ከአፍሪካ የተላከው ደብዳቤ፡ ተፅዕኖው የዘለቀው የባህል ቅኝ ግዛት

French commentary on the Berlin Conference of 1884-1885: Otto von Bismarck, then Chancellor or Germany, is portrayed here wielding a knife over a sliced-up cake, labelled "Africa". His fellow delegates around the table look on in awe. Image copyright Alamy
አጭር የምስል መግለጫ አፍሪካ ሃገራት ድንበሮች በአውሮፓዊያን ተከለለ ነው

በተከታታይ እየቀረበ ባለው የአፍሪካ ጋዜጠኞች ደብዳቤ ኤልዛቤት ኦሄኔ የአፍሪካዊያን ማንነት በቀኝ ግዛት በነበረው አስተሳሰብ የተቃኘ መሆኑን ትገልጻለች።

እንግሊዘኛ ተናጋሪ የሆነው የካሜሮን አካባቢ አዕምሮዬ ውስጥ ነው። ለመገንጠል የሚቀርበው ጥያቄ ብዙም ያልተጓዝኩበትን መንገድ

እንድመርጥ አድርጎኛል።

ያላቸውን ነገር አጠናክረው በሚሄዱና በቅኝ ግዛት ወቅት የነበረው ጉዳይ በምክንያትነት በማይወቅሱት ላይ ትልቅ ዕምነት አለኝ።

የአፍሪካ ሀገራት አሁን ያለቡት ደረጃ የኋለኛው ጊዜያቸው እንዴት ለመቋቋም እንደሚችሉ ስለሚወስን ስለጉዳዩ ማሰብ ጀመርኩ።

የአውሮፓ ሃገራት ድንበሮች መልካም በሚባል መልኩ አይደለም የተመሠረቱት። የአውሮፓ ሃገራት ድንበሮች ሁሉም በሚባል ደረጃ በጦርነት የተመሠረቱ ናቸው።

በርሊን በሚገኝ ትልቅ ጠረጴዛ ላይ ከተሰራው ከእኛ ከአፍሪካዊያን ድንበር ይልቅ በጦርነት የተሰራው የእነሱ ድንበር ለምን ይበልጥ ሠላማዊ ሆነ?

እኛ አፍሪካዊያን የሃገራችንን ድንበር ራሳችን አላካለልነውም። ድንበሮቻችንን ያካለሉልን ደግሞ መሬቱን የያዙትን ህዝቦችን፣ ብሔሮችን ወይንም ቋንቋን ከግምት ሳያስገቡ እንዳመጣላቸው ነው የሳሉት።

ለዚህ ደግሞ እኔ ከማውቀው የጋና እና የቶጎ ድንበር በላይ ምሳሌ ሊሆን የሚችል የለም። በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለ መኖሪያ ቤት ማዕድ ቤቱ በአንዱ ሃገር ውስጥ ሲገኝ መኝታ ቤቱ ሌላ ሃገር ውስጥ ይገኛል።

አባቴ በድንበር አካባቢ ያለው የካካዋ እርሻ በዚህ ጉዳይ ላይ የግሌ ልምድ እንዲኖረኝ አድርጓል።

በአዝመራ ወቅት ምርቱ በየትኛው የድንበር ክልል ይድረቅ የሚለው የሚወሰነው ከሁለቱ ሃገራት ጥሩ ዋጋ በሚያወጣበት በኩል መሆኑን አስታውሳለሁ።

ኤልዛቤት ኦሄኔ፡

Image copyright Elizabeth Ohene

እነዚህ የቅኝ ግዛት ድንበሮች በአካባቢው የሚኖሩትን የተለያዩ ብሔሮች ብዙም ከግምት ያስገቡ አይደሉም።

ስለዚህ ተመሳሳይ ሰዎች በጋናና አይቮሪኮስት፤ ጋናና ቡርኪና ፋሶ እንዲሁም ጋናና ቶጎ ባሉ ሁለቱም ድንበሮች ይገኛሉ።

በዚህ ምክንያትም ተመሳሳይ ጎሳ የዓላቸው ሰዎች በአንደኛው የድንበር ወገን እንግሊዘኛ ሲናገሩ በሌላኛው ወገን ደግሞ ፈረንሳይኛ ይናገራሉ።

ተመሳሳይ ነገር በአብዛኛዎቹ የአህጉሪቱ 54ቱም ሃገሮች አለ።

እነዚህ ጎሳዎች በተለያዩ ሃገራት እንዳይቀሩ በማሰብ ድንበሮቹ በድጋሚ እንዲካለሉ ሃሳብ አልቀረበም።

ይህ ችግር በነጻነት ወቅት ሊፈታ የሚገባው ነገር ቢሆንም በወቅቱ የነበሩ መሪዎች ግን ይህንን አላደረጉም።

ተመሳሳይ ቋንቋ የሚናገሩ ሆኖም በሶስት ሃገራት ተለያይተው የሚኖሩ ሰዎች አዲስ ሃገር ተፈጥሮ አንድ ላይ እንዲኖሩም ሃሳብ አልቀረበም።

እዚህ ጋር ቋንቋ ስል በቀኝ ግዛት የመጡትን እንደ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ፖርቹጋልኛ ወይንም ስፓንኛን ያሉትን ሳይሆን የህዝቦቹን የራሳቸውን ቋንቋ ነው።

ሆኖም እንደሚታየው ለአጭር ጊዜ የቆየው ቅኝ ግዛት ትልቅ ተፅዕኖ በመፍጠር እንደህዝብ ወስኖናል።

'የጀርመን ሥርዓት በጋና'

እኔ የተወለድኩት ባጋናዋ ቮልታ ክልል ነው። ለአጭር ጊዜ ክልሉ በወቅቱ በጀርመን ሥር በነበረችው የያኔዋ ቶጎላንድ የአሁኗ ቶጎ ስር ነበር።

ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በኋላ የቶጎላንድ አካባቢ ለእንግሊዝ እና ፈረንሳይ ተከፋፈለ።

እ.አ.አ በ1950ዎቹ በነበረኝ ልጅነት ጊዜ ከሃምሳ ዓመት በታች በጀርመን የተገዛነው ሰዎች 'ህግ አክባሪዎች'፣ ሰዓት አክባሪዎች፣ የተሰጠነን የትኛውም ሥራ የምናከናውን ጎበዞችና በህግ እና በስርዓት የምናምን እንደሆንን በተደጋጋሚ ተነግሮኛል።

ይህ ደግሞ የሆነው የአካባቢው ጎሳ መገለጫ በመሆኑ ሳይሆን ለአጭር ጊዜም ቢሆን በጀርመን ቅኝ ግዛት ስር የቆየን ህዝቦች በመሆናችን ነው።

በተቃራኒው ደግሞ በጎልድ ኮስት የሚገኙና በእንግሊዝ ቅኝ የተገዙት ሰዎች ደግሞ ደንታ ቢሶች፣ ሞጋቾች እና ስራቸውን በሰዓታቸው የማያጠናቅቁ ህዝቦች ተደርገው ይገለጻሉ።

እንግሊዘኛ ተናጋሪ የሆኑት ካሜሮናዊያንም በጋና ከሚገኘው የቮልታ ክልል ህዝብ ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ነበራቸው።

እነሱም ለእንግሊዝና ለፈረንሳይ የተከፋፈሉት ከጀርመን ቅኝ ግዛት አካባቢዎች ውስጥ ናቸው።

ባካሄዱት ህዝበ ውሳኔም እንደ ቮልታ ክልል ሁሉ ሁለት አማራጭ ነበራቸው። የተወሰነው ናይጄሪያን ሲመርጥ መረጋጋት የተሳነው አካባቢ ደግሞ በፈረንሳይ ስር የምትገኘዋን ካሜሮንን መረጠ።

ራሳቸውን ችለው ሉዓላዊ ሃገር እንዲሆኑ ዕድል ያልተሰጣቸው ሲሆን ከዚያ ጊዜ በኋላም ደስተኛ መሆን አልቻሉም።

የካሜሮን አካል ከሆኑ በኋላ ትልቅ መገለል እንደደረሰባቸውም ያምናሉ።

'እንግሊዘኛ ቅዱስ ነው'

ዋነኛው ቅሬታቸው ደግሞ ብዙ ጊዜ የእንግሊዝን በሚመስለው የትምህርት እና የህግ ስርዓታቸው አብዛኛው ፈረንሳይኛ ተናጋሪ በሆነው በተቀረው የሃገሪቱ ክፍል ዕውቅና አለማግኘቱ ነው።

ከዚህ የሚብሰው እና እኔን ግራ የገባኝ ደግሞ ብዙዎቹ እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች እርስ በእርስ የባህል ቁርኝት ያላቸው እና "በቁጥር አነስተኛ" እንደተደረጉ ማሰባቸው ነው።

ከሃምሳ ዓመት በታች በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር ቆይተው እንግሊዘኛ ተናጋሪ ካሜሮናዊያን ይህንን ማንነት እንዴት ሊላበሱ ቻሉ?

ሁሌም ግራ የሚገባኝ እነዚህ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ካሜሮናዊያን የትኛውን የእንግሊዛዊያንን ባህሪ ወርሰው ነው ካሜሮን እንደሃገራቸው ልትሰማቸው ያልቻለችው።

አጭር የምስል መግለጫ እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች መገለል እንደሚደርስባቸው ይገልጻሉ

ስለ እንግሊዘኛ ተናጋሪው የካሜሮን ክፍል ውጥረት

ክሪኬት አይጫወቱም፤ የእንግሊዛዊያንን ምግብ አይመገቡም እንዲሁም የሙዚቃ ምርጫቸው ከእንግሊዛዊያን ጋር አይመሳሰልም።

ሆኖም "እንግሊዘኛ ተናጋሪ" እንደሆኑ እና "ቋንቋቸው" የሆነው እንግሊዘኛ ቅዱስ እንደሆነ እርግጠኞች ናቸው።

የፈረንሳይኛ ቋንቋ ከእንግሊዘኛ ይበልጣል በሚል ከአንግሊዘኛ ተናጋሪ ዜጎቻቸው በላይ እንደሆኑ የሚገልጹ አንዳንድ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆኑ ካሜሮናዊያንም ገጥመውኛል።

ስለዚህ ምናባዊ ጦርነት በእንግሊዘኛ እና ፈረንሳይኛ መካከል አለ። በካሜሮን እና በሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ አንዳንዴ እንግሊዘኛ እና ጣሊያንኛ መካከል እንዲሁም እንግሊዘኛ እና ፖርቹጋልኛ መካከል ጦርነት አለ። ምክንያቱም የራሳችን መለያ እንዲሆን የምንፈልገው ለአጭር ጊዜም ቢሆን ቅኝ በገዙን ማንነት ነው።

ቀኝ አገዛዝን ብዙ በከባዱ እናየው ነበር። ነገር ግን ተሳስቻለሁ።

ተያያዥ ርዕሶች