የሳምንቱ የአፍሪካውያን ምርጥ ፎቶዎች

ከአፍሪካ እና በዓለም ዙሪያ ከሚኖሩ አፍሪካውያን የተመረጡ የሳምንቱ ፎቶዎች

የአክሱም ፅዮን ማርያም ቤተክርስትያን Image copyright Yirga Gebremedhn

በየዓመቱ ሕዳር 21 የአክሱም ፅዮን ማርያም በዓል በድምቀት ይከበራል። በርካታ ምዕመናን በዓሉን ለማክበር ከሃገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ይመጣሉ። በዚህም የተነሳ ምእመናን የአክሱም ፅዮንን ዳግማዊት እየሩሳሌም ይሏታል። በዚህ ዓመትም በሺዎች የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በስፍራው በመገኘት በዓሉን አክብረዋል።

በአምስተኛው የአፍሪካ እና የአውሮጳ ህብረት ጉባኤ ላይ ሰዎች የጎዳና ላይ ትርኢት ሲያቀርቡ በአቢጃን፥ አይቮሪ ኮስት Image copyright Reuters

ሐሙስ እለት ተወዛዋዦች በአይቮሪ ኮስት የንግድ ከተማ በሆነችው አቢጃን ጎዳናዎች የአውሮፓ አፍሪካ ህብረት ጉባኤ ሲከፈት የውዝዋዜ ትርኢት ሲያቀርቡ፤ የጉባኤው ትኩረት "ወጣቶች ላይ መዋዕለ ነዋይን ማፍሰስ" የሚል የነበረ ቢሆንም ውይይቱ ግን በፍልሰት ቀውስን አጀንዳ አድርጎ ነበር።

የስድስት አመቷ ሐቢባ ከስኳር በአሻንጉሊት ቅርፅ የተሰራ ባህላዊ ከረሜላ ታቅፋለች። በሰሜናዊ ካይሮ ታንታ መውሊድን ለማክበር እየተዘጋጁ ነው። ግብፅ ህዳር 24፣ 2017 Image copyright Reuters

የስድስት አመቷ ሐቢባ ከስኳር በአሻንጉሊት ቅርፅ የተሰራ ባህላዊ የከረሜላ ታቅፋለች። በሰሜናዊ ካይሮ ታንታ መውሊድን ለማክበር ሲዘጋጁ የሚሰሩት ይህ ባህላዊ ከረሜላ አሮሴት አል መውሊድ (የመውሊድ ሙሽራ) በመባል ይታወቃል።

ወይዘሪት ደቡብ አፍሪካ 2017 ዴሚ ሌይ ኔል ፒተርስ የ 2017 ወይዘሪት ዩኒቨርስ ተብላ ዘውድ ስትደፋ። ዴሚ ሌይ ኔል ፒተርስ 22 ዓመቷ ሲሆን የቁንጅና ዘውድን የደፋችው የኮሎምቢያ እና የጃማይካ ተፎካካሪዎቿን አሸንፋ ነው። ኔል ፒተርስ በቢዝነስ አስተዳደር የተመረቀች ሲሆን የአካል ጉዳተኛ እህቷ አርአያዋ እንደሆነች ተናግራለች። Image copyright AFP

እሁድ ዕለት ወይዘሪት ደቡብ አፍሪካ ዴሚ ሌይ ኔል ፒተርስ አሜሪካ በተካሄደ ውድድር የወይዘሪት ዩኒቨርስ ዘውዷን ደፍታለች። በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ ግን በተፈጥሯዊ ፀጉሯ የቀረበችው ወይዘሪት ጃማይካ ከፍተኛ ተወዳጅነትና አድናቆትን አግኝታለች። አንድ የቲውተር ተጠቃሚ"ጃማይካን ብቻ ሳይሆን የአለም ጥቁር ሴቶችን በአፍሮ ፀጉሯ በመወከል አኩርታለች " ብሎ አሞካሽቷታል።

ስቶርምዚ በሞቦ የሽልማት መድረክ ላይ ተገኝቶ አቀንቅኗል። Image copyright Getty Images

የጋና ደም ያለበት እንግሊዛዊው ስቶርምዚ በሞቦ የሽልማት መድረክ ላይ የዓመቱ ታላቅ አሸናፊ ነበር። ሦስት ሽልማቶችን አፍሶ ከመውሰዱ በፊት መድረኩ ላይ በቀጥታ ዘፈኖቹን ተጫውቷል።

የደቡብ ሱዳን ስደተኞች የዳንስ ቡድን Image copyright AFP

ቅዳሜ ዕለት የነገዎቹ ከዋክብት በሰሜን ኡጋንዳ በሚገኘው ቢዲ ቢዲ የስደተኞች መጠለያ ትርኢታቸውን አቅርበዋል። እነዚህ ተወዛዋዦች 'ዘ ዋይት ፋሚሊ' የሚባሉ ሲሆን የቢዲ ቢዲ የተሰጥኦ ውድድርን ለማሸነፍና በኡጋንዳ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ስልጠና ለማግኘት ተስፋ ሰንቀዋል።

በ ኡጋዱጉ የፀሐይል ኃይል ማመንጫ ሲመረቅ ፎቶ የሚያነሳ ግለሰብ Image copyright AFP

ረቡዕ ዕለት በምዕራብ አፍሪካ ትልቁ የሆነውን የፀሐይ ኃይል ማምረቻ ሲመረቅ ፎቶ እያነሳ ያለ ተሳታፊ። የቡርኪናፋሶ መብራት ኃይል ተቋም እንዳለው በዋጋዱጉ አቅራቢያ የተተከለው እና 55 ሺህ ሄክታር ላይ የሰፈረው የፀሀይ ኃይል መሰብሰበያ 10 ሺዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

የዝምባብዌ መከላከያ ኃይል አባል ለምናንግዋ በዓለ ሲመት ልምምድ ላይ በነበሩበት ወቅት ያሳየችው አስቂኝ ፊት Image copyright AFP

የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት ዝግጅት ከመከበሩ በፊት ልምምድ እያደረጉ ከነበሩ ወታደሮች መካከል አንዷ አስቂኝ ፊት ስታሳይ በካሜራ እይታ ውስጥ ገብታለች።

የሞሮኮ ህፃናት አርብ ዕለት በዋና ከተማዋ ራባት ወደ ሚገኘው ትልቁ መስኪድ ዝናብ እንዲዘንብላቸው ለመፀለይ ሲሄዱ Image copyright AFP

አርብ ዕለት የሞሮኮ ህፃናት በዋና ከተማዋ ራባት ወደሚገኘው ትልቁ ሴል መስኪድ ዝናብ እንዲዘንብላቸው ለመፀለይ ሲሄዱ። የሃገሪቱ ንጉሥ ዜጎች ድርቅ እንዳያጠቃቸው ለዝናብ ፀሎት እንዲያደርጉ አዋጅ አስነግረው ነበር።

በሜዲትሪያን ውቅያኖስ ላይ ስደተኛው የተራድኦ ድርጅት ጀልባ ላይ ለመድረስ ከሞገድ ጋር ሲታገል Image copyright AFP

ረቡዕ ዕለት ስደተኞችን የያዘች ጀልባ በሜዲትራንያን ውቅያኖስ ላይ ከሰጠመች በኋላ የተራድኦ ድርጅት ጀልባ ለነፍስ አድን ሥራ ስትደርስ ከሞገዱ ጋር የሚታገል ስደተኛ አግኝታለች።

አፍሪካውያን ስደተኞች በሊቢያ ትሪፖሊ የስደተኞች ማቆያ Image copyright AFP

አፍሪካዊያን ስደተኞች ከሊቢያ ዋና ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ማቆያ ማዕከል የተነሱት ፎቶ። ሰሞኑን እነዚህ ስደተኞች ለባርነት የመሸጣቸው ወሬ ከተሰማ በኋላ የዓለም ህዝብ ክስተቱን በአንድ ድምፅ ኮንኖታል።

አልጂሪያዊ ገበሬ በመንደሪን ለቀማ ላይ Image copyright EPA

አልጄሪያዊው ገበሬ በመንደሪን ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ መንደሪን ሲለቅም። የአልጄሪያዋ ቦውፋሪክ የብርቱካን ከተማ በመባል ትታወቃለች።

ህፃናት በጃዜራ ባህር ዳርቻ ሲጫወቱ Image copyright AFP

አርብ ዕለት የሶማሊያ ህፃናት ከሞቃዲሾ ወጣ ብሎ በሚገኘውና ተወዳጅ በሆነው ጃዜራ ባህር ዳርቻ ሲጫወቱ

ፎቶዎቹ የተወሰዱት ከኤኤፍፒ፣ ኢፒኤ፣ ጌቲ ኢሜጅስ እና ሮይተርስ ነው።