የጋሬት ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን፡ ደ ሂያ፣ ማቲች፣ ፊርሚኖ፣ ሞሰስ፣ ሊንጋርድ፣ ሃዛርድ

Manchester United keeper David de Gea Image copyright Rex Features
አጭር የምስል መግለጫ ደ ሂያ ከአርሴናል ጋር በነበረው ጨዋታ 14 ኳሶችን አድኗል

የፕሪሚር ሊጉ አናት ላይ የሚገኙት ማንቸስተር ሲቲዎች ባለቀ ሰዓት ጎል እያስቆጠሩ ማሸነፋቸውን ቀጥለዋል።

ቼልሲዎች ደግሞ ኒውካስትልን 3 ለ 1 ማሸነፍ ችለዋል።

በስቶክ የተሸነፉት ስዋንሲዎች በሊጉ ግርጌ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።

የጋሬት ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን እነሆ።

ግብ ጠባቂ - ዴቪድ ደ ሂያ (ማንቸስተር ዩናይትድ)

ከ2003/204 የፕሪሚር ሊጉ ውድድር በኋላ ነው ዴቪድ ደ ሂያ ከአርሴናል ጋር በነበረው ጨዋታ 14 ኳሶችን በማዳን ክብረወሰኑን ለመጋራት ችሏል።

ከዚህ በፊት ይህንን ማሳካት የቻሉት ቪቶ ማኖኔ እና ቲም ክሩል ናቸው።

ማንቸስተር ዩናይትድ የሊጉን ዋንጫ ካነሳ ዋነኛው ምክንያት ደ ሂያ ነው። ከአርሴናል ጋር በነበረው ጨዋታ ተጫዋቹ ድንቅ ነበር።

ተከላካይ - አንቶኒዮ ቫሌንሽያ (ማንቸስተር ዩናይትድ)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ቫሌንሽያ ዘንድሮ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል

አንቶንዮ ቫሌንሽያ በዘንድሮው የሊጉ ውድድር ሁለተኛ ጎሉን አስቆጥሯል። ከዚህ ቀደም በአንድ ዓመት ብዙ ጎሎችን ያስቆጠረው በ2011/12 ውድድር ዘመን ሲሆን አራት ጎሎችንም ከመረብ አሳርፎ ነበር።

ዘንድሮ የተከላካዩ አቋም ምርጥ ሲሆን ይህም በዚሁ ይቀጥላል። በቡድኑ ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ በማሳረፍ ላይም ይገኛል።

ይህ የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድን ከሜዳው ውጭ ትክክለኛ አቋም ካሳየባቸው ጨዋታዎች አንዱ ሲሆን ቫሌንሺያ ደግሞ ይህን አሳክቷል።

ተከላካይ - አንድሪያስ ክርስቲያንሰን (ቼልሲ)

Image copyright Empics
አጭር የምስል መግለጫ ክርስቲያንሰን ከተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ቼልሲ በአንዱ ብቻ ነው የተሸነፈው

ክርስቲያንሰን ከተሰለፈባቸው ስምንት ጨዋታዎች ቼልሲ የተሸነፈው በአንዱ ብቻ ነው።

ተጫዋቹ ለክለቡ የመጀመሪያውን ጎል እንዳያስቆጥር የጎል ብረት እንቅፋት ሆኖበታል።

ክርስቲያንሰን በሉዊዝ ደረጃ የማይገኝ ተጫዋች ቢሆንም አሁን ያለውን ዕድገት ጠብቆ የሚቀጥል ከሆነ አንቶንዮ ኮንቴ ብራዚላዊውን በዚህ ዓመት መጨረሻ ሊለቁ ይችላሉ።

ተከላካይ - አሽይ ዊሊያምስ (ኤቨርተን)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ዊሊያምስ ዘንድሮ ከየትኛውም የቡድን አጋሮቹ በላይ ኳሶችን ተከላክሏል

አሽሊይ ዊሊያምስ በዘንድሮው ዓመት ከየትኛውም የኤቨርተን ተጫዋች በላይ ብዙ ኳሶችን ተከላክሏል።

የሳም አላርድየስ ወደ ኤቨርተን መምጣት ከፍተኛ ለውጥ አምጥቷል።

አሰልጣኙ ቡድኑን ከወራጅነት ለማትረፍ ቃል ገብተዋል።

ተጫዋቾቹ ይህንን ዓላማ ምንያህል እንደሚጋሩት ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

ተከላካይ - ቪክተር ሞሰስ (ቼልሲ)

Image copyright Rex Features
አጭር የምስል መግለጫ ሞሰስ ከጥር በኋላ ጎል በሚሆን ኳስ ላይ ተሳትፏል

ለጎል የሚሆን ኳስ ያቀበለው ቪክተር ሞሰስ ከጥር በኋላ ጎል በሚሆን ኳስ ላይ ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው።

ከሁለት ዓመት በፊት ከክለብ ክለብ ሲዘዋወር የነበረውን ተጫዋች ያለውን ችሎታውን ያወቀለት አልነበረም። ሞሰስ በቼልሲ የፕሪሚር ሊጉንና የዩሮፓ ሊግን ማሸነፍ ችሏል።

አሰልጣኝ ኮንቴ መደበኛ የነበረውን ተጫዋች ወደ ትልቅነት ቀይረውታል። ሌሎች ግን ይህንን ማድረግ አልቻሉም።

አማካይ - ዴቪድ ሲልቫ (ማንቸስተር ሲቲ)

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሲልቫ በ11 ጨዋታዎች በስምንት ጎሎች ላይ ተሳትፏል

ዴቪድ ሲልቫ ባለፉት 11 የሊጉ ጨዋታዎች በስምንት ጎሎች ላይ ተሳትፎ ነበረው።

ዌስትሃሞች ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ጥሩ የተጫወቱ ሲሆን ውጤት ይዘው መውጣት ይገባቸው ነበር ብዬም አስባለሁ።

ዴቪድ ሲልቫ ከዌስት ሃም ጋር የነበረው ጨዋታ ከአንድ አምበል የሚጠበቅን ሃላፊነት ተወጥቷል። ማንቸስተር ዩናይትዶች በሚቀጥለው ሳምንት የማንቸስተር ደርቢ ሊጠነቀቁ ይገባቸዋል። ሲቲዎች ጥሩ ባልሆኑበት ወቅትም ነጥብ እየሰበሰቡ ነው።

አማካይ - ኔማንያ ማቲች (ማንቸስተር ዩናይትድ)

Image copyright Empics
አጭር የምስል መግለጫ ማቲች ማንቸስተር ባሸነፈባቸው ሁሉም ጨዋታዎች ከተሰለፉ ተጫዋቾች አንዱ ነው

ማንቸስተር ዩናይትድ ዘንድሮ ማሸነፍ በቻለባቸው 11 ጨዋታዎች መሰለፍ ከቻሉ አራት ተጫዋቾች አንዱ ኔማንያ ማቲች ነው።

ማቲች አርሴናል በማጥቃቱ በኩል ሲበረታ ተከላካዩን ሸፍኖ የተጫወተ ሲሆን ቡድኑ በመልሶ ማጥቃት እንዲሳተፍም አድርጓል።

ደ ሂያ፣ ማቲች እና ቫሌንሽያ የማንቸስተር ዩናይትድ የዋንጫ ተስፋዎች ናቸው። እነዚህ ተጫዋቾች ጤነኛ ከሆኑ እንደ ፖል ፖግባ ያሉት ተጫዋቾች በማጥቃቱ ረገድ ነጻነት ይኖራቸዋል። ይህ ግን የሚሆነው ፖግባ ሜዳ ላይ ካለ ብቻ ነው።

አማካይ - ፊሊፔ ኩቲንሆ (ሊቨርፑል)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ኩቲንሆ ባለፉት 10 ጨዋታዎች በአስራ ሁለት ጎሎች ላይ ተሳትፎ ነበረው

ፊሊፔ ኩቲንሆ ባለፉት 10 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች 12 ጎሎች ላይ ተሳትፎ ነበረው።

ኩቲንሆ ካለው የቅጣት ምት ብቃቱ በተጨማሪ ጥሩ ፈጣሪ ተጫዋች ነው።

ብራይተኖች ተጫዋቹን ፍጹም ቅጣት ምት መከላከል አለመቻላቸው ብቻ ሳይሆን የመከላከያ አጥሩ ሲንቀሳቀስ ምን እንደሚፈጠር ታይቷል። ዋናው ነጥብ መከላከያ አጥሩ መንቀሳቀስ የለበትም ነው። ከተንቀሳቀሰ በተጫዋቾቹ መሃል ወይም በእግራቸው ስር ኳስ ያልፋል። ይህ ደግሞ የግብ ጠባቂ ችግር አይደለም።

አጥቂ - ኤደን ሃዛርድ (ቼልሲ)

Image copyright Rex Features
አጭር የምስል መግለጫ ሃዛርድ በአስር ጨዋታዎች አስራ አንድ ጎሎችን አስቆጥሯል

ቼልሲ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች ላይ ኤደን ሃዛርድ አስራ አንድ ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል።

ቤኒቴዝ አስፈላጊው ድጋፍ ከተደረገላቸው ኒውካስትልን ለሊጉ ዋንጫ ተፎካካሪ እንደሚያደርጉት አምናለሁ።

ይህን ደግሞ በቫሌንሽያም አሳይተውናል። እንደባርሴሎ እና ሪያል ማድሪድ ያሉ ትልልቅ ቡድኖችን ማስቆም ከቻሉ ሁለቱን የማንቸስተር ቡድኖች ማቆም ይችላሉ።

አጥቂ - ሮቤርቶ ፊርሚኖ (ሊቨርፑል)

Image copyright Rex Features
አጭር የምስል መግለጫ ፊርሚኖ ሊቨርፑልን ከተቀላቀለ በኋላ 26 የሊግ ጎሎችን አስቆጥሯል

ከነሐሴ 2015 ጀምሮ በፕሪሚር ሊጉ መጨጫወት የቻለው ሮቤርቶ ፊርሚኖ 26 ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ይህ ደግሞ ከሊቨርፑል ተጫወቾች ቀዳሚው ያደርገዋል።

ብራይተን በሊቨርፑል እንደሚሸነፍ ብጠብቅም በዚህ መልኩ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም። ሊቨርፑሎች ድንቅ አቋም አሳይተዋል።

ፊርሚኖም ቢሆን የኩቲንሆን እና የሳላሃን አስደናቂ ችሎታ ሊጠቀምበት ችሏል።

አጥቂ - ጄሴ ሊንጋርድ (ማንቸስተር ዩናይትድ)

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ሊንጋርድ በሁለት ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን አስቆጥሯል

ጄሴ ሊንጋርድ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን በፕሪሚር ሊጉ አስቆጥሯል። ይህ ደግሞ ቀደም ሲል በ51 ጨዋታዎች ካስቆጠራቸው ጋር ተስተካካይ ነው።

ለሳምንታት ሞውሪንሆ እነዚህን ተጫዋቾች ማጫወት እንዳለበት ስናገር ቆይቻለሁ። ከሊቨርፑል ጋር በአንፊልድ በነበረው ጨዋታም ይህን ማድረግ ነበረበት።

ማንቸስተር ዩናይትዶች በመልሶ ማጥቃት ውጤታማ ከመሆናቸውም በላይ በዚህ ውስጥ የሊንጋርድ ሚና ከፍተኛ ነበር። ተጫዋቹ ከአማካይ ቦታ ኳስን ወደ ማጥቃት የሚቀይርበት መንገድ አስደናቂ ነበር።