ሴቶች እንዲደፈሩ ያበረታታው ግብጻዊ የህግ ባለሙያ ተፈረደበት

Nabih al-Wahsh has previously denied the holocaust
አጭር የምስል መግለጫ ዋህሽ በእስራኤላዊያን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ "ምናባዊ" ሲል ገልጾታል።

የተቀዳደደ ጂንስ የሚለብሱ ሴቶች ቅጣታቸው ተገደው መደፈር ሊሆን እንደሚገባ የገለጸው ግብጻዊ የህግ ባለሙያ በሦስት ዓመት እስር ተቀጣ።

ወግ አጥባቂ እንደሆነ የሚነገርለት ናቢህ አል-ዋህሽ ከእስር ቅጣቱ በተጨማሪ 1130 ዶላር እንዲከፍልም ተወስኖበታል።

በአንድ የቴሌቭዢን ጣቢያ ላይ ሴተኛ አዳሪነትን አስመልክቶ በተዘጋጀ ረቂቅ ህግ ላይ በተደረገ ክርክር ወቅት ነው የህግ ባለሙያው አስተያየቱን የሰጠው።

"አንዲት ሴት ግማሽ ሠውነቷን እያሳች ስትሄድ ስታዩ ደስተኛ ትሆናላችሁ?" ብሎ ጠይቋል።

"አንዲት ሴት እንደዛ ሆና ስትሄድ ወሲባዊ ትንኮሳ ማድረግ የጀግንነት ተግባር ሲሆን አስገድዶ መድፈር ደግሞ ብሔራዊ ሃላፊነት ነው" ብሏል።

የተቀዳደደ ልብስ የሚለብሱ ሴቶች "ወንዶች ትንኮሳ እንዲያደርሱባቸው እየጋበዙ ነው" ያለው ዋህሽ፤ "ሞራልን መጠበቅ የሃገርን ድንበር ከመጠበቅ በላይ በጣም አስፈላጊ ነው" ብሏል።

ብዙዎች በባለሙያው ላይ ቅሬታ ካሰሙ በኋላ ነበር አቃቤ ህግ ክስ ያቀረበበት።

ብሔራዊ የሴቶች መብት ምክር ቤት አስተያየቱ ላይ ቅሬታ አቅርቦ "ከግብጽ ሕገ-መንግሥት በተጻጻሪ" ሴቶች ተገደው እንዲደፈሩ የቀረበ "ሕገ-ወጥ ጥሪ" ነው ብሏል።

ምክር ቤቱ ከሁለት ሳምንት በፊት በቴሌቭዥን ስለተላለፈው ጉዳይ ለመገናኛ ብዙሃን ቁጥጥር ካውንስል ቅሬታውን አስገብቷል።

ዋህሽ ከዚህ ቀደም በእስራኤላዊያን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ "ምናባዊ" ሲል ገልጾ ፀረ-አይሁድ መሆኑን በበይፋ ተናግሯል።

በሌላ ወቅት "አንድ እስራኤላዊ ካገኘሁ እገላለሁ" ሲል ለአንድ ቴሌቭዥን ጣቢያ አስታውቋል።

ባለፈው ዓመትም ዋህሽ ሴቶች ሁሌም ጸጉራቸውን መሸፈን አይጠበቅባቸውም ካሉ ከአንድ የሃይማኖት መሪ ጋር በተሌቭዥን ስቱዲዮ ግጭት ውስጥ ገብቶ ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች