ቼልሲና ሃዛርድ የሚገርም ብቃት ያሳዩበት ነበር፤ በተለይ ደግሞ ወደ ባኩ ተጉዘው ካደረጉት የቻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ በኋላ እንዲህ ዓይነት ጨዋታን በአቻ መወጣት መቻላቸው።

ሃዛርድ አዲስ በተሰጠው የተደራቢ አጥቂነት ሚና እጅግ ጥሩ ሲንቀሳቀስ ነበር። ከዳኒ ድሪንክዋተር የተላከለት ኳስ ማስቆጠር ቢችል ጨዋታው ከዚህም የበለጠ ሊያምር ይችል እንደነበረ አስባለሁ።

አጥቂ - ሰርጂዮ አጉዌሮ (ሲቲ)

Image copyright Getty Images

በሃደርስፊልድ 1 - 0 እየተመሩ ባለቡት ሁኔታ አርጀንቲናዊው ሰርጂዮ አጉዌሮ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ልክ ልምምድ ላይ እንዳለ ነበር በነፃነት ያስቆጠራት።

ከዛም አልፎ አጉዌሮ በዚህ የውድድር ዓመት የለወጠው ትልቁ ነገር ኳስን ለቡድን ጓደኞቹ መልቀቅ መቻሉ ነው።