የሳምንቱ አጋማሽ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

የሳምንቱ አጋማሽ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት Image copyright GLYN KIRK

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሲቀጥሉ ዛሬ እኩለ ለሌት ገደማ መሪው ማንቸስተር ሲቲ ከሳውዝሃምፕተን እንዲሁም አርሴናል ከሃደርስፊል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ላውሮ የጫወታዎቹን ግምት እንዲህ ያስቀምጣል።

አርሴናል ከሃደርስፊልድ

Image copyright BBC Sport

አርሴናሎች ከበርንሌይ ጋር የነበራቸውን ጨዋታ በትግልም ቢሆን 1 - 0 በማሸነፍ ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። ነገር ግን ከሃደርስፊልድ ጋር የሚኖራቸው ጨዋታ ቀለል የሚል ይመስለኛል።

ሃደርስፊልዶች ማንችስተር ሲቲን ቢፈትኑም አመሻሽ ላይ ለራሂም ስተርሊንግ ጎል እጅ ሰጥተዋል። ከሲቲ የነበራቸው ጨዋታ በጣም እንዳዳከማቸው አስባለሁ።

ላውሮ፡ 3 - 0

ቦርንማውዝ ከበርንሌይ

Image copyright BBC Sport

ቦርንማውዝ ባለፈው ጨዋታቸው ከስዋንሲ አቻ ተለያይተዋል። ባለፉት ሳምነታት ካደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ የተሸነፉት። በነጥብ ወደላይ መገስገሳቸውንም ቀጥለውበታል።

በርንሌይ ሰንጠረዡ አናት ላይ ከሚገኙ አራት ቡድኖች ተርታ ለመሰለፍ የነበራቸው ተስፋ በአርሴናል በደረሰባቸው ሽንፈት ሳቢያ ከሽፏል። ነገር ግን አሰልጣኝ ሾን ዳይሽ ልጆቹ ባሳዩት አቋም ደስተኛ ነበር።

የዚህን ጨዋታ አሸናፊ መገመት እጅግ ስለሚያዳግት ነጥብ ይጋራሉ ብዬ እገምታለሁ።

ላውሮ፡ 1 -1

ቼልሲ ከስዋንሲ

Image copyright BBC Sport

ስዋንሲ በያዝነው የውድድር ዘመን ከሁሉም ቡድኖች ያነሰ ጎል ነው ያስቆጠረው፤ 7 ጎል በ13 ጨዋታዎች።

ስዋንሲዎች ከጨዋታው የተሻለ ነገር ለማግኘት የታቻለቸውን እንደሚያደርጉ ባውቅም ለኔ አንድና አንድ አሸናፊ ብቻ ነው ያለው።

ላውሮ፡ 2 - 0

ኤቨርተን ከዌስትሃም

Image copyright BBC Sport

ሮናልድ ኩመንን ካባረረ አንድ ወር ያለፈው ኤቨርተን አሁንም አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ፍላጎት ያለው አይመስልም። ባለፈው ከሳውዝሃምፕተን ጋር በነበራቸው ጨዋታም ተሸንፈዋል። የአጥቂ መስመራቸውም ሆነ የተከላካይ መስመሩ ምንም ቅርፅ የሌለው ቡድን ሆኗል ኤቨርተን።

ዌስትሃምን ይዘው ወደ ጉዲሰን ፓርክ የሚያቀኑት ዴቪድ ሞዬስ ከሌይስተር ጋር በነበራቻው ጨዋታ አቻ በመውጣት የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል።

ኤቨርተኖች በበኩላቸው በሳውዝሃምፕተን ከተረቱ በኋላ አሰልጣን አልባ ሆነዋል። ሞራላቸውም አሁን በጣም በመላሸቁ እኔ ግምቴ ዌስትሃም እንደሚያሸንፍ ነው።

ላውሮ፡ 0 - 1

ማንቸስተር ሲቲ ከሳውዝሃምፕተን

Image copyright BBC Sport

ሳውዝሃምፕተን በስተመጨረሻም ወደ ድል ተመልሰዋል። ነገር ግን ድሉን የተቀዳጁት ደካማ አቋም እያሳየ በሚገኘው ኤቨርተን ላይ ነው።

ከሲቲ የሚኖራቸው ጨዋታ ቀላል እንደማይሆን እሙን ነው። ምንም እንኳ ሲቲ በንፅፅር ከቀደመው አቋማቸው ቢቀንሱም ማሸነፋቸውን አላቆሙም።

ላውሮ፡ 2 - 0

ስቶክ ሲቲ ከሊቨርፑል

Image copyright BBC Sport

ስቶክ ሁሌም እንደሚያደርጉት የሚፋለሙ ይስለኛል፤ ምንም እንኳ ነጥብ በስተመጨረሻ ወደ ሊቨርፑል እንደምታቀና ባምንም።

ሊቨርፑሎች ከቼልሲ በነበራቸው ጨዋታ ጥሩ ተጫውተው ነበር። የተከላካይ ክፍላቸው የተሻለ ቢሆን ኖሮ ሶስት ነጥብ ይዘው ሊወጡም ይችሉ ነበር ባይ ነኝ።

1 - 2

ተያያዥ ርዕሶች