አርጀንቲና የጠፋውን ሰርጓጅ መርከብ መፈለጓን አቋረጠች

የአርጀንቲና ባህር ኃይል Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ የጠፉትን 44 የመርከቧን አባላትን በህይወት የማግኘት ተስፋ ተሟጧል

የአርጀንቲና ባህር ኃይል ከሁለት ሳምንት በፊት የጠፋችውን ሰርጓጅ መርከብ 44 አባላት ህይወት ለማትረፍ የሚያደርገውን ጥረት አቋርጧል።

"የጠፋችውን ሰርጓጅ መርከብ በመፈለግ ብርቱ ጥረት ብናደርግም ማግኘት ግን አልቻልንም።" ብለዋል የባህር ኃይሉ ቃል አቀባይ የሆኑት ኤኒሪኬ ባልቢ።

የጠፋችው ሰርጓጅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ መልእክት ያስተላለፈችው ህዳር 15 እሮብ ዕለት ነበር።

የመርከቧን ሰራተኞች ህይወት የማትረፍ ተስፋን ያጨለመው የጠፋችበት አካባቢ ተሰምቷል የተባለው ፍንዳታ ነው።

የባህር ኃይሉ እዚህ ውሳኔ ላይ ለምን ደረሰ?

ካቢቴን ባልቢ የሰርጓጅ መርከቧ ፍለጋ "አባላቶቻችንን የማግኘት እድል ከነበረን እጥፍ ቀናት በላይ ፈልገናል" ብለዋል።

አስተያየታቸው የጠፋችው ሰርጓጅ መርከብ አባላት ለማትረፍ ይፈጃል ተብሎ የተገመተውን ጊዜ ያሳያል።

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ካፒቴን ባልቢ "የፍለጋ ደረጃው ተቀይሯል" ብለዋል

ካፒቴን ባልቢ እንዳሉት የአባላቱን እጣፈንታ ለመናገር ባይቻልም "እስካሁን ፍለጋው በተካሄደበት አካባቢ ምንም የመርከቧን አካላት አልተገኘም።"

"የፍለጋ ደረጃው ተቀይሯል።" በርካታ ሰርጓጅ መርከቦችን አሰማርተን መርከቧ የጠፋችበት አካባቢ በባህር ወለሉ ዙሪያ የመርከቧን አካላት ወደመፈለግ ሄደናል ብለዋል።

ሰርጓጅ መርከቧ ላይ ምንድን ነው የተከሰተው?

ሳን ሁዋን የተሰኘችው የአርጀንቲና ሰርጓጅ መርከብ 44 ሰዎችን አሳፍራ ከተልዕኮዋ ወደ ዋና መቀመጫው እየተመለሰች ባለበት ወቅት ነወ "የኤሌትሪክ መቋረጥ" ሪፖርት የተደረገው።

መርከቧ ተልእኮዋን አቋርጣ ወደ ባህር ኃይሉ እንድትመለስ ወዲያውኑ ተነግሯት ነበር

የአርጀንቲና ባህር ኃይል ለመጨረሻ ጊዜ ከመርከቧ ጋር የሬዲዮ ምልልስ ያደረገው ህዳር 15 በ07:30 (10:30 GMT) ላይ ነበር። ያኔ የመርከቧ አባላትም ሰላም ነበሩ።

ተያያዥ ርዕሶች